Page 1 of 1

እንዲህማ አታዋርዱን!

Posted: 23 Jul 2021, 14:17
by sarcasm
እንዲህማ አታዋርዱን!

By Abayneh Kassie

ካህናት ልብሰ ተክህኖ የሚለብሱት፣ ጽንሐሕ የሚይዙት፣ የመፆር መስቀል የሚያወጡት፣ ጃንጥላ የሚዘረጉት ለመንፈሳዊ ዓላማ ብቻ ነው፡፡ ይህም ማዕከላዊነቷን በጠበቀችው ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አመራር የሚፈጸም ነው፡፡ እንዲህ ባለ ወግ “ሰላማዊ ሰልፍ” እንዴት ሊወጡ ቻሉ? እውነት እውነት እላለሁ ቤተ ክርስቲያን ለብቻዋ ሕወሐትን ልቃወም ብላ ብትሰለፍ ሺህ ምክንያቶች ስላሏት ባልጎረበጠኝ፡፡ ይህ ግን አመመኝ፡፡

እያንዳንዱ ቄስ ወይም ዲያቆን ወይም መነኮስ በግሉ ቢሰለፍ ችግር የለብኝም፡፡ እንደዚህ ግን ተቋማዊ በመሰለ ኹኔታ ሰልፍ መውጣት የሰልፉ ዓላማ ምንም ይኹን ምን የማዕከላዊቷን ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መጣስ ነው፡፡ ሲቀጥል የሰላምና የአንድነት ጥሪ ሊያስተላልፉ የሚገባቸው ሰዎች ለተቃራኒው መቆማቸው እጅግ ያዋርዳል፡፡

ኦርቶዶክሳዊያን ብዙ ሥራ እንዳለብን ግልጽ ነው፡፡ በወዲያም በወዲህም ቤተ ክርስቲያንን የሚከፋፍሉ ነገሮች አደገኞች ናቸው፡፡

ከወንጌል ከተማ ከመስቀል ዓላማ አያናውጠን!


Please wait, video is loading...

Re: እንዲህማ አታዋርዱን!

Posted: 23 Jul 2021, 14:28
by Abere

Re: እንዲህማ አታዋርዱን!

Posted: 20 Aug 2023, 09:02
by sarcasm
ሃፍረትቢሱ አባይነህም ይህን ያህል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ካፈረ፤ ተራ ምእመናን ምን ያህል ያፍሩ ይሆን?

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን እንደ ተቋም ከብልጽግና ጋር መወገንዋ የሚጠራጠር የለም።