አገራችን ላይ ላለፉት አምስት ወራት ገበያ ላይ የነበረው ሙዝ የቀቸጨ: የማይጥም : የማይበስል :ሲያዩት የማያምር ነው:: ባለፈውም ዓመት እንዲህ ይሆን ነበር:: ምክንያቱ ግን ምን ይሆን?
ቡርቱካን ከበላሁ ብዙ ግዜ ሆኖኛል:: ቡርቱካን እስከንችራሹ ገበያ ላይ የለም:: አሁን ብቅ እያለ ቢሆንም ዋጋው በክሎ 80 ብር ነው:: ለዛውም ሎሚ ሎሚ የሚል::
ምንድነው ምክንያቱ? ለመሆኑ ይህን የሚከታተል የመንግስት አካልና ባለሙያ አለ?
አፍሪካ ውስጥ የሚበቅሉ በጣም አሪፍ እና ተወዳጅ አትክልቶች ለምን አገራችን ላይ እንዲበቅል አልተደረገም? ችግር አለብን እንዴ ? ለምሳሌ ለቸኮሌት የሚፈለገው cocoa፣
እንዲሁም coconut
በስታርችህነቱ ይዘቱ የሚታወቀው እና በምዕራብ አፍሪካ የሚታወቀው yam አገራችን ላይ የሉም:: ለምን ለምን?
በጣም ትልቁ ነገር green tea እኛ አገር ለመሆኑ አለ እንዴ ? ይህ የሻይ ዘር በጣም ለጤና አስፈላጊ መሆኑ ቢታወቅም አገራችን ላይ አይገኝም:: ለምን fermented/ቀይ ሻይ ከሆነው ሻይ ይህ ገበያ ላይ አይቀርብልንም:: አገራችን ችግር ላይ ያለች ይመስለኛል: