DDT
ፖለቲካ የምታቅ ሰው መስለሀኝ ነበር! አታቅም ማለት ነው ። ከዚህ ሃረግ በታችህ temari post ያደረገውን የህዝብ አስተያየት ስማ። ቃል በቃል ላለፈው 3 ቀን ስጽፈው የነበእውን ነው ሚነግሩህ ። ተቃዋሚዎች ድምጽ ያላገኙት እነሱም መንግስት የመለወጥ አላማ አልነበራቸውም፣ ህዝቡም ያለው መንግስት አተንክሮ ሰላም ለማግኘት እንጂ አዲስ መንግስት የማቆም አላማ አልነበረውም ። አሁንም ቢሆን ህዝቡ ምን አለ መሰልህ ? አቢይ አካታች ኢንክሉሲቨ መንግስት ይሁን ነው ያሉጥ እዚህ ቪዲዮ ላይ ምጸማቸው ሰዎች ፖለቲካ ያስተምሩሃል። ግዚው ወስደህ አዳምጣቸው ። ስለ ኢዜማ መሸነፍ የጻፍኩትን በኋላ ወደ ላይ አማጣዋለሁ። ልብ አድርግ ፖለቲካን እንደ ሳይንስ የተማርኩትና ጥርሴን የነእልኩበት ነገር ነው።
ህዝቡን ስማ፡ ሶስት የምርጫ ጥያቄ ነው የነበረው፤ ሰላም፣ የኑሮ ወድነት (ኢንፍሌሽን እና ስራ አጥነት (ኢምፕሎይመንት) ። የኢዜማ ክሽፈት ምክኛት የሚዳሰስ የሚቀመስ የህዝብ ጥያቄ ስላልነበረው ነው ማሸነፍ ሳይሆን ድምጽ የተነፈገው! አበቃሁ ! አቢይ ሌሎችን ማካተት ያለበት ለራሱ ሲል እንጂ ለማንም አይደለም። ፖለቲካ አለማወቅክን አየሁት!
ይህን ስማ
viewtopic.php?f=2&t=262577
And, this is what I wrote on June 23rd. Compare it with the commentaries of the people in the above video!
ኢዜማ የረባ የፖለቲካ ተጽዕኖ ለመፍጠር ወደ 20% የሚጠጋ ወንበር እንደ ሚፈልግ አስልቼ ከ70 እስከ 100 ወንበር እንዲኖረው ማስፈለጉን ተስፋ አድርጌ ያለኝ አስፐሪሽን ከላይ ብያለሁ ። ይህ የኔ የግል አስፐሬሽን ነበር ። በመሬት ላይ አገር ቤት ያለው ሪያሊቲ ከኔ ምኞት የተለየ ሆነ ። በቃ ሌላ ነገር የለውም ። መሰረታዊ ትንተናዬ በዚያቅ ቀን ብዬዋለሁ ። ያስገረመኝ ነገር ቢኖር ሕዝቡ ድምጹን ይህን ያህል መንፈጉ እንጂ እኔ ኢዜማ አቢይን ያሸንፋል የሚል እምነትም ሃሳብም ኖሮኝ አላቅም ።
እኔ ሆረስ ነኝ፣ ቃል አልፈልጥም! የኢትዮጵያ 2013 ምርጫ ሙሉ ግምገማ ገና አልተደረገም። ነገር ግን በብዙ ብዙ መንገድ ይህ ምርጫ የኢትዮጵያን ፖለቲካ የሚለውጥ ስለሆነ በአንጎሌ ጫፍ ላይ ሳይሆን በልቤ ስር ጥልቅ ደስታ ተሰምቶኛል ። ለምን?
እኔ የማምንበት ነገር አለ፣ ቲኦሪ ሃሳብ ነው፣ ምናብ ነው። ያ ቲኦሪ የሚፈተነው በተግባር ነው ። ጥሩ ቲኦሪ ብቻውን ጥሩ ተግባር አይሆንም። ጥሩ ተግባር የራሱ ሕግ አለው ። እሱን የተግባር ፍልስፍና፣ ዘ ፊሎሶፊ ኦፍ አክሽን ወይም ሆነ ብለን የምናደገው ተግባር ፍልስፍና ይባላል።
ፖለቲካም እንዲሁ የተግባር ህግ አለው ። ላንድ ፖለቲካኛ የፖለቲካ ተግባሩ ቁልፍ ቁም ነገር ቁልጭ አግድርጎ በአንድ ቃል ለማስቀመጥ መቻል አለበት ።
የ2013 ምርጫ አላማ ምንድን ነው ለሚለው ቁጥር አንድ ጥያቄ እኔ ደግሜ ደግሜ እንዳልኩት የዚህ ምርጫ ግብ በሕዝቡ እይታና ፍላጎት አንድ ያለን መንግስት ለመለወጥ፣ አንድ ሪጂም ወይም አስተዳደር ካንዱ ቡድን ወደ ሌላ ቡድን ለመለወጥ አይደለም ብያለሁ ። የህዝቡ ፍላጎ በወያኔ ተሰባብሮ ተፍረክርኮ ያለውን መንግስት ማጠንከር፣ አገር አንድ አድርጎ ማጠንከር ነው የህዝቡ መሰረታዊ ጥያቄና ፍላጎት ።
ይህ ነው የዚህ ምርጫ ተግባር ፍልስፍና መቆሚያ ! ስለሆነም በምርጫው ከተካፈሉት ዋና ዋና ፓርቲዎች ስንቶቹ ይህን ፍልስፍና እንደሚገባቸው አላቅም ። ኢዜማ አንድም ግዜ በዚህ ምርጫ ሲወዳደር አላማው የአቢይን መንግስት አውርዶ ሌላ አዲስ የኢዜማ መንግስት ለማምጣት ነው ብሎ አያውቅም ። ስለዚህ ኢዜማ በዚህ ምርጫ የብልጽግና አጋር እንጂ ተቃራኒ አልነበረም ።
ይህ አቋም ትክክል ነበር ። ሕዝቡ ዛሬ የመሰከረው ያንን ነው ። ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ያላቸው ፍላጎት ጠንካራ፣ ሰላም የሚያስጠብቅ፣ አገር የሚያስቀጥል መንግስት ማደራጀት እንጂ የአቢይን መንግስት አውርዶ አዲስ መንግስት ለመሆን አይደለም። ይህን የማያውቅ ፖለቲከኛ ወደ ሌላ ስራ መሄድ አለበት ።
ከሁሉም አስቀድሞ ህዝቡ ፖለቲከኞችን ያስተማረው ትምህርት ይህ ነው። እያንዳንዱ ምርጫ የዚያን ወቅት ግብና አጀንዳ አለው ፣ የዛሬ ምርጫ አጀንዳ ሰላም ማስፈን እንጂ መንግስት መለወጥ አይደለም ፤ የሆነውም ያ ነው ።
እነኢዜማ ፣ አብን ፣ ባልደራስ ፣ ምናምን ለምን የሕዝብ ድምጽ ተከለከሉ? ከላይ ብዬዋለሁ! የተሳሳተ የመሪዎች ቲኦሪ በትክክለኛ የህዝብ ተግባር ይታረማል ይባላል።
እኔ ላለፈው 30 አመት በኢትዮጵያ ከ4 ወይ 5 ፓርቲዎች በላይ መኖር የለባቸውውም ብያለሁ፤ አሁንም እላለሁ ። ዛሬ ህዝቡ የላከው ትምህርት ያ ነው። ወይ አንድ ሁኑ ወይ ወግዱ ነው ያለው ሕዝቡ ።
በኢትዮጵያ አንድ በጎሳ ቀመር የቆመ ፓርቲ አለ፣ እሱም ብልጽግና ነው ። በዜጋ ፖለቲካ ቀመር የሚቆሙ አንድ ሊብራል ፣አንድ ሶሺያል ዴሞክራሲ ፣አንድ ወግ አጥባቂ ፓርቲዎች ሊኖሩ ይችላሉ ። ሌላ አንድ አረንጓዴ ፓርቲ ሊኖር ይችላል። በቃ ከዚህ አልፈው በግለሰቦች ምኞትና ድንቁርና ላይ የቆሙ 50፣ 100 ፓርቲዎች በህዝብ እንደ ሚወገዱ ይህው አየን፣ አበቃ ! የፖለቲካ ፓርቲዎች የመንግስት አደራጅ እንጂ መንግስት እና አገር ማፍረሻ መሳሪያዎች አይደሉም ። ፓርቲ ድርጅት ነው፣ ድርጅት መሳሪያ ነው ።
ሶስተኛው፣ ኢዜማ ለምን ድምጽ ተነፈገ የሚለው ቀላል ጥያቄ ነው! ፈረንጆች ፖለቲካ የሰፈር ጨዋታ፣ የሰፈር ትግል ነው ይላሉ ። ይህም ማለት በዴሞክራሲ ውስጥ አንድ ግለሰብ ምረጡኝ ለማለት እሱ ወይም እሷ በዝርዝር ለዚያ ሰፈር፣ ለዚያ መራጭ ህዝብ ሊያደርግ፣ ምን ሊያሻሽል እንዳቀደ እና ያም ዝርዝር የሰፈር ግብ ከሌላው ፓርቲ ፕላን እንዴት እንደ ሚሻል በፋክት፣ በግልጽ ህዝቡን ማሳመን አለበት ።
ኢዜማ አንድም ቦታ ይህን ሲያደርግ አልታየም፣ ኢዜማ በፍልስፍና በዜጋ ፖለቲካ ንድፈ ነገር ከብልጽግና መለየቱ ቢታወቅም ሪቴይል ፖለቲካ ወይም የፖለቲካ ችርቻሮ የሚባለው ጭብጥ፣ የሚዳሰስ፣ የሚቀመስ ጥቅም ለህዝብ ስላላቀረበ ህዝቡ ድምጹን የሚስጥለት ምክንያት አልነበረም። ይህው ነው ሌላ ምስጢር የለውም ።
ስለሆነም ይህ ምርጫ የብዙሃኖች ጥበብ ወይም ዊዝደም ኦፍ ዘ ማስስ የተረጋገጠበት ልምድ ነው ። ይህ ማለት በተለይ ብልጽግናና ኢዜማ ግልጽ የሆነ የአጭር ግዜ ልዩነት ስለሌላቸው ፣ ፈረንጅ እንደ ሚለው ለአንድ ስራ ሁለት ሰው ከቀጠርክ አንዱን አባርር ፣ ሰዉ ብልህ፣ ብልጥ ስለሆነ ሰላምና ጸጥታ ላይ ያለውን ቡድን አጠናክሮ ጠንካራ አገር እና መንግስት እንዲኖር ድምጹን ለዚያ ሰጠ ። ይህ ነው ምስጢሩ !!
ኢዜማ አልተሸነፈም ፣ ያልጠየቀውን ሊሰጠው አይችልም ። የጎሳው ሲስተም፣ የጎሳው መዋቅር ላይ ኢዜማ ቦታ እንደሌለው ፣ኢዜማ ሊመራው ሊቆጣጠረው የሚችል እስትራክቸር እንዳልሆነ ከኢዜማ በላይ ህዝቡ አውቆ የተሳሳተውን ቲኦሪ አርሞላቸዋል ። ኢዜማ በኤትኖክራሲ ላይ ዴሞክራሲ ለተገብር አይችልም ። ኢጎሳዊ ሲስተም እስከሌለ ድረስ ኢዜማ መንግሳትዊ ስልጣን ልይዝ አይችልም ። ይህ የፖልቲካ ሕግ ነው።
የኢዜማ አላማና ስራ ኢጎሳዊ የሆነ የዜጎች ሲስተም መፍጠር ስለሆነ ወደዚያ ተግባሩ ይሄዳል ማለት ነው።
ይህ ምርጫ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች ህይወት ላንዴም ለሁሌም ይለውጣል የሚል እምነት አለኝ ። በሌላ ፖስት ላይ እንዳልኩት የዜጋ ፓርቲዎች ቢያንስ 20% ወንበር ካላገኙ የብልጽግና ማጣፈጫ ከመሆን ያለፈ ፋይዳ ስለማይኖራቸው ፓርላማ ከመቀመጥ አለመግባታቸው የተሻለው ነው። የዛሬ አምስት አመት 2 ወይም 3 አገር አቀፍ ፓርቲ ሆነው ይምጡ። እስከዚያ ኢትዮጵያ አባይን ትሙላ !! በቃ