Page 1 of 1

የሑመራው ሓኪም ማስታወሻ

Posted: 30 May 2021, 19:07
by sarcasm
የሑመራው ሓኪም ማስታወሻ
ክፍል 1
እኔ ሓኪም ነኝ። የህወሓትም የብልፅግናም ደጋፊ ባልሆንም ውሸትን ግን አብዝቼ እፀየፋለሁ።

ማስረጃ 1 ፡ ኤርትራ በጥቅምት 30/2013 እና በሕዳር 1/2013 ዓ.ም በከባድ መሳርያ ሑመራ ከተማን ደበደበች። በዚህ ስራዋም በርካታ ንፁሃን የከተማዋ ነዋሪ ፈጀች። በተጠቀሰው እለት ማለትም ጥቅምት 30/2013 ምሽት አደባይ የምትባል ከሑመራ በ 18ኪ.ሜ ርቀት የምትገኝ የምዕራብ ትግራይ ከተማ የኤርትራ ሰራዊትገባ።

ማስረጀ 2 ፡ ሕዳር 5/2013 ዓ.ም ትግራይ ወደ አስመራ ኤርፖርት ሮኬት ተኮሰች። ለምን ተኮሰች? ሕሊና ላለው መልሱ ቀላል ነው።
ሲጠቃለል ኤርትራ የተተኮሰባት ትግራይን ለቃ እንድትወጣ ነበር። እነ እንትና እንደሚሉት ኤርትራ ተተኩሶባት ሳይሆን ቀድማ ነው የገባችው።
በወቅቱ እሰራበት የነበርኩበት ሑመራ ሆስፒታል እና መኖርያ ቤቴ የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል።
..............
ለምን ይዋሻል????? የኢ/ያ ህዝብ ሆይ አስተዋይ ልቦና ይስጥህ እንጂ ሑመራ ሆስፒታልን ለቅቄ እስከ ወጣሁበት መጋቢት 25/2013 ዓ.ም ድረስ የነበሩ እውነታዎችን ሳንጨምርና ሳንቀንስ በቦታው ሆነን በኣካል ያየነውን እናቀርባለን።

ፍርዱንም ላንተ እንተውልሀለን።

ክፍል 2
የሑመራ አጠቃላይ ሆስፒታል ሰራተኛ ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ በከፍተኛ የሙያ ስነምግባር በጦርነቱ የተጎዱ የሀገር መከላከያ ወታደሮች እና የትግራይ ልዩ ሓይል አባላት ያለ ምንም ልዩነት እግዚአብሔር በሰጠው እውቀት ሲያክም ቢሰነብትም ጥቅምት 30 /2013 ዓ/ም ግን ኤርትራ በተለምዶ ኹዳር ገበያ፣ማርያም ቤተክርስቲያን እና መስጊድ ተብለዉ የሚታወቁ የቀበሌ ሁለት መንደሮች በከባድ መሳርያ ስትደበደብ በመዋሏ ንፁሃን የከተማዋ ነዋሪዎች እንደቅጠል ረገፉ። ሆስፒታላችንም በደም ጎርፍ ታጠበ፣ እናቶች ለራሳቸው ቆስለው የሞቱም በከፍተኛ ሁኔታ የተመቱም ህፃናት ልጆቻቸውን አዝለው የሀኪም ያለህ ሲሉ ይምፀናሉ። ምስኪኑ ሓኪምም የሚይዘው የሚጨብጠዉ አጣ። የቱን ላስቀድም የትኛውንስ ቅድሚያ ባክም ላድነው እችላለሁ በሚል ሕክምናዊ ሳይንስ አቅሙ በፈቀደለት ፍጥነት ከግዜ ጋር ትንቅንቁን ተያይዞታል። ተጨማሪ 4 የድንገተኛ መታከሚያ ማእከላት በመክፈት ሰርጂኑ፣የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስቱ ፣ አዋላጅ ሀኪሙ ፣ ጠቅላላ ሀኪሙ ፣ ላቦራቶሪስቱ፣ ፋርማሲስቱ፣ ነርሱ፣ አስተዳደሩ፣ ፅዳተኛ፣ ዘበኛው ሁሉ የሚግባቡት በአንድ ቋንቋ ነው። የከተማዋ ነዋሪ ሳምንቱን ሙሉ ቆስለዉ እየታከሙ ለነበሩት መከላከያ እና ልዩ ሓይል አባላት የሚያመጣዉን ጁስ አብረን እየጠጣን ሳምንቱን ሙሉ (24/2/2013- 30/2/2013) እያከምን ብንቆይም ጭፍጨፋው ያስደንገጠው ምስኪኑ ሕዝባችን ስደት ብቸኛ ሕይወቱን የማዳኛ አማራጭ ሆነ።

ሱዳን ከሑመራ የአንድ ሰዓት የእግር ጉዞ ቅርብ ነች። ነገር ግን ድንበር ላይ ትልቅ ወንዝ አለና እሱንም የሚያሻግር ሰው ያስፈልጋል።
የሆነስ ሆነና ህፃናት፣ እርጉዝ ሴት፣ ከተጋቡ ገና ሳምንት ያልሆናቸው ሙሽሮች፣ ብቸኛ ልጃቸውን የተነጠቁ ሽማግሌዎች፣ በየመንገዱ ያለቀባሪ የወደቁት ንፁሃን ዜጎችን በአይኑ አይቷልና የኤርትራ መድፎችም ተጠናክረዉ በመቀጠላቸው ሕዝባችን አስከፊዉን የስደት ፅዋ መጎንጨት መረጠ።

በዛች እለት አመሻሹ ላይ በሆስፒታሉ ድንገተኛ ክፍል አብረዉኝ ደፋቀና ሲሉ የዋሉት ሀኪሞችና ነርሶች አጠገቤ አለመኖራቸውን ያስተዋልኩት ቁስለኛ በዝቶብኝ አጋዥ ፈልጌ ቀና ያልኩ ግዜ ነበር። ምርመራዎች እና መድሓኒቶች ደም ጭምር ቢያስፈልጉኝም ላቦራቶሪና ፋርማሲ ተዘግተዋል። ማታ 3፡30 ከነበርኩበት ክፍል ወጣ ብዬ እየሆነ ያለውን ስመለከት የሆስፒታል ሰራተኛ አደባይ ወደ ምትባል ከተማ እየተሰደደ ነው። በሐሳብ ብዛት ትካዜ ውስጥ እንዳለሁ አንዱ ጓደኛዬ ሓኪም አይቶኝ "ፋንትሽ ና መኪና ውስጥ ግባ እንሂድ" ሲለኝ በድንጋጤም በፍርሃትም ተውጬ አይ እናንተ ሂዱ እኔ እዚሁ አድራለሁ ነገ የከፋ ነገር ከተፈጠረ መጥተህ ውሰደኝ ብዬው ተለያየን። እንዳልሄድ በሞትና በህይወት መካከል *ሾክ* ውስጥ ያሉ ታካሚዎች ይሞቱብኛል። ሌሎችም ደም እሚፈሳቸው ቁስለኞች ነበሩኝና ቁስላቸዉን መስፋት ነበረብኝ። ድግነቱ የውሃ ምግብም ሆነ ለመስፊያነት የሚያገለግል መሳርያ ነበረኝ።

ከሁሉም በላይ ደረታቸው ላይ ደምና አየር የተጠራቀምባቸው(haemopneumothorax) በሽተኞችን ሰርጅን ባለመኖሩ በብቸኝነት ከፅዳት ሰራተኛ ጋር በህይወት የደረት ቱቦ (chest tube) ለመስራት የተገደድኩበት ግዜ ነበር።

ሕዳር 1/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 12፡00 አንድ መሳርያ ድንገተኛ ክፍል አካባቢ ያረፈች መሳርያ ካሸለብኩበት የበሽተኛ አልጋ አነቃችኝ እናም ደህና የሆኑትን ከሆስፒታሉ አስወጥቼ ዶክመንቶቼን ለማምጣት በሩጫ ወደ መኖርያ ቤቴ ሄድኩኝ።

መንገድ ላይ እያለሁ ሻዕቢያዎች መድፋቸውን ማዝነባቸዉን አጠናክረው ቤት ስደርስ ታሪክ ተቀየረ። የቤቴ መስተዋቶች መርገፍ ጀምሩ። ሰፈሬ በመድፍ መታረስ ጀመረች። ግቢው ሰዉ የለውም ። ምይዘው ምጨብጠው አጣሁ አጠገቤ ወዳለው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን እንዳልሄድም
ቤተክርስቲያን አካባቢ እየተደበደበ ነው።

ቢጨንቀኝ ጎረቤት ግድግዳ ላይ ከተሰቀለቺው የቅድስት አርሴማ ስዕል ስር ተደፍቼ ንስሃ ጀመርኩኝ።
በድንገት ነገሮች ተለወጡ። ...
.....................
ምን ተፈጠረ?
በቀጣይ ክፍል
*ጉዞ ወደ ራውያን
* ከራዉያን መልስ...ሆስፒታል
* የ22 ሬሳዎች ጉዳይ
*ሆስፒታሉና ያሳለፍኩዋቸው ፈተናዎች
*ረሃብ
* የሕዝብ ሰቆቃ፣እስር፣ተጠናክሮ የቀጠለዉ ስደት፣የሕዝብ ሀብት ዘረፍ፣ ጭካኔያዊ ግድያ እና አስገድዶ መድፈር እናያለን። የነገ ሰዉ ይበለን።


ክፍል 3
በዚህ ክፍል
* ትረፊ ያላት ነብስ ጉዞ ወደ ራውያን
* ከራዉያን መልስ...ሆስፒታል፣
* የድንበር የለሽ ሃኪሞች ቡድን MSF አስተዋፅኦ በሆስፒታላችን፣
* የውሎ አበል፣ምግብ፣ደሞዝ የሚከፈላቸው ሰራተኞች እና በረሃብ አለንጋ እየተገረፉ ስለ ሕዝባቸው ብለው ሁሉን ችለው እየሰሩ ስለነበሩ ሙያተኞች፣
* 2 ወር ሙሉ ለህዝብ ሲባል በበሶ እና ቆሎ የታለፉ ግዜያቶች፣
* ጁንታው እና ፋኖው ሀኪም በማንና ለምን ተባለ፣
* 135 ብር የፈጠረችው ደስታ፣
* በችግር ግዜ የደረሱ ወዳጆች፣
* ብቸኝነት በሆስፒታል
* የ22 ሬሳዎች ጉዳይ
*ሆስፒታሉና ያሳለፍኩዋቸው ፈተናዎች
*ረሃብ
* የሕዝብ ሰቆቃ፣እስር፣ተጠናክሮ የቀጠለዉ ስደት፣የሕዝብ ሀብት ዘረፋ፣ ጭካኔያዊ ግድያ እና አስገድዶ መድፈር ፣
* ኮሮና መመርመርያ PCR ማሽን መንግስታዊ ስርቆት፣
* የእስር ሙከራዎች፣
* 6 የግድያ ሙከራዎች ፣
* ስልታዊ መፈናቅሎች፣
* ስልታዊ ግድያዎች፣
* ሰራተኛውን ለመታደግ ከሁለት ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊዎች እስከ ጤና ሚ/ር ሀላፊዎች ጋር የተደረጉ ውይይቶችና ውጤታቸው፣
* የኢ/ያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ጋር ያደረግኳቸው 2(ሁመራ ላይ እና አዲስ አበባ ላይ) ቃለ መጠይቆች ፣
* የሆስፒታሉን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ከ WHO, UNICEF, ICRC, IMC እና MSF ጋር የተሰሩ ስራዎች፣
* ያልተሰማው የማይካድራ ጉድ፣
* ተአምረኞቹ መንታ ህፃናት፣
* በዘግናኝ ግድያ በረሃ ተወስደው ከተረሸኑ ገበሬዎች መካካል ሳምንት ሙሉ ሽንቱን እየጠጣ በህይወት የተረፈዉ ገበሬና መጨረሻዉ፣
* የ131 ሰዎች ሚስጥራዊ ግድያ፣
* ዲቭዥን እና የደረሰባት ሰቆቃ፣
* የቤት ወረራ፣
* ሰሊጥ፣ ማሽላ፣ጥጥ፣ እንስሳት፣ ዘመናዊ የእርሻ መሳርያ ማሽኖች፣ ተሽከርካሪዎች ማን ዘረፋቸው? ወዴትስ ተወሰዱ?
* በየመንገዱ የወለዱ እናቶች ጉዳይ፣
* ኮማንድ ፖስቱና በማታ የሚወልዱ እናቶች ችግር፣
* የመጨረሻዋ ሰዓት በሑመራ...... እነዚህን ለመፃፍ ብዕሬን ባነሳሁ ቁጥር እንባዬ ኩልል እያለ ሲወርድ ስሜቴን እየረበሸኝ በመቸገሬ ማስታወሻዬን አጣጥፌ ማስቀመጥን መረጥኩኝ...... ተረጋግቼ እመለስበታለሁ።

https://www.facebook.com/fantayegm/post ... 6967718449

Re: የሑመራው ሓኪም ማስታወሻ

Posted: 30 May 2021, 20:16
by Tog Wajale E.R.
We Put The Dedebit Woorgach Agga*me Tigrayian Back To Stone Ages.

Bissbiss Shettattam Agga*me Mighty Amara People Will Rule Tigrai Next 1000 Years To Come. Go Figure Bissbiss Shettattam Agga*mes.
We Are Not Done Yet Until We Make Tigrai Like Aleppo Syria. Go Figure.