(ለአንባቢዎቼ)
Kibrom Zebib Sibhatleab የሰላማዊ ፓለቲካ ታጋይ ነው። በእኛ ዕድሜ ስለ ሰላማዊ ትግል፣ ስለ ዴሞክራሲ፣ ስለ ፌደራሊዝም፣ ስለ የህዝቦች መከባበርና ፍቅር የሚታገል የባይቶና ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ዘርፍ ሃላፊ በእስር ላይ ይገኛል። በእርግጥ የት ቦታ እንደታሰረ ማወቅ አልተቻለም። ፍርድቤት ስለ መቅረቡም አልተነገረም።
~~~~
Note: ስለ ሰላማዊ ትግል፣ ስለ ዴሞክራስያዊና ሰብአዊ መብት የተማራችሁ ሁሉ፤ በሰብአዊና ዴሞክራስያዊ መብቶች ዙርያ የምትሰሩ ሁሉ፣ በፓለቲካ ድርጅት ተደራጅታችሁ ሆነ ሳትደራጁ ስለ መብት ስለ ዴሞክራሲ፣ ስለ ሰላማዊ ትግል ጊዚያችሁ ጉልበታችሁ የምታበረክቱ ሁሉ... የሃይማኖት ሰዎችና አማኞች፣ የስነፅሑፍ ሰዎች፣ የሚድያ ሰዎችና ጋዜጠኞች ሁሉ ዛሬ ስለ አንድ ንፁህ ሰላማዊ የፓለቲካ ታጋይ ስለ ክብሮም ዘቢብ መታሰርን ጠይቁ ፃፉ። መንግስትን ጠይቁ፣ "ግፍን ፍራ ተው!" በሉ፤
ከሰሞኑ በሺዎች ተጋሩ የንግድ ቤታቸው ታሽጎባቸዋል፣ በሺዎች በመኪኖች እየተጫኑ ተወስዷል... ስለሁሉም justice እንጠይቅ...
የንግድቤት መዝጋት ጉዳቱ የነጋዴው ብቻ አይደለም፣ ሰራተኞቹም ስራ አጥ ይሆናሉ፣ በዙርያቸው ያለውም ሁሉ ተጎጂ ነው፣ የአከራይ ገቢም እንዲሁ ይቀንሳል ወይም ይጠፋል፣ ሌላ ጭቅጭቅ ይፈጠራል፣ የመንግስት የግብር ገቢውም ይወርዳል፣ ለተጨማሪ የቢሮክራሲ ጉዳዮችም ይዳረጋል፣ የኑሮ ውድነቱም ከመሻሻል ይልቅ ይባባሳል ጉዳቱም ለሁሉም ዜጋ ይሆናል፣
ባጭሩ ጉዳቱ አንድ ቦታ ላይ የሚቆም ጉዳት አይደለም... ልባም መንግስት:- ስራ ፈጣሪ ነጋዴዎችን እያበረታታ፣ ስራ ዕድል እየፈጠረ ዳጎስ ያለ ግብር ይሰበስባል እንጂ በአንድ ሳምት ውስጥ ባልተጠና መንገድ፣ የችኮላ ውሳኔ በመወሰን ዜጋውና ሃገሩ ለተደራራቢ ጉዳት አይዳርግም። ፍራቻና ጥርጣሬ ካለም'ኮ በማህበር እያደራጁ ማሰራትና መከታተል ይቻላል። እና ይታሰብበት።
Anyways, ለአንባብያኖቼ የምለው: ያለው መካረሩ፣ መጠላላቱ፣ ጣት መቀሳሰሩ ወዴት እንዳደረሰን አይተናል... ከዚህ በላይ እንዲቀጥል አናድርግ፣ I know ከብዙ መከራና ስቃይ በኃላ "ቆም ማለታችን አይቀርም!" ዛሬ "ቆም" ብንል ግን ቀጣዩ ሊደርስ ያሰበውን ጥፋት ማዳን እንችላለን ነው፣ ነው።
እናንተ ስለ ንፁሃንና ስለ ሰላማዉያን ተጋሩ ፍትህ ስትጠይቁ ሌላውም በየቤቱ ስላለው አጥፊ መጠየቅ እንጀምራል፣ ሆኖም ግን በቀጥታ በማጥቃትም ይሁን በዝምታ የዚህ ግፍ ተባባሪ ስትሆኑ ነገሩ ይከራል፣ የከረረም ይበጠሳል እንጂ ሊድን አይችልም... አፍንጫ ሲመታ ዓይን ያለቅሳ፣ ዳሩ ሲረበሽ መሃሉ ዳር ይሆናል፣ ሰው ሰውን የሚረዳው አንድም አዝኖለት ነው ሌላም ግን ነግ በኔ እያለ ነውና እንተባበር... መተባበርን ከዚሁ እንጀምር፣ አዳዲስ መሪዎች እንፍጠር☝
ፍትህ በግፍ ታስረው ላሉ ሁሉም ዜጎችና ንግድ ቤቶች፤ ፍትህ ለውድ ወንድማችን ክብሩ
ሠላም
https://www.facebook.com/thomas.hailu.5 ... 5411330870