Page 1 of 1
Breaking: US and Kenya to resume military training from July in policy shift
Posted: 31 May 2021, 08:39
by Thomas H
Bye Bye $hithiopia
The US considers Kenya not Ethiopia a "strategic" partner in the fight against terrorism in Africa.
Source:
https://nation.africa/kenya/news/us-and ... 4MOkURAG2s
Re: Breaking: US and Kenya to resume military training from July in policy shift
Posted: 31 May 2021, 09:16
by Thomas H
WOW!
John Sphere
May 29 at 8:15 PM ·
ሀገራችን እንደ አሁን መሪ አልባ የቀረችበት ግዜ የለም። አሜሪካ ማእቀብ ስትጥልብን ለምን ይህ ሆነ እንዴት ይሄን መቀልበስ ይቻላል ። ማእቀቡስ ምን ጉዳት ያመጣል ። በነገራችን ላይ አሜሪካ ማእቀብ የጣለችባቸው ጠንካራ ኢኮኖሚ ያላቸው ኢራን እና ራሽያ እንኳን ሳይቀሩ ተሽመድምደዋል። እኛ ስንሆን ደግሞ ማሰብ ነው። ስለዚህ ይህን ተንትኖ የአሜሪካንን ሀሳብ የሚያስቀይር ከሙህር እስከ ታዋቂ ሰው ታስክ ፎርስ አቋቁመህ መሞገት እና ማባበል ሲቻል ጠቅላዩ ጭራሽ እኛ በቀይ ባህር ላይ ሊኖረን ስላለው ተፅኖ ደንፎ ይዟቸው ነው፣ እኛ ተንበርክከን አናቅም ወዘተ ድንፋታ የሽመልስን እዚህ የማልጠቅሰው ከእርሱ አእምሮ ከዚህ በላይ ስለማልጠብቅ ነው ። በሽመልስ ንግግር የሳቁት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጉዳይም በዲፕሎማሲ መስክ ሌላ ማኖ ነው። በአጠቃላይ በአብይ አቅም ማነስ ምክንያት ኬንያ ከግብፅ ጋር ወታደራዊ ስምምነት አድርጋለች፣ በእኛ ውሀ እና ጫት እንዲሁም ወደብ ክራይ በምንደጉማት ብራችን የምትኖረው ጅቡቲ እንኳን በአብይ ምክንያት ሀገራችንን በመናቅ ከግብፅ ጋር ስምምነት ደርሰዋል፣ ሱዳን ሰባ ኪሎ ሜትር የጎንደርን መሬት መያዟ አልበቃ ብሏት ቤንሻንጉልም የኔ ነው ብላለች ። እንግዲህ ይህ ሰውየ ወይ የለየለት ወፈፌ ከሆነ ፀበል ይግባ ካላመመውም በአለማችን ትንሹ የአይ ኪው ባለቤት የሀገር መሪ ተብሎ ሙዚየም ውስጥ ይቀመጥ ። ሀገራችን ግን በእርሱ ምክንያት ስትፈርስ ቁመን አናየውም። በእርሱ ምክንያት በሀገራችን ከቡራዩ እስከ ትግራይ ፣ ከወለጋ እስከ ቤንሻንጉል ደም ፈሷል። ይህም ይሁን ነገ ያልፍ እና ሀገር ይረጋጋ ይሆናል ስንል ጭራሽ ከአለም ነጥሎ ቁጭ አደረገን። እንኳን እኛ ችጋራም ቀርቶ የዳቦ ቅርጫት ትባል የነበረችው ዝሙባቤ እንኳን ማእቀቡ ባሳደረባት ጫና ምክንያት ዜጎቿ አንድ ዳቦ ለመግዛት በጆንያ ብር ይዘው ሲሄዱ ተመልክተናል። እናም ዝም ያላችሁ ሙህራኖች ይህን የተሳሳተ የመንግስት አካሄድ መላ በሉት። የአሜሪካንን እና አውሮፓውያን ማእቀብ በሰልፍ አንመልሰውም። በሉአላዊነታችን አንደራደርም ግን ደግሞ ነገሮችን እያቀጣጠልን በራሳችን ላይ ቀንበር አናከብድም። እኔ የምኖርባት ካናዳ እንኳን ዘጠና በመቶ ንግዷ ከአሜሪካ ጋር ነው። ያለአሜሪካ መተንፈስ አትችልም። እናም የአሜሪካ ማእቀብን እንደ ግብፅ ማስፈራራያ አቅልሎ ማየት ነገ ዋጋ የሚያስከፍለው የሀገሬን ገበሬ ነው። እናም መንግስት ሆይ ተኝተህ በመክረምህ ያመጣሀውን ማእቀብ ዛሬም ከእንቅልፍህ ነቅተህ እንዴት መመከት እንዳለብህ ማሰብ ሲገባህ በባዶ ሜዳ በሉአላዊነት ካባ ተጀቡነህ ዘራፍ ብትል የምትዘርፈው አንዳች ዶላር የለም።