Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Ejersa
- Member
- Posts: 3978
- Joined: 05 Nov 2019, 10:39
Post
by Ejersa » 30 Jun 2021, 06:46
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና መከላከያ ሰራዊት በጋራ በሰጡት መግለጫ “ከዚህ በኋላ በሰሜን ኢትዮጵያ ፤ትግራይ ክልል ለሚከሰት ችግር የኢትዮጵያ መንግስት ተጠያቂ” እንደማይሆን አስታወቀ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሬድዋን ሁሴን ዛሬ በሰጡት መግለጫ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከመቀሌ ለቆ በመውጣቱ፤ የፌዴራል መንግስት ከዚህ በኋላ በትግራይ ክልል ዙሪያ ለሚኖር ችግር ተጠያቂ እንደማይሆን ተናግረዋል፡፡
ዓለም አቀፍ ተቋማትም “ከዚህ በኋላ ዕርዳታ ደረሰ አልደረሰ ብለው የፌዴራ መንግስትን ሊጠይቁ” እንደማይገባ የገለጹት አምባሳደር ሬድዋን፤ የትግራይ ክልልን በተመለከተ ሙሉ ኃላፊነቱን አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው ህወሃት እንደሚወሰድም ገልጸዋል፡፡
አምባሳደር ሬድዋን በትግራይ ክልል የተከሰተው ግጭት፤ ኢትዮጵያን ለከፍተኛ ኪሳራ እንደዳረጋት ገልጸው በልማት ሂደቱ ላይም ከፍተኛ ተጽዕኖ እንዳሳደረ ተናግረዋል፡፡
ሕወሃት የሀገርን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ እንደጣለ ያነሱት ሚኒስትር ዴኤታው ሱዳን፤ የኢትዮጵያን ሉኣላዊ ድንበር ጥሳ እንድትገባ አጋልጦ እንደነበርም ገልጸዋል፡፡ በትግራይ ክልል በተደረገ ዘመቻ፤ ከ 100 ቢሊየን ብር በላይ መውጣቱም ተገልጿል፡፡ መንግስት የተናጠል ተኩስ አቁም ያወጀው እና ወታደሮችን ከመቀሌ ያስወጣው በመንግስት ፖለቲካዊ ውሳኔ መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል፡፡
መንግስት የተኩስ አቁም ያወጀው እና ወታደሮችን ከመቀሌ ያስወጣው፤ ሀገርን ለተጨማሪ የሀብት ብክነት ላለመዳረግ መሆኑ ተገልጿል፡፡ አሁን ላይ የኢትዮጵያ ጦር በማንኛውም ጊዜ ወደ ትግራይ የመመለስ ሙሉ አቅም እንዳለውም ሚኒስትር ደኤታው አብራርተዋል፡፡
-
Abe Abraham
- Senior Member
- Posts: 14414
- Joined: 05 Jun 2013, 13:00
Post
by Abe Abraham » 30 Jun 2021, 08:48
አሁን ላይ የኢትዮጵያ ጦር በማንኛውም ጊዜ ወደ ትግራይ የመመለስ ሙሉ አቅም እንዳለውም ሚኒስትር ደኤታው አብራርተዋል፡፡