ጫወታው ደርቷል:: የዋንጫው ጫወታ ወደ ጥሎ ማለፍ ፍልሚያ ተሸጋግሮ አማራና ትግሬ እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ እያደረጉ ነው:: የዋንጫው ጫወታ በትግራይ ዋና ከተማ በመቀሌ ነው እየተደረገ ያለው:: በመጀመሪያ ደቂቃዎች አማራ በትግሬዎቹ ሜዳ በመጫወት የመጀመሪያዋን ጎል ያስቆጥራል ተብሎ ስታሰብ ትግሬዎች በኦፍ ሳይድ ስልት ወደፍት አፈገፈጉና አማራዎቹን ወደመሃል መለሱ:: ትግሬዎች በርትተው የጫወታውን ሁኔታ በመቀየር አማራን እስጨንቀዋል:: ብዙ ተጫዋቾች ከትግረው ቡድን በመጎዳታቸው ብዙ ቅያሪ እያደረጉ ጫወታውን በመቀጠል አማራን አስጨንቀዋል:: ከሁለቱ አሸናፊ ለዋንጫ ከኦሮሞዎቹ ጋር ይጫወታል::
የኦሮሞዎቹ ቀደም ብለው መዘጋጀት ፍሬ ያፈራ ይመስላል:: የኦሮሚያው አምበል ሽመልስ አዱኛ ከጥቅት ወራት በፍት ባደረገው ቃለምልልስ ኦሮሞዎች አሸናፊ ሆነው ለመውጣት እንደ አብይ አህመድ የመሰሉትን እንተርናሽናል ተጫዋቾችን እንደሚያሰልፉ ተናግሯል:: አብይ አህመድ የአመቱ ድንቅ ተጫዋች በመሆን የወርቅ ሜዳልያ በአውሮፓ መሸለሙ ይታወሳል::
ከሁለቱ ቀደም ብሎ ጎል ያስቆጠረ ከኦሮሞዎቹ ጋር ይጋጠማል:: ጫወታው በሰሜን መሆኑ ለኦሮሞዎቹ መልካም እድል ነው:: የሰሜኑ አሸናፊ በጣም የሚዳከም ስሆን ኦሮሞዎቹ በቀላሉ እንደሚያሸንፉ ይጠበቃል::