Page 1 of 1

ወልቃይት የማይደፈር ሆነ ለምን ራያ? ይህ ሳምንት ወሳኝ ነው!!የኦሮምያ ኃይል ገባ አልተባለም ነበር እንዴ?

Posted: 24 Jul 2021, 12:21
by Abaymado

ወልቃይት የማይበገር ነው የሆነው : ለምን? ምክንያቱም በደንብ ተዘጋጅተውበታል:: በደንብ የታጠቀ ኃይል አለ:: ያለው ችግር ከተከዜ ማለፍ አለመፈለጋቸው ነው::ተከዜ ላይ ቆሞ መጠበቁ ሌላ መከራ ማምጣት ነው :: ተከዜን ተሻግረው ቢገቡ ጥሩ ነበር:

የራያው ግን ችግር ያለበት ቦታ ነው::: መከላከያ ለመሆኑ አለ እንዴ? የኦሮምያ ኃይል ገባ አልተባለም ነበር እንዴ? አሁን እየተፋለጡ ያሉት አፋሮች እና አማራዎች ብቻ ናቸው::

እንደሚባለው ከሆነ ወያኔ በቆቦ እና በአፋር ሬሳ በሬሳ ቢሆንም አሁንም በ 6 መኪና ጭኖ እንደገባ ነው:: ቆቦ ላይ ደሞ እንደተከበቡ ነው የሚነገረው: መውጫ የላቸውም:: ለዚህም ነው ይህ ሳምንት ወሳኝ የሚሆነው::

መከላከያ ካልተዋጋ : የአማራ ልዩ ኃይል ሁሉንም መጨረስ ይችላል:: እናም የክልሉ መንግስት በደንብ የታጠቀ ኃይል በብዛት ማስፈር አለበት::



የእኔ ምክር: የሌለ የውሸት ፕሮፓጋንዳ አለበት :: ብዙ ሕዝብ አለን: እና የምን መቀባጠር ነው:: ተደመሰሰ ጁንታው አለቀለት ምናምን የህፃናቶች ዘፈን መቅረት አለበት ::