Page 1 of 1

የአማራ ጦርና የኢትዮጵያ ሰራዊት በአንድ እዝና በአንድ ፕላን ስር መጓዝ አለባቸው!

Posted: 13 Jul 2021, 12:37
by Horus
ጦርነቱ ተጀመረ እንጂ ማለቂያው አይደለም ። ትግሬ ገና ለዘመናት ካማራ ጋር መዋጋት ይኖርበታል፣ ያ ደሞ የማይቻል ነው ። ኮረምን ላንድ ቀን መያዝ ሃላፊ ጊዜያዊ ነገር ነው። መፍትሄ ወታደራዊ ብቻ አይሆን ፖለቲካዊ ነው ።

ትግሬ እንደ ማህበረ ሰብ እየፈረሰ ነው ። ይህ ሁሉ የምናየው የህጻናት ጦር ምልመላ፣ የልጃገረዶች ምልመላና መድፈር፣ እርስ በርስ መጋደል፣ ድርቀት፣ አምበጣ፣ ውድመት፣ ወድመት ገና መጀመሩ እንጂ ማብቃቱ አይደለም ። ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው ባንዳ ትህነግ ን የወለደው ፣ ያሳደገው አሜርካ ነው።

አዳሜ ያሻውን ሊዋሽ ሊሰብክ ይችላል! ትግሬ ግን በደምብ እየፈረሰች ነው ።

Re: የአማራ ጦርና የኢትዮጵያ ሰራዊት በአንድ እዝና በአንድ ፕላን ስር መጓዝ አለባቸው!

Posted: 13 Jul 2021, 12:44
by Wedi
ጅል!! በምንም ታምር አንድ አይሆኑም!! አብይ አህመድ የአማራ ህዝብ እያስተቃው ነው ያለው!! አብይ አይደለም እንዶዴ የአማራ ልዮ ሃይል ያሸነፈው በትዕዛ ወደ ኋላ እንዲመለስ እያደረገ ያለው??

Re: የአማራ ጦርና የኢትዮጵያ ሰራዊት በአንድ እዝና በአንድ ፕላን ስር መጓዝ አለባቸው!

Posted: 13 Jul 2021, 12:54
by Horus
በእኔ ግምት ያማራ ጦር ተመለስ የተባለው ጦርነቱ ድንበር እንዲኖረው ታስቦ ይመስለኛል። ስለዚህ ጥያቄው የአማራ መቆም ያለበት ድንበር የት እንደ ሆነ ያማራ ህዝባዊ ሰራዊት፣ ያማራ መንግስትና የፌዴራል ሰራዊት በአንድ ፕላን መናበብ አለባቸው ። ይህ ይመስለኛል ያለው ችግር! አብን ያመራር ክፍተት የሚለው ይህን ለማሳየት መሰለኝ ። ዞሮ ዞሮ ጦርነቱ መጀመሩ እንጂ ማብቃቱ አይደለም ።

Re: የአማራ ጦርና የኢትዮጵያ ሰራዊት በአንድ እዝና በአንድ ፕላን ስር መጓዝ አለባቸው!

Posted: 13 Jul 2021, 13:04
by Abere
Horus,

It is naïve to hold a risky share of stock for long. Backing Abiy Ahmed and his Orommuma stuffed EDF is a heavy loss. It is high time to dump Abiy Ahmed and chase out his fake EDF from Amhara territories. The cost-benefit analysis is not justifying supporting ODP-OLF EDF. አማራ ሚሊሻ እኮ ጥይት ከመከላከያ ገዝቶ ነው እራሱን የሚጠብቀው። I think EDF is already an expired entity and has already disgraced itself in the face of 50 million Amhara and other true Ethiopians. This EDF has been harassing and killing Amhara before November 2020 for 30 years while it was babysitting the Tigre-woyane in Tigray by harassing Eritreans. So, Amhara does not have any business left with OLF/EDF.

Re: የአማራ ጦርና የኢትዮጵያ ሰራዊት በአንድ እዝና በአንድ ፕላን ስር መጓዝ አለባቸው!

Posted: 13 Jul 2021, 13:13
by Horus
አበረ
ቁጭትህ ይገባኛል! ግን ያንተ አማራጭኮ የነበረ ነው፣ ዘመነ መሳፍንት ማለት በትክክል ያለው ነው ፤ ማዕከላዊ መንግስት ደክሞ ትግሬ የራሱ ጦር፣ አማራ የራሱ ጦር፣ ኦሮሞ የራሱ ጦር፣ ሱማሌ እያልን ወደ ቅድመ ቴዎድሮስ ዘመን እንሄለን ያለ ምንም ጥርጥር ። ከዚያ በኋላ አንድ ኢትዮጵያ ማለት ተረት ይሆናል። ያ ደሞ የነአሜሪካና አውሮፓና አረብ ዘላለማዊ ምኞት ነው። ምርጫው የእኛ ነው ! ሰላም

Re: የአማራ ጦርና የኢትዮጵያ ሰራዊት በአንድ እዝና በአንድ ፕላን ስር መጓዝ አለባቸው!

Posted: 13 Jul 2021, 13:24
by Lakeshore
ኣንተ ብዳታም ሆሩስ የሚሉህ ይሽማግሌ ቅለታም ባማን ኪሳራ ነው ሰላም ሰላም የመትለው። ምድረ ጋላ በህዝብ በጀት ያጋላ ወራሪ ሲያድረጅ አኛ ኣገር ሲመዘበር ኣማራ በቻ ኣገር የሚዋጋበት ጉዳይ ምንድን ነው። ከንግዲህ ዯብይ ጋላ ጦር በውያኔ አንድዛ ተግርፎ የፈረጠጠ ያምራ ጀግና ቢገጥመው ሸ ሽቶ ወደ ሱዳን አንደ ሚገባ ምንም ጥርጥር የለውም። ኣሁን ችግረ ይሆኑብን ኣማራነን በላው ከጋላው ጋር በማበር ኣምራን ያሚያስመቱት ናቸው። ኣምራ ክልል ወስጥ ያሉትን ኣመራሮች ኣግቶ መያዝ አና ስልጣናቸውን አንደኢ ለቁ ማስገደድ ያስፈልጋል።

የሄ ሆረስ የሚሉትን መጋዣ ኪኒኑን ሲውጥ ደህና የሚሆንን አና ሳይውጥ ደግሞ የወንድ ኣዳሪ ችላማለት ነው።

Re: የአማራ ጦርና የኢትዮጵያ ሰራዊት በአንድ እዝና በአንድ ፕላን ስር መጓዝ አለባቸው!

Posted: 13 Jul 2021, 13:31
by Abere
ሆረስ
በእውነት እኮ አሁን ማዕከላዊ መንግሥት አለ ለማለት አይቻልም። በዘመነ መሳፍንት እንኳን አብሮ የተሰዋለትን ህዝብ አሳልፎ ለጥላት ሰጥቶ አይሄድም። ያን ከሚያደረግ ሽጉጡን ጠጥቶ ይሞታል። በመቀሌ ምንም ሳይሰሙ ጥሏቸ የወጡት ወታደሮች፣ የኮሌጅ ተማሪዎች ተመልከት። ኣአሁን ደግሞ ለግድያ ከድቶ ጥሏቸው የወጣውን የራያን ህዝብ ተመልክት። ህግ አስከብራለሁ ይልሃል ህግ እና ሞራል ግን አያውቅም። የኢትዮዽያ ህዝብ ጥሎት የሚሼሽ ወይም የሚዋሽ መሪ አይወድም። በታሪክ ዐፄ ኃይለሥላሤ ከማይጨው ሸሽተው በመቅደላ በኩል ሊያመልጡ ሲሉ የተንታ/ መቅደላ ስዎች አጫዋች መስኖ ከሚባል ቦታ ላይ እኛን አጋፍጠህ የትነው የምትፈረጥጠው ብለው ጦርነት ተኩስ ገጠሙ ። ንጉሡም በጭንቅ በመከራ ሰው ደብቆ ኣስመለጣቸው::

ወንድ ልጅ ሴት ልጅ - በወለደበት፣
ተፈሪ መቅደላን ተጨንቆ አለፋት።

ይባላል በዚያ ቁጭት ጭምር ሳይሆን አይቀርም ልጅ እያሱን ጉድጓድ ውስጥ ኣአስረው ገድለውት የጠፉት። Sometimes the solution could be outside of the common belief. As you may know EDF is a terminally-ill institution with the OLF disease. It is not worth funding and supporting. I hate to support a losing team in soccer match and especially if one or two of its players are bribed by the opposite team and always touch the soccer ball in the penalty area. Orommuma EDF is touching mano internationally and the coach Abiy Ahmed is the one telling to do that exactly. Patterns don't lie, if one wrangles them correctly.

Re: የአማራ ጦርና የኢትዮጵያ ሰራዊት በአንድ እዝና በአንድ ፕላን ስር መጓዝ አለባቸው!

Posted: 13 Jul 2021, 14:18
by Horus
አበረ
የዛሬን አላውቅም እንጂ እኔና አንተን እስከ ዛሬ የምንስማማበት አንድ እጅግ መሰረታዊ ነገር አለ ፤ እሱም የኢትዮጵያ ችግር ሁሉ፣ የሁሉም ጎሳዎች ችግር ሁሉ ምንጩ፣ ገፊ ምክኛቱ የጎሳ ስርዓት ነው ። ይህ ሁሉ የምታየው መታመስ እና ሰቆቃ የዘር ፖለቲካ ዉጤት ነው ። እናም ነገሩ ገና እየባሰ እንጂ እያነሰ አይሄድም በዚያ ሰርዓት ላይ አገር አቀፍ ቅዋሜ አንስተን እስካላፈርሰው ደረስ ።

የትግሬ ጦርነት የተበላሸው ዛሬ አይደለም፤ በኖቬምበር 30 2020 ነው ። እንዴት በለኝ ። ትግሬ በመደበኛ ጦርነት እንደ ማያሸንፍ አውቆ ሃይሉን ሁሉ ይዞ ወደ በረሃ አፈገፈገ ። ከዚያም በኋላ ያሉትን በመቶች ሺ የሚቆጠር ሰው በመደበኛ ጦር አደረጃጀት ሳይሆን በትናንሽ የጎሬላ ውጊያ አደረጃጀት አዋቅሮ በመላ ትግሬ ተራሮችና ሸለቆች በተነ ።

የኢትዮጵያ ሰራዊት መደበኛ ጦርነቱን ልክ እንዳሸነፈ ለቆ ወጥቶ አሁን ያለበት ያማራ ድምበር ላይ ሰፍሮ የተወነ ሃይሉን ለጎሬላ ዉጊያ ማደራጀት ሲገባው ትግሬ ውስጥ ለ7 ስምንት ወራት በጎሬላ ጋንታዎችና በህዝብ ሲወጋ ከርሞ ደክሞ ወጣ ። ስለዚህ ካንተ ጋር የምስማማው በኢትዮጵያ ጄኔራሎች ስህተት ላይ ነው።

ዛሬ ወደድንም ጠላንም ያለን ያ ጦር ነው ። በንዴት ተነስተን ባንድ ቀን የምንፈታው ነገር አይደለም ። ልብ በል ፣ በጎሳ ሲስተም ዉስጥ ሰራዊቱ በቀላሉ በጎሳ ተከፋፍሎ እንደ ጨው ሊቀልጥ ይችላል ። ችግራችን ጎሳ ነውና ። ባማራ በኩል ስላለው ፣ የዛሬን ሁኒታ ነው እንጂ ምንም የተለወጠ ነገር የለም ። በእኔ እምነት ቢበዛ ቢበዛ በወልቃይትና ራያ ህዝቡ በድምጽ የወስን ወደ ሚል መፍትሄ ነው የሚኬደው ። ጦርነቱም ከቀጠለ አማራ መደራጃ ግዜ እንጂ የሰውና የቁሳቁስ እጥረት የለውም ። ሄዶ ሄዶ ችግሩ ትግሬ ላይ ነው የሚያርፈው ። ዛሬም ቢሆን ህጻናትና ልላገረዶችን ጦር ሜዳ ሚልኩት የሰው እጥረት ስላላቸው ነው። ከ18 እስከ 25 እድሜ ያሉት ትግሬዎች ጥቂት ናቸው ።

Re: የአማራ ጦርና የኢትዮጵያ ሰራዊት በአንድ እዝና በአንድ ፕላን ስር መጓዝ አለባቸው!

Posted: 13 Jul 2021, 14:33
by Abe Abraham
Horus wrote:
13 Jul 2021, 14:18

ዛሬ ወደድንም ጠላንም ያለን ያ ጦር ነው ። በንዴት ተነስተን ባንድ ቀን የምንፈታው ነገር አይደለም ። ልብ በል ፣ በጎሳ ሲስተም ዉስጥ ሰራዊቱ በቀላሉ በጎሳ ተከፋፍሎ እንደ ጨው ሊቀልጥ ይችላል ። ችግራችን ጎሳ ነውና ። ባማራ በኩል ስላለው ፣ የዛሬን ሁኒታ ነው እንጂ ምንም የተለወጠ ነገር የለም ። በእኔ እምነት ቢበዛ ቢበዛ በወልቃይትና ራያ ህዝቡ (???????) በድምጽ የወስን ወደ ሚል መፍትሄ ነው የሚኬደው

ጦርነቱም ከቀጠለ አማራ መደራጃ ግዜ እንጂ የሰውና የቁሳቁስ እጥረት የለውም ። ሄዶ ሄዶ ችግሩ ትግሬ ላይ ነው የሚያርፈው ። ዛሬም ቢሆን ህጻናትና ልላገረዶችን ጦር ሜዳ ሚልኩት የሰው እጥረት ስላላቸው ነው። ከ18 እስከ 25 እድሜ ያሉት ትግሬዎች ጥቂት ናቸው ።
You are not paying attention to the external factor - American involvement. The Amhara people have a big problem in getting enough supply of weapons and they are denied the right to defend themselves.

Re: የአማራ ጦርና የኢትዮጵያ ሰራዊት በአንድ እዝና በአንድ ፕላን ስር መጓዝ አለባቸው!

Posted: 13 Jul 2021, 14:56
by Horus
አቤ
አሜሪካ እና እንግሊዝ ባማራ ላይ የተነሱት ዛሬ አይደለም ። ሃይለ ስላሴን የጣሉት እነሱ ናቸው ። እነመልስ አዲስ አበባ የገቡ እለት ናሽናል ኢንተስት የሚባለው የዋዝንግተን መጋዚን አማራ የትግሬን ህዝብ ማጥፋት ይፈልጋል ብሎ ጽፎ ነበር። ዛሬም የተለውጠ ነገር የለም። ያሜርካ አቋም አንድ ነው ። ጥያቄው አሁን ምን እናድርግ ነው ።

በእርስ በርስ ጦርነት ደህንነቱ የሚጠበቅ ጎሳ የለም ። አማራ ጸረ ጎሳ የሆነውን ህዝብ ሁሉ በማስተባበር ከሰሜን ደቡብ ድረስ፣ ኢትዮያዊ ማዕከላዊ መንግስት በማጠናከር የትግሬና ሌላም ተገንጣይ ሃይል አብረን መቋቋም እንጂ ራሳቸው እነኮሀን በሰሩልን እገመንግስት ከተበታተን እንኳስ እድገት ሰላም እንኳ አይኖረንም ።

ይህን ማለት ግን ዛሬ አማራ ራሱን አይከላከለ ማለት አይደለም ። አማራም ቢሆን ልዩ ሃይሉን ወደ ትግሬ ዘልቆ በመግባት የትግሬ የረግረግ ፖለቲካና ቀውስ ውስጥ መዘፈቅ አይኖርበትም ፣ የትግሬን ችግር ለነሱ መልሶ ሰጥቶ ድንበሩን ቆልፎ ሁሉንም ማየት ነው ። ይህ እኔ በግሌ ሚታየኝ ስዕል ነው

Re: የአማራ ጦርና የኢትዮጵያ ሰራዊት በአንድ እዝና በአንድ ፕላን ስር መጓዝ አለባቸው!

Posted: 13 Jul 2021, 15:18
by Abe Abraham
Horus wrote:
13 Jul 2021, 14:56

I always respect your judgement and your look at developments. I am not calling for Amhara forces to enter Tigray proper and fight rather the Amhara forces should be given the right weapons to defend themselves in the areas that they control and the periphery of Tigray proper because the government has declared a ceasefire from its side. Therefore either the government protects the Amhara or the Amhara should be given enough support to de the work by themselves.

Re: የአማራ ጦርና የኢትዮጵያ ሰራዊት በአንድ እዝና በአንድ ፕላን ስር መጓዝ አለባቸው!

Posted: 13 Jul 2021, 15:34
by Abere
ሆረስ፤

ስለ ኢትዮዽያ አንድነት እና ፀረ-ጎሳ አቋም የተለየ ነገር የለኝም። ግን አሁን ያለው የጎሣ መከላከያ ሰራዊት መሆኑን ደግሞ በተደጋጋሚ ከመሬት ላይ እያየን ስለሆነ ተቃውሟችን ከዚህ በጎሳ ደዌ ብፅኑ ከታመመው መከላከያ መጀመር አለብን ባይ ነኝ። አማራ እራሱን የመከላከል እና የመጠበቅ ሙሉ ተፈጥሮአዊ መብት አለው። በመሰረቱ እኔ እንደ ኢትዮዽያ መከላከያ ሰራዊት ዓላማ ቢስ በፍጹም አይቸ አላውቅም ከባለፉት - 30 ዓመታት ወድህ። ህዝብ እና አገር ሳይሆን ባለሥልጣን የሚጠብቅ ወንጀለኛ ጄሌ ነው። ለምን የኢትዮዽያ ህዝብ ግብር ገንዝብ ደመወዝ እንደ ሚከፈልው ይገርመኛል። ለ Unite Nations የሚሼጥ mercenary ወታደር እንጅ ብሄራዊ ወታደር አይደለም። መፍረስ አለበት። አሁን በግልፅ የኦነግ መከላከያ ኃይል ነው ፡ የጦር ጠቅላይ አዛዡ የጎሳ የኦነግ ቅንደኛ ሰው ነው። እና ዐማራ በሬ ካራጁ በሆነ መንገድ እንደት ነው ሊኖር የሚችለው? ትልቁ ምሥል ከግድግዳው ላይ የሚታይ ይመስለኛል።

Horus wrote:
13 Jul 2021, 14:18
አበረ
የዛሬን አላውቅም እንጂ እኔና አንተን እስከ ዛሬ የምንስማማበት አንድ እጅግ መሰረታዊ ነገር አለ ፤ እሱም የኢትዮጵያ ችግር ሁሉ፣ የሁሉም ጎሳዎች ችግር ሁሉ ምንጩ፣ ገፊ ምክኛቱ የጎሳ ስርዓት ነው ። ይህ ሁሉ የምታየው መታመስ እና ሰቆቃ የዘር ፖለቲካ ዉጤት ነው ። እናም ነገሩ ገና እየባሰ እንጂ እያነሰ አይሄድም በዚያ ሰርዓት ላይ አገር አቀፍ ቅዋሜ አንስተን እስካላፈርሰው ደረስ ።

የትግሬ ጦርነት የተበላሸው ዛሬ አይደለም፤ በኖቬምበር 30 2020 ነው ። እንዴት በለኝ ። ትግሬ በመደበኛ ጦርነት እንደ ማያሸንፍ አውቆ ሃይሉን ሁሉ ይዞ ወደ በረሃ አፈገፈገ ። ከዚያም በኋላ ያሉትን በመቶች ሺ የሚቆጠር ሰው በመደበኛ ጦር አደረጃጀት ሳይሆን በትናንሽ የጎሬላ ውጊያ አደረጃጀት አዋቅሮ በመላ ትግሬ ተራሮችና ሸለቆች በተነ ።

የኢትዮጵያ ሰራዊት መደበኛ ጦርነቱን ልክ እንዳሸነፈ ለቆ ወጥቶ አሁን ያለበት ያማራ ድምበር ላይ ሰፍሮ የተወነ ሃይሉን ለጎሬላ ዉጊያ ማደራጀት ሲገባው ትግሬ ውስጥ ለ7 ስምንት ወራት በጎሬላ ጋንታዎችና በህዝብ ሲወጋ ከርሞ ደክሞ ወጣ ። ስለዚህ ካንተ ጋር የምስማማው በኢትዮጵያ ጄኔራሎች ስህተት ላይ ነው።

ዛሬ ወደድንም ጠላንም ያለን ያ ጦር ነው ። በንዴት ተነስተን ባንድ ቀን የምንፈታው ነገር አይደለም ። ልብ በል ፣ በጎሳ ሲስተም ዉስጥ ሰራዊቱ በቀላሉ በጎሳ ተከፋፍሎ እንደ ጨው ሊቀልጥ ይችላል ። ችግራችን ጎሳ ነውና ። ባማራ በኩል ስላለው ፣ የዛሬን ሁኒታ ነው እንጂ ምንም የተለወጠ ነገር የለም ። በእኔ እምነት ቢበዛ ቢበዛ በወልቃይትና ራያ ህዝቡ በድምጽ የወስን ወደ ሚል መፍትሄ ነው የሚኬደው ። ጦርነቱም ከቀጠለ አማራ መደራጃ ግዜ እንጂ የሰውና የቁሳቁስ እጥረት የለውም ። ሄዶ ሄዶ ችግሩ ትግሬ ላይ ነው የሚያርፈው ። ዛሬም ቢሆን ህጻናትና ልላገረዶችን ጦር ሜዳ ሚልኩት የሰው እጥረት ስላላቸው ነው። ከ18 እስከ 25 እድሜ ያሉት ትግሬዎች ጥቂት ናቸው ።

Re: የአማራ ጦርና የኢትዮጵያ ሰራዊት በአንድ እዝና በአንድ ፕላን ስር መጓዝ አለባቸው!

Posted: 13 Jul 2021, 17:04
by Horus
እኔ ልሳሳት እንችላለሁ፣ ግን አሜሪካ የምስጢር ጦርነት በኢትዮጵያ ላይ እየወጋ ይመስለኛል ። በኢትዮጵያ የፕሮክሲ ጦረነት አቅዶ የትግሬ ባንዳ ሰራዊት በሁሉም መንገድ በመርዳት ጦር እየወጋን ይመስለኛል ። የኢትዮጵያና ሩሲያ ቅርበት ልክ የሱማሌ ጦርነት እየመሰለ ነው።

ሰዎች አይሆንምን ትተው ይሆናል ይዘው አሜሪካ በእውነት ምን እያደረገ ነው የሚለው መመርመር አለባቸው? ወያኔ የፕሮክሲ ፈረሰ ነው። በእርግጥ ትግሬ በአሜሪካ እየተረዳ ኢትዮጵያን በመውጋት ላይ ከሆነ ለዚያ የሚመጥን ወታደራዊና ፖለቲካዊ እስትራተጂ ማሰብ አለበት የኢትዮጵያ ልጅ ማለቴ ነው።

ስለዚህ በውስጥ የሚደረገው ሽኩቻና መወቃቀስ መቆም አለበት ።

ልብ በሉ ነገሮች ሁሉ የጦዙት የምርጫው ዉጤት ከታወቀ በኋላ ነው ። ይህ ሁሉ በፕላን የሚደረግ ነው የሚመስለው!

ስለዚህ ዉጊያችን ካሜሪካ ጋር ከሆነ የኢትዮጵያ ዝግጅት መሆን ያለበት በሌላ ደረጃ፣ በምኒሊክ አድዋ ሞዴል እንጂ ባካባቢ ሚሊሺያ በተበታተነ ሞዴል ትርፉ ሽንፈትና የባንዳዎች ወደ ስልጣን መመለስ ነው ።

በጦርና መንግስት አካባቢ ያሉት ሰዎች አንድ ጥልቅ ግንዛቤ ለህዝቡ ማስጨበጥ ግድ ይላቸዋል?

የምዕራብ ፕሮክሲ ጦርነት በኢትዮጵያ አለ ወይስ የለም? ግብጽ በጦር ኢትዮጵያን እወጋለሁ ብላለች፣ በአለም ፎረም ላይ! እንዴትና በምን ሞዴል ነው የምትወጋን? የግብጽ ፕሮክሲ ትግሬዎች ቢሆኑስ?

መልስ መኖር አለበት!