Page 1 of 1

"ኤርትራን ጋብዘው ነው ህዝቡን ያስጨፈጨፉት። ስለዚህ መከላከያ የራሱን ህዝብ ከድቶ በጠላት (የኤርትራ እና የአማራ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ) ሃይል አስመታው እንጂ ህዝቡ መከላከያን አልከዳም።"

Posted: 08 Jul 2021, 18:57
by sarcasm
"የትግራይ ህዝብ መከላከያን ከዳ የሚባለው ነገር ሲበዛ ይገርማል። መከላከያም "ተከዳሁ" እያለ በየሚድያው እየቀረበ የሚያናፍሰው የጥላቻ መርዝ ምንም እውነትነት አይኖረውም።

ሲጀመር መከላከያ በትግራይ ህዝብ ተጋብዞ ወይንም የትግራይን ህዝብ ከጠላት ለመታደግ አይደለም ወደ ትግራይ የገባው። የትግራይ ሃይል አጠቃኝ (ሰሜን እዝ) ብሎ ከታጠቀው የትግራይ ሃይል ጋር ሊዋጋ ገባ ብንል እንኴ ህዝብ የሚወጋበት፣ ህዝብ እየተገደለ ወደ ገደል የሚጣልበት ምክንያት አልነበረም። ተከዳ የሚባለው ህዝቡን ለመታደግ ገብቶ ቢጠቃ ነው ለምሳሌ ኤርትራ ትግራይን ወርራ ከኤርትራ ሃይል ሊከላከላቸው ገብቶ ህዝቡ መልሶ እነሱኑ ቢወጋቸው "ተከዳን" ማለት ይችላሉ።

የሆነው ግን ኤርትራን ጋብዘው ነው ህዝቡን ያስጨፈጨፉት። ስለዚህ መከላከያ የራሱን ህዝብ ከድቶ በጠላት (የኤርትራ እና የአማራ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ) ሃይል አስመታው እንጂ ህዝቡ መከላከያን አልከዳም። ህዝቡ በመከላከያም፣ በኤርትራ ጦርም፣ በአማራ ክልል ሃይሎችም ሲጠቃ ሌላ የሚያድነው አቤት የሚልበት አካል ስለሌለ ተገዶ ራሱን ወደ መከላከል ገባ። እንደ ህዝብ የተቃጣበትን እንደ ህዝብ ቆሞ ተከላከለ። እናም ከጂው ከውጭ እና ከውስጥ ወራሪ ሃይሎች ያላዳነው እና ያስጨፈጨፈው አካል እንጂ ህዝቡ አይደለም።"
Please wait, video is loading...