እነ ጃዋር መሐመድ "ፆመ ትግራይ" ሊፆሙ ነው - የረሃብ አድማው በትግራይ ክልል እየታየ ያለውን “የጅምላ ግድያና ኢ-ፍትሃዊ አገዛዝ ለመቃወም” ነው ሲሉ በችሎት ተናገሩ
Posted: 26 May 2021, 11:24
እነ ጃዋር መሐመድ ከዛሬ ጀምሮ ፍርድ ቤት መቅረብ አንፈልግም አሉ
“እኛ እዚህ የመጣነው ከተፈረደብን ለመቀጣት፤ ነጻ ከተባልን ለመውጣት ነው” ያሉት አቶ ጃዋር፤ “ከዛሬ ጀምሮ በገዛ ፍቃዳችን ፍርድ ቤት አንቀርብም” ሲሉ ለፍርድ ቤቱ አስታውቀዋል። ይህንን ውሳኔ ደግፈው የተናገሩት አቶ በቀለ ገርባ በበኩላቸው “በግድ ተጎትተን እና ተደብድበን ካልሆነ በቀር ወደዚህ ፍርድ ቤት አንመጣም” ሲሉ ተደምጠዋል።
አቶ ጃዋር ወደ ፍርድ ቤት ላለመምጣት መወሰናቸውን ከማስታወቃቸው በተጨማሪም በትግራይ ክልል እየተከሰተ ላለው ሁኔታ የትግራይ ህዝብ የረሃብ አድማ ላይ በመሆኑ፤ እነርሱም ለሁለት ቀናት ምግብ እንደማይበሉ ተናግረዋል። የረሃብ አድማው በትግራይ ክልል በትግራይ ክልል እየታየ ያለውን “የጅምላ ግድያና ኢ-ፍትሃዊ አገዛዝ ለመቃወም” መሆኑን ተከሳሹ አስረድተዋል።
Read the artice at Ethiopia Insider https://ethiopiainsider.com/2021/3350/