Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"የጅቡቲን መስመር ትጠብቃላችሁ ተብለን መጥተን፤ አሁን ለምንድነው ከትግራይ ጋር እንድንዋጋ ወደ ጦርነት ቀጠና የምታስገቡን" የኦሮሚያና ሌሎች ዘማቾች

Post by sarcasm » 15 Jul 2021, 14:48

ሰበር ዜና ከጎሊና

የኦሮሚያና ሌሎች ዘማቾች ጎሊና በተሰፕች በዓፋር የዞን 4 ቀበሌ ላይ ሲደርሱ፤ "መከላከያ ወደ ትግራይ ስለሚዘምት፤ የጅቡቲን መስመር ትጠብቃላችሁ ተብለን መጥተን፤ አሁን ለምንድነው ከትግራይ ጋር እንድንዋጋ ወደ ጦርነት ቀጠና የምታስገቡን" የሚል ጥያቄ አንስተው፤ ከመሪዎቻቸው ጋር ተፋጠው እዚያው አድረዋል!

ክላሽንና ብሬን መትረየስ የታጠቀው ይህ "ዘማች ጦር" በትግራይ ላይ ለመዝመት በጎሊና በኩል ቆርጦ በዘቡል ወደ ያሎ ትግራይ እንዲገባ የውጊያ ቀጠና እንደተሰጠው ነው፤ ይህ እምቢተኝነትና ረብሻ የተነሳው፤ ይላሉ ምንጮቻችን::

እኔ አገር ቤት የማውቀው ሰው በደቦ በአዋጅ ተጠራርቶ ተሰባስቦ ይሄድ የነበረው ለእርሻና ሰብል ለመሰብሰብ ነበር! ዘንድሮ ግን የጣልያን ወረራ ዘመን አስመስለውት፤ ህዝቡን እያሞኙት፤ እነ እንትና በዘቡል እነ እገሌ በላሊበላ እለፉ እየተባባሉ፤ የወታደራዊ ፕላናቸውን በአዋጅ እያስነገሩ፤ የገበሬውን ልጅ አታለው ሊማግዱት ነው!
የጎሊና ዘማች ሁኔታ በእንደዚህ ሁኔታ ውጥረት ውስጥ እንደገባ፤ ኣማራውን ዘማች ቀላቅለው ነገሩን ለማብረድ በሚል፤ በቆቦ ወልድያ መስመር በሽብር ውስጥ ሲናጥና ሲሸሽ የነበረውን የአማራ ዘማች በተገኘው ተሽከርካሪ እየጫኑ ወደ ጭፍራ በማጓጓዝ ላይ ይገኛሉ::

መደበኛና እስከ አፍንጫው የተደራጀና የታጠቀ የመንግስታት የመከላከያ ሰራዊት አሰልፈው ያልቻሉትን በአሳፋሪ ሽንፈት ከትግራይ የተባረሩበትን ጦርነት፤ ለእርስት አስመላሾችና የስልጣን ጥመኞች ሲባል፤ የብሄር ብሄረሰቦችን ልጆች በእንደዚህ መልኩ ወደ እሳት እያስገቧቸው ነው::

https://www.facebook.com/kassa.hailemar ... 8360423773