****
ኦሮሚያ እና ሲዳማን ጨምሮ በበርካታ የሃገሪቱ አከባቢዎች ብልፅግና ብቻውን ነው የተወዳደረው።
ይህ የሆነው ገዢው ፓርቲ ከፍተኛ ድጋፍ ያላቸውን ድርጅቶችና ፖለቲከኞች ከምርጫው ገፍቶ በማስወጣቱ ነው። በተለይ የግራ ፖለቲከኞችና ድርጅቶች እንዲጠፉ ተድርጓል።
አስመራጬ ቦርድም ተመራጭ ድርጅቶችም አህዳውያን እና ሌሎች ሆዳቸውንና ኪሳቸውን ከሞሉ ግድ የማይላቸው ግለሰቦች ናቸው።
እናም ምርጫው ሁሉን አሳታፊ እና ፍትሃዊ አልነበረም። የአህዳውያን ምርጫ ነው።
አህዳውያን ብቻ የደነሱበት ምርጫ ደግሞ ታሪካዊ የሆነውን የሃገሪቱን የፖለቲካ ችግር አያቃልልም። ብልፅግናም ቢሆን ህጋዊ ነኝ ሊል ይችል ይሆናል፤ በዚህ ሂደት ቅቡልነትን ማረጋገጥ ግን ፈፅሞ አይችልም።
Please wait, video is loading...