Page 1 of 1

Tigray President Dr. Debretsion Gebremichael's Message to Ethiopian People - in Amharic

Posted: 15 Jul 2021, 10:11
by sarcasm

Re: Tigray President Dr. Debretsion Gebremichael's Message to Ethiopian People - in Amharic

Posted: 15 Jul 2021, 11:28
by euroland
:lol: :lol: :lol:

Edu junta
Don’t that remind you of Sadam Hussein’s 11th hours speech to American people ? :lol: During his speech Sadam was pleading for forgiveness while also threatening the total decimation of the “invaders”. What an irony. This tells me what Detsi’s final outcome will be very soon.
sarcasm wrote:
15 Jul 2021, 10:11

Re: Tigray President Dr. Debretsion Gebremichael's Message to Ethiopian People - in Amharic

Posted: 15 Jul 2021, 14:24
by sarcasm
የትግራይ መንግሥት ፕረዚዳንት ታጋይ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ለኢትዮጵያ ህዝብ ያስተላለፉት መልእክት
================================================================================================
የተከበራቹህ የኢትዮጵያ ህዝቦች፤ የትግራይ ህዝብ በመከላከያ ሰራዊት፣ በኤርትራ ጦር፣ በአማራ ክልል ልዩ ሃይል እና ሚልሻ እንዲሁም በሌሎች የውጭ ሃይሎች ከፍተኛ በደል እና ግፍ ሲፈፀምበት ከዛም አልፎ የትግራይን ህዝብ እንደ ህዝብ ለማጥፋት ጥይት፣ ረሃብ፣ አሰቃቂ ጾታዊ ጥቃት እና ንብረት ማራቆትን ያቀናጀ የጥፋት ፓኬጅ ለስምንት ወራት ሲፈጸምበት ቆይቷል።

ይሁን እንጂ የትግራይ ህዝብ በተፈጸሙበት ግፎች አንገቱን ደፍቶ እና ሞራሉ ተሰብሮ ፈርቶ የሚገዛ ሳይሆን በደሎቹ ለበለጠ ትግል አነሳስቶት የትግራይ ህዝብ የትም ይኑር እንደ አንድ ሰው በከፍተኛ ቁርጠኝነት ጠላቶቹን ታግሎና መስዋእትነት ከፍሎ መብቶቹን በእጁ ማስገባት ጀምሯል። በቀጣይም የተቀሩት መንቶቹ ሳይሸራረፉ ሙሉ በሙሉ በእጁ ለማስገባት ትግሉን ይቀጥላል።

ባለፉት ስምንት ወራት ከተፈጸሙት አንዱ ህገመንግሥትን በመርገጥ የትግራይ መንግሥት የሚያስተዳድራቸውን ቦታዎች በእብሪትና በሃይ የተቆጣጠሩትን ወንጀለኞች እከባቢውን ለቃቹህ ወደመጣችሁበት ያለማንገራገር ተመለሱ ቢባሉም በጉልበታቸው በመተማመን አንለቅም ብለው ለከፍተኛ ጥፋት ሲዘጋጁ ከርመዋል። አሁንም በተደጋጋሚ በጉልበት የያዛችሁት ቦታ በቶሎ ለቃቹህ ውጡ እንላለን። ካልሆነ ባለፈው ስምንት ወራቶች እንዳደረግነው ሁሉ አሁንም መብታችንን ታግለን እናስከብራለን።
የትግራይ ህዝብ ህዝብን እንደ ህዝብ ጠላት አድርጎ ፈርጆ አያውቅም። የትግራይ ህዝብ ትላንት የአማራ ጠላት አልነበረም ዛሬም የአማራ ጠላት አይደለም ነገም የአማራ ህዝብ ጠላት አይሆንም። ይሁን እንጂ በስልጣን ላይ ያሉት ስልጣናቸውን ላለመልቀቅ የሙጥኝ ብለው ይዘው የአማራን ህዝብ ወደ ከፍተኛ አደጋ እና ጥፋት እያስገቡት ይገኛሉ። ህዝቡም ለስልጣን ጥመኞች እና ተስፈኞች ተብሎ የሚከፈል ሂወት መኖር የለበትም ብሎ መቃወምና መታገል አለበት።

ሌሎች ኢትዮጵያውያንም በትግራይ ላይ እየተካሄደ ባለው ጦርነት የተፈጸሙ ግፎች እና በደሎች ተጠያቂዎች ወደ ፍርድ ይቅረቡ በማለት የድርሻቹህን ተጫወቱ እንጂ፤ የውጭ ወራሪን ሃይል ጋብዞ ማሸነፍ ያልቻለውን የትግራይ ህዝብ ትግል በተጨማሪ ዝግጅቶች ለዳግም ጥፋት እና እልቂት አንተባበርም ይበቃል አንሰለፍም ብላቹህ ለራሳቹህ እና ለታሪካቹህ የሚበጅ ትግል ብታካሂዱ ይሻላል የሚል መልእክት አለን።

አመሰኛለሁ።