Page 1 of 1

ባቡር መንገድ (ቸርችል ጎዳና) ዛሬ ምን ይመስላል?

Posted: 16 Jul 2021, 01:51
by Horus
ትዝታችን በኢ ቢ ኤስ የቸርችል ጎጋና መጀመሪያ ስም መርምሮ አልደረሰበትም ። ታሪኩ እንዲህ ነው ። አዲስ አበባ ጫካና ጭቃ መንገድ በነበረት የዛሬ 110 አመት የዛሬው እንደ መርካቶ ያለው የገበያ ቦታና የመንግስት መስሪያ ቤቶች ሁሉ ዛሬ ጊዮርጊስ ያለበት የምኒልክ አደባባይ ነበር ። ያ ነው አራዳ የሚባለው።

ካዲስ አበባ እስከ ጂቡቲ የተዘረጋው የባቡር መንገድ የሚነሳው በላጋር ጉምሩክ ወይም ለግሃር በሚባለው ባቡር ጣቢያ ነበር ።

እናም ከአራዳ (ጊዮርጊስ) እስከ ለግሃር ባቡር ጣቢያ በጫካው ውስጥ የሚሄ ቀጭን የግር መንገድ ነበር ። ያም ባቡር መንገድ ይባል ነበር ። ከዚያም ተነስቶ ነው በተልምዶ አውራ ጎዳና ስንል ባቡር መንገድ የምንለው ።

ያን የድሮ ባቡር መንገድ ነው ዛሬ ቸርችል ጎዳና የሚባለው ። ጣሊያን ሲወጣ በእንግሊዙ የሁለተኛ አለም ጦርነት አሸናፊ በሆነው ዊንስተን ቸርችል ስም የተሰየመው ።

ወደፊት ግን ተመልሶ ባቡር መንገድ መባል አለበት እላለሁ !!



Re: ባቡር መንገድ (ቸርችል ጎዳና) ዛሬ ምን ይመስላል?

Posted: 16 Jul 2021, 02:44
by Horus