ሰውዬው የብልፅግና ወንጌል አቀንቃኝ፣ በዋሽንግተን C-Street የሚገኝ ዕድሜ ጠገቡ "The Family" የተሰኘው የፕሮቴስታንታዊ ፋሺዝም የረጅም ጊዜ ዘዋሪና አባል የሆነ ሲሆን፥ የብልፅግና ወንጌልን ለማስፋፋት የሀገራት መሪዎችን እየመለመሉ በራሳቸው አስተምህሮ የሚያጠምቁ ናቸው።
ሰውዬው በ2018 ዓ.ም በኮንግረስ ተገኝቶ ከአብይ ወደ ስልጣን መምጣት በኋላ HR. 128 በኢትዮጵያ እንዳይተገበር ሲሞግት እንደተናገረው ፥አብይ አህመድን በ2016 ዓ.ም በ leader's breakfast በአካል እንዳገኘው ይገልፃል። Leader's Breakfast የሚባለው በዚሁ The Family በሚባለው ድርጅት የሚዘጋጅ አመታዊ event ሲሆን በመደበኛ አጠራር National Prayer Breakfast ይባላል።
ኢንሆፍ እንደሚለው አብይ አህመድ በ2016 ዓ.ም ማለትም ወደ ስልጣን ከመምጣቱ ሁለት ዓመት ቀደም ብሎ፥ በዚህ ዝግጅት በተገኘበት ወቅት ለኢንሆፍ "በጌታ የኖረበት የህይወት ጉዞውን" ተርኮለታል።
በአመቱም ማለትም በ2017 ዓ.ም አብይ አህመድ ወደስልጣን ከመምጣቱ አንድ አመት ቀደም ብሎ በድጋሚ ተገናኝተው፥ "ሀገሪቱን በሠላማዊ መንገድ እንዴት Unify ማድረግ እንዳለባቸው" መወያየታቸውን ይገልፃል።
እንግዲህ በ2018 ዓ.ም አምባሳደር ያማማቶ አብይ አህመድ ካልተመረጠ ሞተን እንገኛለን ብሎ አብይን ወደ ስልጣን ያመጡት፥ ከ2016 ዓ.ም ምናልባትም ከዚያም ቀደም ብሎ፥ የዚህ The Family የተሰኘው የብልፅግና ወንጌል ፋሽስታዊ ፅንፍ መልምሎ ለተልዕኮ ሲያዘጋጀው ለመኖሩ ጠቋሚ ነው።
ጂሚ ኢንሆፍ ዛሬ የሚያላዝነው ለሀገሪቱ ተጨንቆ ሳይሆን፥ ኮትኩቶና ተልዕኮ ሰጥቶ የቀባው ተላላኪው አብይ አህመድ አንገት ላይ የባይደን አስተዳደር የማነቂያ ሸምቀቆውን አጥልቆ፥ ወንበሩን ከእግሩ ስር አንስቶ ግብዓተ-መሬቱን እውን ሊያደርግ ስለተቃረበ ብቻ ነው።
የአማራን ፖለቲካ ለኦሮሙማው ፋሽስታዊ ቡድን የስልጣን ማደላደያ አድርጎ ላቀረበው አማርኛ ተናጋሪው የኦሮሙማ ጉዳይ አስፈፃሚው ቡድን አንድ መልዕክት ማስተላለፍ ግድ ይላል። እናንተ ሆድ እንጂ ማሰቢያ ጭንቅላት ስለሌላችሁ ከተረትና በምናባችሁ ከሳላችሁት የቁም ቅዠት ውጪ መኖር አትችሉም። ለዚህም ነው "ሪፐብሊካኖች ደግፈውናል" ብላችሁ በሌለ ነገር መከረኛውን ህዝብ እያደናገራችሁ ያላችሁት። አብይን እንጂ ሀገሪቷንም እናንተንም ደግፎ አይደለም ያ ያረጀ ሴናተር ብቻውን እየጮኸ ያለው። እሱም ለብቻው የሚያላዝነው፥ ጉዳይ ያስፈፅምልኛል፣ የብልፅግና ወንጌልን (Prosperity Gospel) ያስፋፋልኛል ያለውና የደከመበት ደቀመዝሙሩ በአለማቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ አይንህ ለአፈር ስለተባለበት፥ የመጨረሻዋን የቀብር አፈር በእጁ ዘግኖ እየወረወረ ሟች የአብይ አህመድ መንግስትን እየተሰናበተ ነው። በሀይልና በሸፍጥ በአማራ ጫንቃ ላይ ለዘመናት መኖራችሁ ሳያንስ፥ የአማራን Cause ለትራፊ ለቀማ የደጅ መጥኛ ስላደረጋችሁት፥ አማራ በታሪኩ አይቶት የማያውቀውን ውርደት አከናንባችሁታል። እናንተ እስካላችሁ ድረስ የትኛውም የአማራ መከራ እንደማይወገድ፣ የተስፋ ጭላንጭል ታይቶበት የነበረ ድል መሳይ ነገር ሁሉ እንደሚባክን ግልፅ እየሆነ መጥቷል።
ከጠላት ጋር ያልተሰለፈው የአማራ ልሂቅና በጠቅላላው ህዝቡስ ቢሆን፥ በጥቂት የባንዳ ስብስብ ምክንያት ዳግም 1983ን ለመድገምና ሁሉን ሊያጣ በጫፍ ቆሞ ሳለ፥ የራሴን አጀንዳ ከተለጣፊነት አዙሪት አውጥቼ በራሴ መንገድ አስኬደዋለሁ ማለት እንዴት አቃተው⁉
ዴቭ ዳዊት።


Please wait, video is loading...