AbebeB ጥራዝ ነጠቅ ነው : ኣውቃለሁ ለማለት ነው ? here is complete reply:
https://www.facebook.com/muluken.tesfaw ... 1429067765
ያላነበበውን ወይም አንብቦት ያልገባውን መጽሐፍ የሚጠቅሰው የትግሬ ሜዲያ ሐውሱ ስታሊን ገብረ ሥላሴ
( Achamyeleh Tamiru )
አንድ ወዳጄ የትግሬ ሜዲያ ሐውስ “ጋዜጠኛ” የሆነ ሰው “ስለ ወልቃይት ታሪክ ጽፏልና መልስ ስጥ" የሚል መልዕክት ዛሬ ጧት በውስጥ መስመር ልኮልኝ አነበብሁት። ወዳጄ “ጋዜጠኛ” ሲል የገለጠው ይህ የትግሬ ሜዲያ ሐውስ ሰው ከዚህ በፊት «እኔ የምኮራበት አንድ ነገር ቢኖር በእኔ ትውልድ ኢትዮጵያ ስትፈርስ ቆሜ ማየቴ ነው» ሲል የሰማነው ስታሊን ገብረ ሥላሴ ነው።
ስታሊን ወልቃይትን የትግሬ እንደሆነች ያሳያል በሚል በፌስቡክ ግድግዳው ያጋራው የታሪክ ገጽ ስትፈርስ ቆሞ በማየቱ እንደሚኮራበት ስለነገረን አገር የእንግሊዝ ኢደንበርግ ተወላጁ ማይክል ሩሴል እ.ኤ.አ. በ1800 ዓ.ም. “Nubia And Abyssinia” በሚል የጻፈውን መጽሐፍ ነው።
በነገራችን ላይ ይህንን የማይክል ሩሴልን መጽሐፍ ሳያነቡ በወረራ የያዟቸውን የጎንደርና የወሎ ወረዳዎች ለማጻናት ሲሉ እንደ ታሪክ ምንጭ በመጠቀም ስታሊን ገብረ ሥላሴ የመጀመሪያው አይደለም። ከአራት ዓመታት በፊት ኃይላይ አበራ የሚባለ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ የማውቀው የእንዳፈላሲት ልጅ የሆነ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ መምህር ለጥፎት መልስ ሰጥቼው ነበር። በዚህ ዓመትም "የፈንቅል መሪ" ነኝ ይል የነበረውና በወያኔ የተገደለው የማነ ንጉሥ፤ የአረናው አምዶም ገብረ ሥላሴ፣ ወዘተ ለጥፈውት ያላነበቡትንና አንብበውት ያልገባቸውን መጽሐፍ እንደሚጠቅሱ በማውሳት መልስ ሰጥቼ ነበር።
እንግዲህ ስታሊን እንደ አዲስ ግኝት የሩሴልን መጽሐፍ ዛሬ ለማጣቀስ የሚሞክረው ለአራት ዓመታት መልስ ሲሰጥበት የኖረውንና መጽሐፉን ገልጦ ቢያነበው የያዘው ማስረጃ እሱ ሊነግረን ከፈለገው በተቃራኒ ስለመሆኑ ያልተገነዘበውን መጽሐፍ ነው። ስታሊን ሳያነብ የሚጠቅሰውን የማይክል ሩሴልን “Nubia And Abyssinia” መጽሐፍ ቢያነበው ኖሮ ወልቃይትን፣ ጠለምትን፣ ጠገዴንና ሁመራን የትግሬ ለማድረግ የጠቀሰው መጽሐፍ የአማራና የትግሬ ተፈጥሯዊ ወሰን የተከዜ ወንዝ እንደሆነ ከሶስት አራት ጊዜ እንደጠቀሰና ሩሴል “የትግሬና የአማራ ተፈጥሯዊ ወሰን” ሲል የገለጸው ተከዜን ተሻግረው ይገባናል የሚሉት መሬት ቢኖር መጽሐፉ ወራሪዎች ስለመሆናቸው በማስረጃነት የሚቀረብ እንጂ ይገባናል የሚሉትን የሚደግፍ አለመሆኑን ይረዳ ነበር።
ስታሊን የጠቀሰው “Nubia And Abyssinia” የማይክል ሩሴል መጽሐፍ መግቢያ ላይ እንደተገለጠው ደራሲው መጽሐፉን የጻፈው ስኮትላንዳዊው ጀምስ ብሩስ፣ ሔንሪ ሳልትና ናትናኤል ፒርሰን ኢትዮጵያን ጎብኝተው የጻፏቸው መጽሐፍት በዋና የታሪክ ምንጭነት በመጠቀም ነው። እነዚህ ተጓዦች ስለ ወልቃይት ታሪክ በዘመናቸው የሰጧቸውን ምስክርነቶች "የወልቃትር ጉዳይ" በሚል ርዕስ በጻፍሁት የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ በዝርዝር ማግኘት ይቻላል።
ስታሊን ገብረ ሥላሴ ሳያነብ ከለጠፋው የማይክል ሩሴል መጽሐፍ “Nubia And Abyssinia” የመጽሐፉ ገጽ 5 ገጾችን ያህል ወደኋላ ተመልሶ ቢያነብ ኖሮ በጠቀሰው መጽሐፉ ገጽ 74 ላይ ማይክል ሩሴል “ተከዜ የአማራና ትግሬ ተፈጥሯዊ ወሰን ነው” በሚል የጻፈውን ያገኘው ነበር። በመጽሐፉ ገጽ 115 ላይም ተመሳሳይ የታሪም ምስክርነት ተጽፎ እናገኛለን።
ባጭሩ ስታሊን ሳያነብ የጠቀሰው የማይክል ሩሴል “Nubia And Abyssinia” መጽሐፍ ገጽ 74 ላይ “ተከዜ የአማራና ትግሬ ተፈጥሯዊ ወሰን ነው” በሚል የተጠቀሰው የታሪክ ምስክርነት ከታች ተያይዟል። ከዚህ በተጨማሪ በዚሁ ስታሊን በጠቀሰው የማይክል ሩሴል መጽሐፍ ገጽ 115 ላይ ትግራይ ተከዜን ተሻግሮ እንደሚገኝ የጻፉት ተያይዟል።
ስታሊን የእውነት ጋዜጠኛ ቢሆንና ስለ ትግራይ ታሪካዊ ወሰን የማሳወው የእውነት ፍላጎት ቢኖረው ኖሮ ኢትዮጵያን ያልጎበኘውንና ኢትዮጵያን የማያውቀውን ማይክል ሩሴል ለመጥቀስ እንግሊዝ ድረስ ሄዶ ከሚሄድ “ያገለግልባት” የነበረችው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ከዝና ያስቀመጠችውንና ሩሴል መጽሐፉን ባሳተመበት ዘመን ትግሬን ያስተዳድሩብ የነበሩት ራስ ወልደ ሥላሴ የሚያስተዳድሩት የትግሬ ግዛት ወሰኑ ከየት እስከየት እንደሆነ የሰጡትን ምስክርነት ያገኝ ነበር። ሩሴል መጽሐፉን በጻፈበት ዘመን ትግሬን ያስተዳድሩ የነበሩት የትግሬ ተወላጁ ራስ ወልደ ሥላሴ የትግሬ ግዛት ከየት እስከየት እንደሆነ ለወቅቱ አንጋሽ ለራስ ጉግሣ በጻፉት ደብዳቤ ጠቅሰውት እናገኛለን።
ሩሴል መጽሐፉን ባሳተመበት ዘመን የወቅቱ የትግሬ ገዢ ራስ ወልደ ሥላሴ ስለሚያስተዳድሩት የትግሬ ጠቅላይ ግዛት ወሰን የነገሩን የዘመነ መሳፍንቱ ራሥ ጉግሣ ትግሬን በማዕከላዊው መንግሥት ስር አድርገው ለመግዛት ባሰቡና የማስገበር ዘመቻ ወደ ትግሬ ለማድረግ በተሰናዱ ጊዜ ራስ ወልደ ሥላሴ የራስ ጉግሣን ወረራ በመቃወም ወደ ጎንደር በላኩት ደብዳቤ ነበር። ይህን የራስ ወልደ ሥላሴን ደብዳቤ ከራስ ወልደ ሥላሴ ጋር እንጣሎ ይኖር የነበረው ናትናኤል ፒርስ በማስታወሻው እንዲህ መዝግቦታል፤
“…እርስዎም ሆነ ከርስዎ በፊት የነበሩት [እንደራሴው] አባትዎ ትግሬን ተቆጣጥረው አያውቁም። እኔም ላሳስብዎት የምፈልገው ትግሬን ለመውረር ተከዜን አቋርጣለሁ ብለው እንዳያስቡ ነው።”
[ምንጭ፡ Pearce, N. (1831). The Life and Adventures of Nathaniel Pearce Written by Himself; Page 71.]
ስለዚህ ጉዳይ የታሪከ ነገሥቱ ጸሐፊ የሚከተለውን ይነግረናል፤
ወመጽአ ደጅ አዝማች ዘውዴ እም ሰፈሩ ይባባ ወዓደወ ፈለገ አባይ ፀብዓ ለበጌድምር፤ ወማኅረከ ሰብአ ወአልህምተ በአፈረዋናት ወበወይራ ወተመይጠ ውስተ ሰፈሩ። ወእንዘ ሀሎ በዝየ አኃዞ ለወልደ ፋሲል ሽፍታ ዘቁለላ አንዖኛ ሀብቱ ወሀቦ ለደጅ አዝማች ዘውዴ ፈነዎ ውስተ ሙቃሔሁ። ወመጽአ ወሬ እም በጌምድር እንዘ ይብል ተንሥአ ደጅ አዝማች ጉግሣ እምሰፈሩ ልቦ ደጅ አዝማች ዘውዴኒ ተንሥአ እምሐገየ ቦቱ ይባባ ሐለፈ መንገለ ወዳግ በጽንፈ አንዳሳ። ወሰፈረ በህየ። ወመጽአ ደጅ አዝማች ጉግሣ በበሰፈሩ ወሰፈረ በሮቢት ወተዓየኑ ፪ሆሙ። ወእምድሀረዝ መጽኡ መነኮሳት ዘገዳመ ቆራጣ ለአስተሳልሞ ፪መኳንንት ተካየዱ በጽኑዕ መሐላ። እንዘ ሀለው በዝንቱ መጽኡ ወዓልቱ ለራስ ወልደ ሥላሴ ለአስተሣልሞ። አነ ሀለውኩ በብሔርየ አንትሙኒ ንበሩ በበብሔርክሙ በፍቅር ወበሰላም ይቤሉ መኳንንት ኦሆ።
[ምንጭ፡ Blundell, W. (Ed.)(1922). The Royal Chronicle of Abyssinia, 1769-1840. The University Press; Page 193.]
ትርጉም፤
ደጃዝማች ዘውዴ ከሰፈራቸው ከይባባ ተነስተው በጌምድርን ለመውጋት አባይን ተሻግረው ሄዱ። የአፈረዋናትና የወይራን ሰው ማርከው ከብቱን ዘርፈው ወደሰፈራቸው ተመለሱ። በዚያም ሳሉ አንፆኛ ሀብቱ የቁለላውን ሽፍታ የፋሲልን ልጅ ይዞ ለደጃዝማች ዘውዴ በሰጣቸው ጊዜ አስረው ላኩት። ደጀዝማች ጉግሣ ከሰፈራቸው ከሊቦ ተነስተዋል የሚል ወሬ ከበጌምድርበተሰማ ጊዜ ደጃዝማች ዘውዴ ከይባባ ተነስተው የወዳግን መንገድ ይዘው አንዳሳ ድንበር ሄደው ሰፈሩ። ደጃዝማች ጉግሣም ከሰፈራቸው ተነስተው ሮቢት ላይ ሰፈሩ፤ ሁለቱም ድንኳናቸውን ተከሉ። ከዚህ በኋላ የቆራጣ [ወለተ ጴጥሮስ] ገዳም መነኮሳት ሁለቱን መኳንንት ሊያስታርቁ መጡ፤ [አስታርቀውም] በጽኑ መሃላ ቃል ኪዳን አስገቧቸው። በዚህ ሁኔታ ሳሉ የራስ ወልደ ሥላሴ አሸከሮች ሊያስታርቁ መጡ። “እኔ በአገሬ አለሁኝ እናንተም በየአገራችሁ በፍቅርና በሰላም ኑሩ”[ብለው በአሽከሮቻቸው አማካኝነት የዕርቅ ሀሳብ አቀረቡ]። መኳንንቱም [በራስ ወልደ ሥላሴ የዕርቅ ሀሳብ] ተስማሙ።
ራስ ወልደ ሥላሴ “በአገሬ አለሁ” ያሉት ትግሬን ነው። ራስ ጉግሳም ተከዜን ተሻግሮ ትግራይንና አባይን ተሻግሮ ጎጃምን አስገብራለሁ ሳይል ሁሉም መኳንንት በየአገራቸው በሰላም እንዲኖሩ ሀሳብ አቀረቡ። ለእንደራሴው ለራስ ጉግሣና ለዘውዴ ከላኩት መልዕክት የምንረዳው አገሬ ትግራይ የሚሉት የሚገኘው ከተከዜ በስተ ምስራቅ መሆኑን ነው። በዚህ ወቅት ትግራይ ከተከዜ በስተ ምዕራብ አንድ ጋት መሬት ቢኖረው ኖሮ ገዢው ራስ ወልደ ሥላሴ ለራስ ጉግሣ በላኩት መልዕክት “ትግሬን ለመውረር ተከዜን አቋርጣለሁ ብለው እንዳይሞክሩ” የሚል መልዕክት ትግሬን ሊወርር ነው ብለው ላሰቡት ለራስ ጉግሣ አይልኩም ነበር። [ ምንጭ፡ Abir, M. (1968). Ethiopia: Era of Princes, Longmans, Green and Co.; Pages 30-33]
ራስ ወልደ ሥላሴ ከራስ ጉግሣ ጋር ለመግጠም ዝግጅት ያደርጉ በነበረበት ጊዜ የላስታና የዋግ ገዢዎች ከራስ ወልደ ሥላሴ ጋር አብረው ሲሰለፉ፤ የስሜንና የወልቃይት ገዢዎች ደግሞ በራስ ጉግሣ በኩል ተሰልፈው ራስ ወልደ ሥላሴን ለመውጋት ተነስተው ነበር። ከራስ ጉግሣ ጋር በመሆን የትግሬውን ገዢ ራስ ወልደ ሥላሴን ለመውጋት ስሜንና ወልቃይት ሲነሱ ስሜንን ራስ ገብሬ፤ ወልቃይትን ደግሞ ልጃቸው ቀኛዝማች ኃይለ ማርያም ገብሬ ይገዙ እንደነበር ናትናኤል ፒርስ መዝግቦታል። [ምንጮች፤ Pearce, N. (1831). The Life and Adventures of Nathaniel Pearce written by Himself; page 100 and 105. See also; Abir, M. (1968). Ethiopia: Era of Princes, Longmans, Green and Co.; Page 32.
በሌላ አነጋገር ወልደ ሥላሴ ትግሬን ጠቅልለው ይገዙ በነበረበት ወቅት፤ ራስ ገብሬ ስሜንን፣ ልጃቸው ቀኛዝማች ኃይለ ማርያም ደግሞ የወልቃይት ገዢ ሆነው ለማዕከላዊ መንግሥቱ እንደራሴ ለራስ ጉግሣ እየገበሩ እስከ ባምብሎ በመለስ ተከዜ በፈሰስ ያስተዳድሩ ነበር። ቀኛዝማች ኃይለ ማርያም ገብሬ በ1803 ደጃዝማች ተብለው ባባታቸው ስር የወልቃይት ገዢ ሆነው ከቆዩ በኋላ አባታቸው በ1807 ዓ.ም. ሲሞቱ ከተከዜ በመለስ ባምብሎ በፈሰስ ያለውን የስሜን ግዛት እስከ 1818 ዓ.ም. ድረስ አስተዳድረውታል። [ ምንጭ፡ Abir, M. (1968). Ethiopia: Era of Princes, Longmans, Green and Co.; Page 32-33.] ነበገራችን ላይ ቀኛዝማች ኃይል ማርያም የእቴጌ ጣይቱ አያት ናችው። የእቴጌ ጣይቱ ሙሉ ስም ጣይቱ ብጡል ኃይለ ማርያም ገብሬ ተስፋ እያለ እስከ ዮልዮስ ድረስ ይሄዳል። ደጃዝማች ዮልዮስ የወለቃ ተወላጅ ሲሆኑ በዐፄ ሱስንዮስ ዘመን ተከዜ በፈሰስ ባምብሎ በመለስ የሆነውን ስሜንን ያስተዳደሩና ንጉሡ ሃይማኖታቸውን በየቀሩ ጊዜ ይህንን የንጉሡን ሃይማኖት መቀየር በመቃወም ንጉሡን ከሥልጣን ለማውረድ ከንጉሡ ጋር ጠገዴ ላይ በተካሄደው ጦርነት በጦር ሜዳ የወደቁ ጀግና ናቸው።
እንግዲህ! ማይክል ሩሴል መጽሐፉን ባሳተመበት ዘመን የነበረው ታሪክ ከፍ ብሎ የቀረበውን ይመስላል። ሌላው ቢቀር ስታሊን ሳያነብ በጠቀሰው የማይክል ሩሴል “Nubia And Abyssinia” መጽሐፍ መሰረት እንኳን ብንሄድ ተከዜ የአማራና ትግሬ ተፈጥሯዊ ወሰን ስለሆነ የትግሬ ብሔርተኞች ተከዜን ተሻግረው ይገባናል የሚሉት አጽመ ርስት እንደሌላቸው ሊያውቁ ይገባል እንላለን።
በተረፈ ያላነበበውን መጽሐፍ የሚጠቅሰውን ስታሊን ገብረ ሥላሴን «ከመጠምጠም መማር ይቅደም» ፤ «ወሬ ሲነግሩህ ሀሳብ ጨምርበት» ፤ "በሊቃውንት ፊት ጥቅስ" የሚሉትን የአያቶቻችን ጥልቅ ምክር በመለገስ ተስናብቻለሁ።
ከታች የታተሙት ሁለት ገጾች ስታሊን ገብረ ሥላሴ ሳያነብ በጠቀሰው የማይክል ሩሴል “Nubia And Abyssinia” መጽሐፍ ውስጥ ተከዜ የትግሬና የአማራ የተፈጥሮ ወሰን መሆኑን የሚያረጋግጡ የታሪክ ማስረጃዎች ናቸው።
መልካም ቀን!
Abebe B ጥራዝ ነጠቅ ነው : ኣውቃለሑ ለማለት ነው ?