
አቶ Hagos Weldekidan የተባሉት የትግራይ ክልል የብልጽግና ፓርቲ አመራር አባል የሆኑት ዛሬ በፌስቡክ ይህንን መልእክት ለጁንታው ባመስተላለፋቸው እናመሰግናለን።
"ታማሚና የቀበጸ ተስፋ እርምጃ"
አንድ ካንሰር ታማሚ በሐኪም ስድስት ወር ብቻ በህይወት እንደሚቆይ ይነግሯል። ታድያ በዚህ የተበሳጨ ታማሚ ሐኪሙን ይገድለዋል። ታማሚው በግድያ ወንጀል ተከሶ 18 ዓመት ይፈረድበታል፤ በውሳኔውና በዳኛውም በጣም ደስተኛ ሆነ። ታማሚው 'ስድስት ወር ትኖራለህ ያለኝን ሐኪም በመግደል 18 ዓመት እንደምኖር በዳኛ ተነግሮኛል' ሲል የደስታውን ምክንያት ገልጸዋል።
አሁን በትግራይ በተለይ በራያ፣ በእንደርታና በሌሎች አከባቢዎች የጊዚያዊ አስተዳደር አመራር አባላት በአሰቃቂ በመግደል ወደ ስልጣን የሚመለስ አለያም አሸንፋሎህ ብሎ የሚያስብ ቡድን መኖሩ ሳይ በጣም ይገርመኛል። የታማሚው ታሪክ በቀቢጸ ተስፋ እየተደገመ ነው። እየተፈጸሙ ያሉትን የስቪል አመራር ግድያዎች ከመልካምነታቸው ይልቅ ፍጹም ጎጂ ናቸው። ግድያ የሚፈጸምባቸው ቤተሰቦችና የአከባቢ ሰዎች እንዲሁም ሰብኣዊነት የሚሰማው ሰው ሁሉ የሚሰጡትን ምላሽ ጠብቁ። ተስፋ መቁረጥ በስህተት ለማረም መሞከሩ ከንቱ ነው። ይህ የመጀመሪያ መጨረሻ እንደሆነ ተገንዘቡ።