Page 1 of 1

ድፊት

Posted: 29 Jul 2021, 17:26
by Horus
ድፊት የቆቅ ማደኛ ብልሃት ነው። ልጆች ሆነን ቆቅ የምናድነው በድፊት ነበር። ቆቅ እንደ ሚታወቀው በጣም ጥንቁቅ ወፍ ነች፣ በቀላሉ ለመያዝ ታስቸግራለች ። ታዲያ የኛ ብልሃት (መች እንደ ተጀመረ ባላቅም) ድፊት መስራት ነበር ። የቃሉ ውስጠ ትርጉም ወጥመድ ማለት ነው ። ድፊት አንድ ትልቅ ሳጤራ ወይም ትንሽ የቤት ክዳን ይመስላል። ከሸምበቆ እና ልጣጭ ነው የምንሰራው ። ከላይ ለጅ ማስገቢያ ቀዳዳ መስኮት እናበጅለታለን ።

ታዲያ ቆቆች በሚደበቁበት ጫካም ሆነ ቁጥቋጦ ወስጥ ይህን ቅርጫት ወስደን ባንድ በኩል ከፍ አደገን ከስር ከፈት በማድረግ በትንሽ ባላ እንደግፈዋለን፣ በባለው ወደ ላይ በመያዝ ማለት ነው ። በባላው ትክክል በድፊቱ ወስጥ ነጫጭ ቦቆሎ ፍሬዎች እንበትናለን፣ ቆቆቹን ለማማለል ማለት ነው ። ይህን አድረገን ወደ ከብት ጥበቃና ጨዋታችን እንሄዳለን።

አሁን ቆቆች ልክ እንደ ዶሮ ጥሬያቸውን ለመጫር ዘው ቱር ሲሉ ያን ያማረ ቦቆሎ ያያሉ። እየተንደረደሩ ለቦቆሎው ፍሬ ሲሽቀዳደሙ ከፍ አድርገን በከፈትንላቸው ክፍተት ሲገቡ ባላውን አብሮ ይጥሉታል። በዚያን ቅጽበት ድፊቱ መሬት ላይ ይደፋል ። ቆቆቹም ቦቆሎውን ለቅመው ከጨረሱ በኋላ ከባላው መውጣት አቅቷቸው እኛ በግዜያችን መጥተን ከላይ በሰራነው ትንሽ ቀዳዳ እጃችን አስገብተን ቆቋን ይዘን ከከብቶቻን ጋር ሲመሽ ወደ ቤት እንሄድ ነበር!

የቆቅ ስጋ በጣም ጣፋጭ ዶርን በእጅጉ የሚበልጥ ነው ።

ይህን የልጅነት ትዝታ ያመጣሁት የኢትዮጵያ ሰራዊት የዉጊያ ስልት ወይም ታክቲክ ቆቅን በድፊት የማደን ሜታፎርና ምስል ስለሆብኝ ነው ። እኒያ የጎንደርና የወሎ መሬቶች ነጫጩ ቦቆሎ ፍሬዎች ተመሰሉኝ። የትግሬ ባንዳዎች ይህን ቦቆሎ እያዩ ሰተት ብለው ድፊት ውስጥ ይገባሉ። ከዚያም ድሮን እያመለከተች ወታደርና ሄሊኮፕተር ይደበድባቸዋል!!

ለነገሩ ቆቅ ማሰብ ስለማትችል ነው የኛን የድፊት ብልሃት ማየት ያቃታት! የትግሬ ባንዳ ምነው አርፎ እዚያ እትግሬ ምድር ቢኖር ዘሎ ድፊት ከሚገባ ብዬ ነው ። የጎንደርና ወሎ ነጭ ቦቆሎ ቢቀርበት ማለቴ ነው !!


Re: ድፊት

Posted: 30 Jul 2021, 00:04
by Horus
ድፊት ወጥመድ ውስጥ የገባው የትግሬ ባንዳ በሚግ 23 ተደበደበ

Re: ድፊት

Posted: 30 Jul 2021, 00:26
by TGAA
ድፊት ወጥመድ ውስጥ የገባው የትግሬ ባንዳ በሚግ 23 ተደበደበ----
ሚግ 23 የ EIF እጅ ከ 42,000 feet ተዘርግቶ ዶጋ አመድ የሚያደርግ ክንድ
በነገራችን ላይ ቆቅ ከርሷ በላይ ቆቅ ያለ አይመስላትም ወያኔም እንደዚያው _ ያስቃል

Re: ድፊት

Posted: 30 Jul 2021, 02:56
by Horus
በቃ ቆቅ ቦቆሎ መሻቷን አትተው፣ በድፊቱ መጠመዷም እንዲሁ

Re: ድፊት

Posted: 30 Jul 2021, 15:09
by Horus
በድፊት የተጠመደው የትግሬ ባንዳ ቆቅ አሁን ደሞ የደም ግፊትና የኮለስትሮል መዳኒት ካልገባልኝ እያለ ነው ። :lol: :lol: :lol: