እነ አብይ አሕመድ ደመቀ መኮንን እና ተመስገን ጥሩነህን የመሳሰሉ የጦር ወንጀለኞች፤ በልጆችህ ደም እየነገዱና እየቀለዱ ነው!
ከኦሮሚያ ከደቡብ ወሎና ከሌሎች የተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በኣውቶቡስ እያሳፈሩ ወደ ደቡብ ትግራይ እያጋዙት ያለው ወገንህ፤ ወደ ሰርግ ወይ ሰብል ለመሰብሰብ አይደለም እየሄደ ያለዉ! ለጥቂት ስግብግቦች የርስት ፍለጋ በእሳት ውስጥ ሊማግዱት እንጂ!
የትግራይ መከላከያ ሰራዊት የሕዝቦች ዕልቂት ስለሚያሳስበው፤ በተቻለው የውግያ ስልት ሁሉ የሟቾችን ቁጥር ለመቀነስ ብርቱ ጥንቃቄ በማድረግ እንዲማረኩ ወይም እንዲፈርሱና እንዲሸሹ እያደረገ ነው:: ከሰሞኑ የደቡብ ትግራይ ውግያም ይህ የጦርነት መርሕ ተግባራዊ በመሆኑ ነው፤ በርካቶች ሊማረኩና በርካቶችም ሊሸሹ የተቻለው:: ይህም ሆኖ ግን በርካቶች በማይመለከታቸው ውግያ በጥቂቶችና ስለጥቂቶች ፍላጎት እርካታ ሲሉ የህይወት ዋጋ ከፍለዋል::
ስለዚህ አሁንም መታወቅና ሊሰመርበት የሚገባው መሰረታዊ ጉዳይ፤ የሰለጠነና እስከአፍንጫው በዘመናዊ ትጥቅ፤ በከባድ የጦር መሳሪያዎች የውግያ አውሮፕላኖችና ድሮኖች የወረረውን፤ ግዙፍ የበርካታ መንግስታት ሰራዊት የሰባበረውን የትግራይ መከላከያ ሓይል፤ በዘማች ታጣቂ ለመዋጋት ማሰብ፤ በሚንቀለቀል የእሳት ነበልባል ውስጥ እራቁትን የመግባት ያህል ነው!
በመሆኑም ኢትዮጵያውያን ሆይ፤ የዘማች ወገኖቻችሁን ህይወት ከወዲሁ አድኑ! እነባጫና መሰሎቹ ሆድአደር ተላላኪዎች፤ እውነታውን ሸፍነው የሚዘባርቁትና የሚቀልዱት በሕዝቦች ልጆች ደም ነው! ለዚህ የጦር ወንጀላቸውም ተጠያቂ የሚሆኑበት ወቅት ሩቅ አይሆንም::
Please wait, video is loading...