Page 1 of 1

የጎጃም ልጆችን እየነጠሉ ማሰር ይቁም! - ተጻፈ በኃይለየሱስ አዳሙ

Posted: 03 Jul 2021, 09:54
by sarcasm
የጎጃም ልጆችን እየነጠሉ ማሰር ይቁም!

በቃሉ አላምረውና አበበ ባዩ የጎጃም ልጆች ናቸው። በሙያቸው ጋዜጠኛ! አብዛኛዎቹ ጎጃሜዎች እንዳደረግነው የትግራዩን ጦርነት ተቃውመዋል። የህወሓት ደጋፊ አይደሉም። ሰላማዊ የትግራይ ተወላጆች ላይ የደረሰውን ሰቆቃ ግን እንደሁላችንም ተቃውመዋል። ምን የሚያሳስር ወንጀል ሰርተው ነው ታድነው የሚታሰሩት?

መፍትሄው ውይይት ነው የሚለውን ሀሳብ አሁን ላይ መንግስትም እያንፀባረቀው ነው። በይፋ ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩት እነ ጌታቸው ሺፈራው በነፃነት በሚንቀሳቀሱበት ሀገር እነዚሀን የጎጃም ልጆች ነጥሎ ማሰር ውስጡ ፀረ ጎጃሜነት ያለበት አካሄድ ነው።

ባስቸኳይ ይፈቱ!

ሰዎችን በጠራራ ፀሀይ የገደሉና ከተማ ያወደሙ ሰዎች በነፃነት በሚንቀሳቀሱበት ሀገር እነዚህን የጎጃም ልጆች የመሰላቸውን ስለተናገሩ ማሰር በፍፁም ተቀባይነት የለውም ብቻ ሳይሆን ፀረ ጎጃሜነትም ነው። በሀሳባቸው ልንስማማ ላንስማማ እንችላለን። ማሰርና መደብደብ ግን ተቀባይነት የለውም!



Please wait, video is loading...

Re: የጎጃም ልጆችን እየነጠሉ ማሰር ይቁም! - ተጻፈ በኃይለየሱስ አዳሙ

Posted: 03 Jul 2021, 10:05
by ethioscience
ደግ አደረጉ :!: :!: እንደባንዳ መስቀል ነበር :!: ከወያኔ ጋር የሚያሽቃብጥ አማራ ከዚህ በላይ ይገባዋል!! ጎጃም ምናምን የሚሉት ለቅሶ የለም :!: :!: :!: