Page 1 of 1

ሆረስ ለምን ሳይማር ያስተማረውን ህዝብና የገዛ ህሊናውንም ክዶ፣ ወደ ተራ ውታፍ ነቀላ ወረደ? ማፈርንስ ለምን ተወ? ሲሳይ አጌና በስንት ጣእሙ! ነቀላም'ኮ ልክ አለው

Posted: 11 Jul 2021, 12:40
by eden
Horus wrote:
10 Jul 2021, 14:18
ብርቱካን ሚደቅሳ በአስገራሚ እንደ ማር ወለላ በሚፈሰው ልሳኗ፣ እንደ ስንዴ በጸዳው ቋንቋዋ፣ እንደ ሜሎዲ በተዋሃደው ሃሳቧ፣ ጥርት ባለው የፖለቲካ ክህሎቷ የኢትዮጵያን የፖለቲካ አየር በሸነል ሽቶ አወደቸው!
ይህን ለመረዳት፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር፣ ታምራት ላይኔ፣ በቅርቡ ያሉትን እናስታውስ:

መሪ ሲወርድ፣ ማህበረሰብ ይወርዳል። ምክንያቱም፣ የተያዙ የማህበራዊ እሴቶች፣ መሪው ሲጥሳቸው፣ ማህበረሰቡ፣ አሃ! ይሄ ፍቁድ ነው በሚል፣ መሪውን ተከትሎ ይወርዳል።

ጉዳዩ ወዲህ ነው...

በሰሜኑ ጦርነት ሽንፈትን ያመጡ ጀነራሎች፣ አብይ፣ ግስላው፣ አነፍናፊው፣ ድል ቁርሱ በማለቱ፣ ሆረስም ይህን ተከትሎ፣ ምርጫው አግላይ እና በብዙ ቦታዎች አብይ ብቻውን የተወዳደረበት መሆኑ እየታወቀ፣ መሬት ላይ ያለውን እውነታ ክዶ፣ ቡርቴን ሲያመልክ ይታያል።

መሪ ሲወርድ፣ ማህበረሰብ ይወርዳል። የሆረስም የቁልቁለት የህሊና ጉዞ ከዚህ የመነጨ ነው።

ሆረስ ጥሩ ማሳያ እንጂ ችግሩ ማህበረሰቡ ውስጥ እየሰረፀ የመጣ መሆኑ፣ ይሄም ለሃገር ግንባታው የማይበጅ መሆኑን ለማሳየት ነው።