Page 1 of 1

Ethiopian real terms annual budget for EC 2014 fell by by 6% from USD $13.7 to $12.9 billion (Deutsche Welle)

Posted: 14 Jul 2021, 18:46
by sarcasm
Ethiopian Economy Under Stewardship of PM Abiy's Government

የዋጋ ግሽበት የተጫነው የኢትዮጵያ በጀት

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በመጨረሻ ስብሰባቸው ለ2014 ዓ.ም. ያጸደቁት በጀት ካለፈው አመት ጋር ሲወዳደር በብር 18 በመቶ ቢጨምርም በዶላር ግን ቀንሷል። ያለፈው አመት የኢትዮጵያ መንግሥት በጀት በብር 476 ቢሊዮን፤ በዶላር ደግሞ 13.7 ቢሊዮን ገደማ ነበርየዘንድሮው በብር ወደ 561.7 ከፍ ቢልም በዶላር 12.9 ቢሊዮን ሆኗል

በማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ መረጃ መሠረት የዋጋ ግሽበት በሰኔ ወር ወደ 24.5 በመቶ ከፍ ብሏል። የምግብ ነክ ሸቀጦች ዋጋ ከ23.7 በመቶ ወደ 28.7 በመቶ ሲያድግ ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች ከ14.8 በመቶ ወደ 19 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።
....
ረዘም ያለ ጊዜ ወስደው ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ "በኤኮኖሚው ያመጣናቸውን ለውጦች ልናመጣ ያልቻልንበት አንዱ ዘርፍ ግሽበት ነው" በማለት መንግሥታቸው በእርግጥም በመቆጣጠር ረገድ እንዳልተሳካለት ለምክር ቤቱ አባላት ተናግረዋል። ጠቅላይ ምኒስትሩ በማብራሪያቸው ላለፉት አመታት ሲንከባለል የቆየ የዋጋ ግሽበት፣ በዓለም አቀፍ ገበያ ነዳጅ እና ማዳበሪያን በመሳሰሉ ሸቀጦች ላይ የታየ የዋጋ ጭማሪ አስተዋፅዖ ማበርከታቸውን ጠቅሰው "እሱ ላይ እንዳናተኩር ደግሞ ግራ እና ቀኝ የያዙን በጣም በርካታ ጉዳዮች አሉ። በእነዚህ ምክንያቶች የዋጋ ግሽበቱ በሚፈለገው ልክ አልተስተካከለም" ብለዋል።

ዐቢይ "በሚቀጥለው አመት ዋና ዋና ሸቀጦችን ገዝተን ግሽበት እንዳያመጣ ብናደርግ የኑሮ ውድነትን አይቀርፈውም፤ በአንድ አመት በምንሰራው ሥራ መቅረፍ አይቻልም" ሲሉ ተደምጠዋል። "ላለፉት አስራ ስድስት አመታት በየአመቱ ባለሁለት አሃዝ የዋጋ ግሽበት ነበር። ይኸ አንደኛው በሌላው ላይ እየተደመረ እየተደመረ የመጣ የዋጋ ግሽበት ሸማቾች እናንተ ባነሳችሁት ልክ ወይም ከዚያ በላይ ሸምተው ማደር በጣም ፈታኝ ሆኗል" ብለው በእርግጥም በኢትዮጵያ ዜጎች ላይ ያሳደረውን ጫና ገልጸውታል።

ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ የዋጋ ግሽበቱን መቀነስ ባይችልም መንግሥታቸው ጥረት ማድረጉን እንዳላቆመ ሥጋት ለበረታባቸው የምክር ቤቱ አባላት አስረድተዋል። ለዚህም ባለፉት ሶስት አመታት "ከውጭ በምንገዛው መጠን ከሸጥን የኑሮ ውድነት ያባብሳል" በሚል አመክንዮ መንግሥት ነዳጅ ከገዛበት ዋጋ በታች እየሸጠ 47 ቢሊዮን ብር መክሰሩን በማሳያነት ጠቅሰዋል። ውኃ እና የቤት ኪራይ የመሳሰሉ አገልግሎቶች ክፍያ እንዳይጨምር ሙከራ መደረጉን፣ በአዲስ አበባ የዳቦ ማምረቻ በማስገንባት ችግሩን ለመቅረፍ ጥረት መደረጉን ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ እየጠቀሱ መንግሥታቸው መፍትሔ ፍለጋ የሰራቸውን ዘርዝረዋል።

"እስካሁን መንግሥት አንደኛ ምግብ ነክ ምርቶች በርከት ብለው እንዲገቡ ጥረት አድርጓል። ብዙ ቢሊዮን ብር መድበን ለማስገባት ሞክረናል። ሁለተኛው ለሕብረት ሥራ ማህበራት ግማሽ ቢሊዮን ብር ገደማ ተጨማሪ ብድር እንዲያገኙ እና ሸቀጦች ማከፋፈል እንዲችሉ ለማድረግ ተሞክሯል። ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች የሚጠቀሙበት አንዱ ቦታ ስለሆነ። ሶስተኛ የአቅርቦት ሰንሰለቱ ሳንካ አስቸጋሪ በመሆኑ የገበያ ማዕከላት አዲስ አበባም በተለያየ ቦታ በስፋት ለመገንባት ጥረት ተደርጓል። አራተኛ የግሉ ዘርፍ በፍራንኮ ቫሉታ ተጨማሪ ታክስ ሳይከፍል ስንዴ፣ ስኳር፣ ዘይት፣ ሩዝ፣ የሕፃናት ዱቄት እንዲያስገባ ተፈቅዷል። በፍራንኮ ቫሉታ የፈቀድንው በቂ ስላልሆነ መንግሥት በተለይ ስንዴ፣ ዘይት እና ስኳር ተጨማሪ ሐብት መድቦ እያስገባ ይገኛል" ያሉት ዐቢይ የመንግሥት ሙከራዎች በተፈለገው መጠን ግሽበቱን ባይቀንሱም በተወሰነ ደረጃ ማገዛቸውን ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መንግሥት እንደሚለው ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይም "ሕገ-ወጥ" ያሏቸውን ነጋዴዎች ለግሽበቱ አስተዋጽዖ ማበርከታቸውን ጠቅሰው ተጠያቂ አድርገዋል። ዐቢይ መደብሮቻቸው "የታሸጉባቸው" ፈቃዶቻቸው "የተሰረዙባቸው" ግፋ ሲልም "በክስ ሒደት ላይ" የሚገኙ መኖራቸውን ጠቁመዋል።

በማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ መረጃ መሠረት የዋጋ ግሽበት በሰኔ ወር ወደ 24.5 በመቶ ከፍ ብሏል። የምግብ ነክ ሸቀጦች ዋጋ ከ23.7 በመቶ ወደ 28.7 በመቶ ሲያድግ ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች ከ14.8 በመቶ ወደ 19 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።


Read the whole article https://www.dw.com/am/%E1%8B%A8%E1%8B%8 ... a-58190921