Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

ይድረስ ለአማራ በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ከካሳ ሃይለማርያም (Unofficial Tigray Defense Forces (TDF) Spokesman)

Post by sarcasm » 13 Jul 2021, 07:13

ይድረስ ለአማራ በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ ሕዝብ
ከካሳ ሃይለማርያም


በዛሬዋ ኢትዮጵያ ላይ ቆም ብለን፤ እንደ ግለሰብ ብቻ ሳይሆን እንደ ሕዝብ፤ በርካታ እጅግ በርካታ ትናንቶችን መለስ ብለን እያስተዋልን፤ ምነው እነዚህ ትናንቶች ባልነበሩ፤ እንደ ሕዝብና እንደ አገር ባላለፍንባቸው፤ እያልን የምናቀረቅርባቸው ትናንቶች አፍ ከገደፍ ሞልተው ፈሰዋል ጅረት ፈጥረዋል፡፡

ሆኖም ግን እንደ ሕዝብ ስለትናንቶች ከንቱነት የሚሰማው ፀፀት፤ ወይንም ተስፋ መቁረጥ አይደለም፡፡ የሚታየው ሰከን ረጋ ብሎ ዛሬን በትናንት ፀፀት ውስጥ ለማየትና፤ ነገን የሚቃኝ ተነሳሽነት አይደለም፡፡ ይልቁንስ ጎልቶ የሚታየውና የሚደመጠው፤ የሁኔታውን አሳሳቢነት ተገንዝቦ የነቃ አይደለም ደንግጦ የባነነ ሕዝብ እንኳን አለመኖሩ ነው፡፡ እንደ ሕዝብና እንደ አገር ተከባብረን በእኩልነት ላይ በተመሰረተ አንድነት ወደ ከፍታ እየወጣን ነው፤ ወይንስ በጥቂቶች ስለጥቂቶች መስተፃምራችን ተበጣጥሶ፤ አገራዊ አንድነታችን ውልቅልቁ ወጥቶ ተፈረካክሶ፤ ቁልቁል ወደ ዓዘቅት እየተምዘገዘግን ነው!?

አገሪቱ እና ሕዝቦቿ ያሉበትን እጅግ አጣብቂኝ እውነታ፤ የዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ በሚገባ የተገነዘበው ቢሆንም፤ ሕዝቦቿ ግን ሊባንኑ እንኳን አለመቻላቸው፤ በርካታዎቹን ዓለምአቀፍ ተንታኞች ያስገረመ ክስተት ሆኗል፡፡ በሌለ የውሸትና ቅጥፈት ፖለቲካ በመስከር፤ በጥቂቶችና ስለጥቂቶች ሁሉንም የአገሪቱን ሕዝቦችና እሴቶች በመያዣነት ቤዛ አድርጎ ማስረከብ፤ እውን የጤና ነውን ያሰኛል! ዓለም የሚያውቀውን ሐቅ በአደባባይ በሚዋሹና በሚክዱ፤ ዓቅምና ችሎታ በሌላቸው፤ የባዕዳን ጠላቶች ጥገኛ ባንዳ በሆኑ፤ የስልጣንና የጥቅም ጥመኞች፤ አማራውን ሆነ ሌላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በማይወክሉ ጥቂቶች፤ ሕዝብና አገር አደጋ ላይ ወድቋል፡፡

ባለፉት ስምንት የጨለማ ወራት፤ ጥቂቶች ስለስልጣንና የሃብት ጥማታቸው እርካታ ሲሉ፤ በቂም በቀል ሰክረው ከባዕዳን ሃይሎች ጋር በማበር፤ በአገራቸው ሕዝቦች ላይ እጅግ ዘግናኝ የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈፀምና እየፈፀሙ መሆናቸው፤ የአገርንና የሕዝብን ሃብት ማውደማቸውና በባዕዳዊ ወራሪ ሃይል እንዲዘረፍ ማድረጋቸው እንዳለ ሆኖ፤ በዓስር ሺዎች የአገሪቱ ገበሬና ወጣት የጦርነት እራት ሆኗል፡፡ በዚህም አገሪቱና ሕዝቦቿ በመጨረሻው የውድቀትና የመበታተን ኣፋፍ ላይ ተንጠላጥለዋል፡፡

በትግራይ ህዝብ ላይ እየተካሄደ ባለው በዚህ የዘር ማጥፋት ጦርነት መሳተፍ፤ ስለጥቂቶችና በጥቂቶች ተጎትቶ የጥይት ማብረጃ ከመሆንና፤ አገርን ከማፍረስ የዘለለ፤ ለአማራም ሆነ በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አንዳችም ዓላማ ሆነ ፋይዳ እንደሌለው፤ ማንም ልቦና ያለው ጤነኛ ሰው ሊገነዘበው የሚችል ሐቅ ነው፡፡

በደቡብ ትግራይ እየተካሄደ በዋለው ውጊያ በግልፅ እንደታየው፤ በአብዛኛው ከአማራ ክልል የዘመተው ወጣትና ጎልማሳ፤ ለምን ዓላማ እንየተዋጋ እንዳለ እንኳን በውል የሚያውቀው ነገር የለም፡፡ በብዙ ሺዎች የአማራ ገበሬና ወጣት፤ በዚህ የክረምት የእርሻ ወቅት ከእርሻውና ኑሮው ተፈናቅሎ፤ ለእነ አብይ አሕመድ፣ ደመቀ መኮንን፣ ተመስገን ጥሩነህ፣ አገኘሁ ተሻገርና መሰሎቻቸው መሰሪ ጥማትና ፍላጎት ማርኪያ፤ በማያውቀው የጦርነት እሳት ውስጥ እየተማገደ ይገኛል፡፡

ይህ በስሜት ቀስቅሰውና በጥላቻ አስክረው በጦርነት እሳት ውስጥ የማገዱት የአማራ ገበሬና ወጣት፤ በቂ ወታደራዊ ስልጠና አይደለም አስፈላጊውን ትጥቅና ዝግጅት እንኳን አላሟሉለትም፡፡ ኋላቀር ሲማኖቭ ጠበንጃ ሳይቀር የታጠቀ የገበሬ ጦር ነው፤ አብይና ኢሳያስ ለስምንት ወራት በበርካታ የመንግስታት መደበኛና ሜካናይዝድ ሰራዊትና ድሮኖች ተደግፈው፤ ሊያንበረክኩት ያልቻሉትን የትግራይ የመከላከያ ሰራዊት እንዲጋፈጥ የማገዱት፡፡

የሞተውን ያህል የአማራም ሆነ በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ወጣትና ገበሬ ቢሞትም ደንታ የሌላቸው እነዚህ ጥቂት ስግብግብ የስልጣን ጥመኞች፤ እንደ አንደኛው የዓለም ጦርነት የሰው ማዕበል (Human wave) የመፍጠር ኋላቀር የውጊያ ስልት በመጠቀም ነው፤ የአማራን ገበሬና ወጣት ሲማግዱት የዋሉት፡፡ ለዚህም እንዲያመቻቸው፤ በመደበኛ የወታደራዊ አደረጃጀት አንድ ብርጌድ እጅግ ቢበዛ እስከ 8 ሻለቃ ሊደራጅ ሲገባ፤ በዚህ የደቡብ ትግራይ ጦርነት የተካፈሉት ምንሊክ፣ አሳምነው ፅጌ፣ አባይና ቴድሮስ የተሰኙት የአማራ ክልል ብርጌዶች ግን፤ እያንዳንዳቸው ከ10 እስከ 13 ሻለቃዎች የታጨቁ ነበሩ፡፡

በትግራይ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ከመፈፀምና የሕዝብንና የመንግስትን ሃብት ከማውደምና ከመዝረፍ የዘለለ፤ ወታደራዊ ስልጠና ብቃትና ትጥቅ ያላሟላው ይህ በገፍ በማዕበል መልክ እንዲማገድ የተደረገው የአማራ ገበሬና ወጣት፤ በማያውቀው በማይመለከተው የጥቂቶች ፍላጎት ማስፈፀሚያ ሆኖ፤ በርካቶች ክቡር ህይወታቸውን ከፍለዋል፡፡ በርካቶችም በሰላም ለትግራይ የመከላከያ ሰራዊት እጃቸውን ሰጥተዋል፡

የትግራይ ሕዝብ በታሪኩ ስለአገርና ሕዝቦች እራሱን አሳልፎ ቤዛ መስዋእት ያደርግ ነበር እንጂ፤ በሌሎች ሕዝቦች ላይ አፈሙዙን አቅንቶ አያውቅም፡፡ ከአንድ ክፍለዘመን በላይ በትግራይ ሕዝብ ማንነት ላይ በተደጋጋሚ እየተፈፀመ ያለው የማእከላዊ መንግስት ጥቃት፣ ጭፍጨፋ፣ ዕልቂት፣ ውድመት ግን፤ መረን የለቀቀ ዓለምን ያሸማቀቀ ነው፡፡ በርካታ ኢትዮጵያውያንም በተለይ ደግሞ የአማራ ገበሬና ወጣት፤ ለዚህ ተከታታይነት ያለው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ቀዳሚ ሰለባ በመሆን፤ በሕዝቦች መካከል የማይሽር ቁርሾ ለትውልድ እያተረፋችሁ ነው፡፡

በትግራይ ላይ የሚካሄደው የእብሪተኝነት ወታደራዊ ዘመቻ፤ በርካቶችን መብላቱ ሳያበቃ፤ አሁንም በርካቶች የጥቂቶችን መሰሪ የክተት ጥሪ እየተቀበሉ ወደ ትግራይ እየዘመቱ፤ መተኪያ የሌለውን ህይወታቸውን በደመከልብነት፤ በከንቱ እየከፈሉ ነው፡፡ ይህ ዘግናኝ የደም መፋሰስ ማቆሚያ ሊበጅለት ይገባል፡፡ ትውልድ እያለቀ ነው! ወደ ትግራይ የምትዘምቱበትና የአብርሃም በግ የምትሆኑበት አንዳችም ምክንያት ወይ ዓላማ የለም!

ለመሆኑ ባለፉት ስምንት ወራት ወደ ትግራይ የዘመቱትና ሳይመለሱ የቀሩት ብዙ ዓስር ሺዎች የኢትዮጵያ ወታደሮች፤ ልጆቼ የት ደረሱ ብሎ የሚጠይቅ ሕዝብ እንዴት ሊገኝ አልቻለም!? በዓለም አቀፉ ሚዲያና የቀይ መስቀል ማሕበር የተረጋገጠውን፤ ከስምንት ሺሕ በላይ በጦር ምርኮኛነት መቐለ የሰፈረው የኢትዮጵያ ሰራዊት በአደባባይ በላኪዎቹ ሲካድ፤ እንዴት የሚጠይቅ ሕዝብ ጠፋ!?

የትግራይ ሕዝብ የመኖር መብቱን ለማስከበር፤ መክፈል የሚገባውን የህይወት ዋጋ ለመክፈል አንዳችም አያመነታም፤ ምን ጊዜም ዝግጁና ብቁ ነው! ሌሎችን ልውረር ላጥፋ አላለም! በቀየው በቤቱ ነው እየተጨፈጨፈ እየታረደ ያለው፤ ሃብት ንብረት ቅርሱ ነው እየወደመ እየተዘረፈ ያለው! አትድረሱብኝ ተከባብረን በዕኩልነት እንኑር ነው ያለው!

“ተከባብረን በዕኩልነት እንኑር!” የምትለውን ሐረግ፤ እንደምን አንድ ጤነኛ አእምሮ ያለው ሰው ወይ አንድ ሕዝብ፤ ሊፀየፍ ሊጠላና በእብሪት ተወጥሮ ሌላውን ሕዝብ ለማጥፋት ነፍጥ ያነሳል!? ስለምንስ የትግራይ እናቶች ህፃናት ልጃገረዶች ይደፈራሉ!? ስለምንስ የትግራይ ሕዝብ ይጨፈጨፋል!? ቅርሶቹ ኣብያተ ክርስታያናትና መስጊዶቹ ስለምን ይወድማሉ!? ስለምንስ የሕዝብና የአገር ሃብት ይወድማል ይዘረፋል!? የአማራም ሆነ በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያልባነኑበት ጥያቄ! ማብቂያ መድረሻው እስከምን ድረስ ይሆን!

https://www.facebook.com/kassa.hailemar ... 9007842375

sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: ይድረስ ለአማራ በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ከካሳ ሃይለማርያም (Unofficial Tigray Defense Forces (TDF) Spokesman)

Post by sarcasm » 13 Jul 2021, 15:10

አርሶ አደሮችና አረጋውያን ቆመህ ጠብቀኛቸውን ወልውለው ለወታደራዊ ግዳጅ እየተመሙ ሲሆን ሸገር ላይ ወታደሮች የንጉሱን ፓርኮች በችግኝ እያስዋቡ ነው። ዘመነ ብልጥግና! ጦርነት ዘለቄታዊ ሰላም አያመጣም በጠረጴዛ ዙሪያ ጨርሱት ብንል ሰሚ ጠፋ።

የሆነው ሆኖ 'ፋኖ ተሰማራ እንደ ሆቺሚን እንደ ቼኩቬራ' የሚሉት የአብን አመራሮች የት የት እንደተሰማሩ እስኪ ጠቁሙን። በለጠ ሞላ በራያ ግንባር ስምሪት እየሰጠ ይታያል ስንል ቆቦ ለድጋሚ ምርጫ እየተዘጋጀ ነው ፤ ጋሻው መርሻ ማይጠ(ፀ)ብሪ ግንባር ሲጠበቅ እስቴ ላይ እስክስታ እየወረደ ነው ፤ አገኘሁ ተሻገር የሰማንያ አመት አዛውንት ለውጊያ መለመልን የሚል ድቤ እያስደለቀ ነው ፤ መንግስቱ ታደለን ምንሽር ከምታስታጥቀው ላይቤሪያ ሄዶ ኢቦላን ቢዋጋ ይመርጣል።

ባጠቃላይ ርስቴ በሚል ሚዲቫል እሳቤ አርሶ አደር የሚያጫርሰው አለሌ በእሳቱ እንደማይለበለብ ያውቃል። ከዛኛው ወገን እዚሁ ፌስቡክ ላይ የምናውቀው አክቲቪስት ሃፍቶም ልዩ ሃይል ከነፓትሮል መኪናው ማርኳል እየተባለ ነው። ጋሻው መርሻና ወዳጆቹም ተመሳሳይ የጦር ሜዳ ጀብዱ ያሳዩን ይሆን? ለማንኛውም በአርሶ አደር ህይወት መቀለዱን ተዉትና ጉዳዩን በውይይት ለመፍታት ሞክሩ። የእርስ በርስ ጦርነት ላይ ነዳጅ መነስነስ ቅሽምና ነው።
Please wait, video is loading...

Post Reply