አማራ እያደረገ ያለውን የህልውና ጦርነት አሸናፊ መሆነ ከፈለገ ከፌደራል መንግስቱም ሆነ ከመከላከያው ራሱን ነጥሎ በራሱ በአማራው ልጆችት የሚታዘዝ ህዝባዊ ሰራዊት አደራጅቶ ሊታገል ይገባዋል!!
****************
በሰልማን መሀመድ የተፃፈ
የቀነጨረው ብልፅግና ፖለቲካዊ አካሄድ
-
ብልፅግና ለአለም አቀፉን ማህበረሰብ የህወሀትን ማንነት አሳያለሁ በሚል የከሰረ ሎጂክ ህወሀት በራያ እና በአፋር የምታደርገውን መስፋፋት ቆሞ እየተመለከተ ነው።
ህወሀት ከምታደርገው ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች አንፃር አፋርን በ ዞን 4 ወይም 2 በኩል እንደምትወር ይታወቅ ነበር። እኛም ምንድን ነው የምትጠብቁት ስንላቸው "ትእዛዝ አልተሰጠንም" ሲሉ ቆዩ ይህን ጊዜ 3 ነገሮችን አሰብን
1-- Conversational ጦርነት ለማድረግ ታስቦ ከከተማ እስኪወጡ እየተጠበቀ ነው።
2-- ሰላማዊ ሰዎች የጦርነቱ ሰለባ እንዳይሆኑ ህወሀት ሙሉ ሀይሉን ከከተሞች እስኪያስወጣ እየተጠበቀ ነው።
3-- ህዝባዊ ድጋፍ ከሚያገኝበት አከባቢ እስከሚወጣ እየተጠበቀ ነው።
.
የአለም ተስፋ ነኝ የሚለው ብልፅግና ይህን ሁሉ የሚጋጋጠው የህወሀትን ተስፋፊነት ፣ ሴት ደፋሪነት ፣ አውዳሚነት ፣ አፈናቃይነት ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ አሳያለሁ ብሎ ነው።
.
እዉነታው ግን ብልፅግና አፋርን እና ራያ ቆቦን ሆነ ብሎ በህወሀት እንዲወረሩ አድርጎ "እዩልኝ ፍረዱኝ" እያለ ቢጋጋጥ ምእራባውያን ለብልፅግና የሚራራ አንጀት አላሳዩም ሌላው ቀርቶ ህወሀት የአለም አቀፉን የጦርነት ህግ (International Humanitarian law) እና አለም አቀፉ የህፃናት መብቶች ስምምነትን (Conversation on right of child) በግልፅ ሲጥስ እየተመለከቱ እንኳን ጥርሳቸውን አልነከሱበትም።
.
በዚህ የብልፅግና ቀሽም የፖለቲካ ጭዋታ ግን ከ54,000 በላይ የአፋር ወንድሞቻችን ተፈናቅለዋል ፣ ከ80 በላይ ሴቶች አፋር ላይ ተደፍረው ደሴ ሆስፒታል ተኝተዋል ፣ ከራያ አላማጣ እና ኮረም ከ20,000 በላይ ሰው ተፈናቅሎ ቆቦ ወልድያ እና መርሳ ገብቷል ፣ በኮረምና በአላማጣ ብቻ ከ90 በላይ ንፁሀን ተገድለዋል።
.
ይህ ሁሉ ዋጋ የሚከፈለው ግን የህወሀትን አረመኔነት አጋለጬ አለም አቀፉን ማህበረሰብ ከጎኔ አሰልፋለሁ ከሚል መሬት ላይ ያለውን ነባራዊ እውነታ ያላገናዘበ ከንቱ ምኞት የተነሳ ነው።
.
በሌላ በኩል ኦህዴድ /ODP/ መራሹ መንግስት ይሄን የምእራባውያን regime Change (የመንግስት አገዛዝ ለውጥ) ፍላጎት መረዳት አቅቶት ፤ ህወሀት ለስልጣኑ ስጋት እስካልሆነች ድረስ በትንሽ በትንሹ እየደቆሰ እድሜዋን እንዲቀጥል እንጂ ሙሉ ለሙሉ የመደምሰስ ፍላጎት እንደሌለው እያንዳንዱ እርምጃዎቹ ምስክር ናቸው። ቢያንስ 200 መኪና ሙሉ ወታደር ከመቀሌ ለማስወጣት ምርጫው እስኪያልፍ የጠበቀ አጭበርባሪ መንግስት መሆኑ አይተናል።
.
መፍትሄው
.
አማራ እንደ ህዝብ ከፌደራል መንግስቱም ሆነ ከመከላከያው ራሱን ነጥሎ በራሱ በአማራው የሚታዘዝ ህዝባዊ ሰራዊት እና አለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ግንባታ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት አለበት። አሁን ባለን ሀይል እየተከላከልን በሚቀጥሉት 6 ወራት ውስጥ ከ 350,000 እስከ 500,000 የሚሆን ጠንካራና ተገዳዳሪ ሰራዊት አሰልጥኖ ብቁ ያድርግ።