Page 1 of 2
ሕዝብ የሚለው ቃል ከየት መጣ?
Posted: 25 May 2021, 02:23
by Horus
ቃል ብርሃን ነው፣ ቃል መብራት ነው!
እስቲ አንዳንድ በድንቁርና ላይ ቆመው ያሉ ቃላትና ጽንሰ ነገሮችን እናጣራ ።
የ'ሕዝብ' ስረቃል...
ቃሉ ሲጀመር የጥንታዊ ቀምጥ ወይም ቆጵት ነው። በዚያን ዘመን 'ከብ' ብሎ ይጀምራል ። 'ካ' በግብጽ ያንድ ነገር መንፈስ፣ ምስል፣ ወይም ዛሬ ጎስት፣ ኢሜጅ የምንለው ነበር። 'ባ' በግብጽ ህይወት፣ ህያው ማለት ሲሆን ዛሬ በላቲን 'ባዮ' የሚባለው ነው። በአነባበብ ደረጃ ግብጾች እንዴት እንዳሉት አሁን ተረስቷል። ስለሆነም አናባቢ የሌለው 'ከብ' አንድ ሰው ማለት ነበር።
'ከ' በድምጽ ሺፍት 'ሸ'፣ 'ሰ' ይሆናሉ ልክ ጠ፣ ጨ እንደ ሚሆነው ። ስለሆነም 'ሸብ፣ ሰብ' ዛሬም በሴምና በላቲን ውስጥ አሉ። ለምሳሌ ሆሞ ሴፒየን በሚለው የሰው ልጅ መጠሪያ ውስጥ ያለው ሴፒየን ሰብ ከሚለው የተወረሰ ነው ። ሰብ ማለት በኢትዮጵያ አብዛኛው ቋንቋዎች ሰው ማለት ነው።
በጉራጌኛ ሰው በቀጥታ ሰብ ይባላል። ቤተሰብ ስንል ቤተሰው ወይም የሰው ቤት ማለታችን ነው። ሰብ ወይም ሰው አንድ ግለሰብ ነው ።
በ ግዕዝና አረብኛ ሰብ ከሚለ ነጠላ ስም 'እስብ፣ ህዝብ' የብዝህ ስም ተቀዳ። በመሰረቱ ብዝህ፣ ብዙ ማለትም ከዚያ የተቀዳ ነው።
በአጭሩ ሕዝብ ማለት ሰብ ለሚለው ነጠላ ስም ፕሉራል ስም ነው ። ሕዝብ ማለት ብዙ ግለሰቦች ማለት ነው ። እንዲያውም በጉራጌ ቋንቋ ሕዝብ ማለት ሰቦች ነው የሚባለው። ብዙ ሰብ ሰቦች ይባልሉ። ብዙ ሰው ሕዝብ ይባላሉ ።
የድንቁርና ስህተቶች
ብሄረሰብ የሚለው ቃል ስህተት ነው ። ብሄረ ሰብ አንድ የብሄር ግለሰብ ማለት እንጂ ያንድ ብሄር ብዙ ሰቦች ወይም ሰዎች ማለት አይደለም ። ይታረም !
ሕዝቦች የሚለው ቃል ደደብ ነው ። ሕዝብ ብዙ ወይም ፕሩላር ስም ነው ። ስለዚህ ድጋሚ ብዝህ ቃል ነው ። ልክ መጻፍት ብዙ ነው ። መጻህፍቶች ደደብ ነው ።ድጋሚ ማብዛት ነው።
ስለዚህ ብሄረሰብ ማለት አንድ ሰው ብቻ ነው የሚጠራው።
ሕዝቦች የሚለው ቃል ፍጹም የድንቁርና አባባል ነው ። ሁለቱም ይታረሙ
የኢትዮጵያ ሕዝቦች የሚሉ ደንቆሮች ናቸው ። ያሉት የኢትዮጵያ ሕዝብ ወይም የኢትዮጵያ ሰቦች ናቸው ።
ሕዝብ ብዙ ሰው፣ ብዙ ሰብ፣ ሰቦች፣ ሰዎች ማለት ነው !!
Re: ሕዝብ የሚለው ቃል ከየት መጣ?
Posted: 25 May 2021, 03:50
by Fiyameta
In Eritrea we say ህዝቢ ኤርትራ። We don't say ህዝብታት ኤርትራ, which is not only grammatically incorrect, but sounds very silly. In fact, out of curiously, I try saying "ህዝብታት ኤርትራ" several times, and it sounds so offensive to my ears each time I say it, not to mention vulgar!
Re: ሕዝብ የሚለው ቃል ከየት መጣ?
Posted: 25 May 2021, 04:10
by Horus
Fiyameta wrote: ↑25 May 2021, 03:50

አው ህዝብታት ቢባል የብዙ ብዙ ስለሚሆን ስህተትነው ። ህዝቢ (የህዝብ ቅጽል፣አጀክቲቭ ነው) Hizb is already a plural form of Seb.
Re: ሕዝብ የሚለው ቃል ከየት መጣ?
Posted: 25 May 2021, 04:14
by Noble Amhara
Horus
Amhara Nen Music (for retarded agame የቡና ቤቶች gossipers its sung here as Amara Hizboch)
Amhara is the size of Romania so we are የአማራ ሕዝቦች because we are far away from each other and we don’t know Every particular group of Amhara so we are united by our Habesha Race so when we are together in one location we become የአማራ ህዝብ for example it’s offensive to say ye bahirdar amara hizboch compared to yeBahir Dar Amhara Hizb the name hizboch for Amhara is only used for the Kilil not Awrajas, Woredas, Ketemas and Kebeles it is offensive to use the term ሕዝቦች for zones and districts of Amhara where we are one people it is offensive and angering to use hizboch on zones of Amhara it is only allowed for our large Kilil
Re: ሕዝብ የሚለው ቃል ከየት መጣ?
Posted: 25 May 2021, 04:22
by Masud
Horse came up with his usual confusion. The peoples of Ethiopia are neither like the people of Somalia who speak the same language and have simliar psychological make up nor like the people of America which are the collection of immigrant individuals. The peoples of Ethiopia, I am saying peoples, are the collection of people who have distinct charateristis, language, culture and value. Unless Ge'ez and amharic are dead language, they will be transformed like any other language. They shouldn't be stuck in the past like Horus. The word Hizb is not engraved on stone.
Tigres who are the inentors and owner of Ge'ez accepted the word Hizboch. The Uragies and Neftegnas has no say on this. The Bashasha Arada came up with an alternative word Hizb copying from Lidetu and Temagn Beyene to confuse Amharas and get vote for his party. As ususals, the Uragies who are the shadoe of Amhara are tryng to justify Amharas confusion. Uragies are YePoletika Shermutoch nachew.
Re: ሕዝብ የሚለው ቃል ከየት መጣ?
Posted: 25 May 2021, 04:23
by Abe Abraham
Fiyameta wrote: ↑25 May 2021, 03:50
In Eritrea we say ህዝቢ ኤርትራ። We don't say ህዝብታት ኤርትራ, which is not only grammatically incorrect, but sounds very silly. In fact, out of curiously, I try saying "ህዝብታት ኤርትራ" several times, and it sounds so offensive to my ears each time I say it, not to mention vulgar!
The dead Junta was trying to inculate the use of "ህዝብታት ኤርትራ" into the minds of its buchilawoch just like it did with the unsuspecting Ethiopians with regard to " የኢትዮጵያ ህዝቦች " in its vicious scheme of divide and rule. Woyane was never interested about ethnicities or social justice.
Re: ሕዝብ የሚለው ቃል ከየት መጣ?
Posted: 25 May 2021, 04:31
by Horus
Noble Amara
ነገሩን እንደ አሻህ ብታረገው ትክክለኛው ቃል ሕዝብ ብቻ ነው። አማራው የትም ሆነ የት በብዛት አማራ ባለበት ሁሉ የሚባለው ያማራ ሕዝብ ብቻ ነው! የሸዋ አማራ ሕዝብ፣ የሃረር አማራ ሕዝብ። የወሎ አማራ ሕዝብ፣ የደጀን ወይ የንፋስ መውጫ አማራ ሕዝብ ነው ትክክለኛው ቃል። ሕዝቦች የሚባል የተሳሳተ ቃል ነው ። በዘልማድ ተብሎ ይሆናል፣ ግን ዛሬ ትክክለኛ አማራኛ መናገር የሚሹ ሕዝቦች ሊሉ አይችሉም
ሌላው ቀርቶ ግዕዙ እጅግ ብዙ ሕዝብ ለማለት ሕዝብ አሕዛብ ይላል ። ያ ማለት ግን የህንድ አሕዛብ፣ ያለም አሕዛብ አያስብለንም። ያለም ሕዝብ፣ የህንድ ሕዝብ ነው የምንለው
Re: ሕዝብ የሚለው ቃል ከየት መጣ?
Posted: 25 May 2021, 04:35
by Noble Amhara
Horus wrote: ↑25 May 2021, 04:31
Noble Amara
ነገሩን እንደ አሻህ ብታረገው ትክክለኛው ቃል ሕዝብ ብቻ ነው። አማራው የትም ሆነ የት በብዛት አማራ ባለበት ሁሉ የሚባለው ያማራ ሕዝብ ብቻ ነው! የሸዋ አማራ ሕዝብ፣ የሃረር አማራ ሕዝብ። የወሎ አማራ ሕዝብ፣ የደጀን ወይ የንፋስ መውጫ አማራ ሕዝብ ነው ትክክለኛው ቃል። ሕዝቦች የሚባል የተሳሳተ ቃል ነው ። በዘልማድ ተብሎ ይሆናል፣ ግን ዛሬ ትክክለኛ አማራኛ መናገር የሚሹ ሕዝቦች ሊሉ አይችሉም
ሌላው ቀርቶ ግዕዙ እጅግ ብዙ ሕዝብ ለማለት ሕዝብ አሕዛብ ይላል ። ያ ማለት ግን የህንድ አሕዛብ፣ ያለም አሕዛብ አያስብለንም። ያለም ሕዝብ፣ የህንድ ሕዝብ ነው የምንለው
Horus
Yes we like Amhara use HIZB over the HIZBOCH the term signifies confusion and lack of knowledge of other Amharas, we Abysinnian Habeshas are one Hizb
Horus
Listen 2

Shewa (Minjar) Amhara and Welkait Amhara Music one close to Addis Ababa and the second by Eritrea this show Historically Amhara is one people spanning Awash Melash and Tekeze Melash
Re: ሕዝብ የሚለው ቃል ከየት መጣ?
Posted: 25 May 2021, 05:39
by Meleket
Re: ሕዝብ የሚለው ቃል ከየት መጣ?
Posted: 25 May 2021, 06:39
by Guest1
Horus
ከጥንት ጀምሮ ህዝቦች የሚለው ቃል ነበር። በአንድ አካባቢ የሚኖር የከተማም የገጠርም ህዝብ ይባላል። የገጠር ልዩ የሚያደርገው በአብዛኛው ተመሳሳይ ቋንቋ የሚናገሩ መሆናቸው እንዳለ ሆኖ። ወይ ጉድ!! ክክክክክ የአቴንስ ህዝብ ሲባል ሮማዊያንን ነበር። ባሪያዎቻቸውን በምን ስም ይጠሩ ነበር? ሮኦማዊያን? ይህ ይጣራ። የቃል አመጣጥን መናገር ብንችልም የድሮ ቃልን ለዛሬ ስንጠቀም የሚመሳሰል ነገር ስላለ ብቻ ነው። ከጊዜ ጋር የህዝብ ትርጉም የተለየ ትርጉም ሊኖረው ይችላል።
ቤተሰብ ማለት የሰው ቤት ማለት ከሆነ ቤተአውሬ የአውሬ ቤት ቤተብሄር የብሄር ቤት ሊባል? from the specific to the general. የሀረር ሰው ነው። የጅጅጋ ሰው ነው የአዲስ አበባ ሰው ነው ይባል ነበር። አይደለም። የዬት አገር ሰው ነህ? ክክክክ
ቤት ክልል አለው። የአውሬ ክልል ጫካ ነው። ብሄርስ? ቦታ አለው። ቤተሰብ ቦታ ይቀይራል። አውሬዎችም ምግብ ፍለጋ ጫካ ይቀይራሉ። ብሄረሰብ ግን ቦታ አይቀይርም? ሲቀይር ባህሪዩና ቋንቋውም ይቀየራል። አይደለም? ከጊዜ ጋር ሁኔታዎች ሲቀየሩ የቃል ትርጉም የተወሳሰብ ይሆናል። የድሮና አዲስ ትርጉም።
ህዝብም ብሄርም የፓለቲካ category ቃል ነው። ሰብ biology ነው። አይደለም? sub human የፓለቲካ ቃል ነው? ብሄረሰብስ የፓለቲካ ቃል ነው አይደለም? ቤተሰብስ? ነው? እና ህብረተሰብ ወይም ማህበረሰብ በአንድ ላይ የሚኖሩ ሰቦች ናቸው። ሰቦች በህብረት እየኖሩ ቋንቋ ፈጠሩ። ሌላ ቋንቋ ማለት ከሌላ ሰብ ጋር አብረው ማህበረስብ ሲፈጥሩ ብዙውን ጊዜ ቋንቋ ቀይጠው ወደ ህዝብ ይቀየራሉ። ብቻቸውን ከሌላ ሰብ ጋር ካልተቀላቀሉ ማህበረሰብ ሆነው ይቀራሉ። ስምም አላቸው። ጎሳ ክላን ትራይብ ይሄ አነጋጋሪ ነው? ክክክክክክ ህዝብ ብዙ ማለት ከሆነ ህዝቦች አላስፈላጊ ነው። ትክክል። ሁለት አገር ውስጥ የሚገኙ ህዝብና ህዝብ = የሁለት አገር ህዝቦች ናቸው። ግልጽ ነው።
የረሳሁት
የአማራ ህዝቦች የተባለበት ምክንያት ግልጽ ላይሆን ይቻላል። ግን አማራ ክልል የተባለውና ከተመደበለት ክልል ውጭ ያሉትን ለማካተት ከሆነ የአማራ ህዝቦች መባሉ ትክክል ነበር። ይህን ለማለት ካልሆነ ህዝብ ብዙ ሆኖ ሳለ ለክልሉ ህዝቦች ማለት አማርኛ ጠንቅቆ አለማወቅ ነው ክክክክክክክ ይህ ስህተት መሆኑን እያውቁና ለማሳነስ የአማራ ህዝቦች መኖራቸው መካድና ህዝብ ብቻ ነው ያለው አንድ ቦታ ነው ያለው ማለትም ትልቅ ስህተት ወይም ሌላ ድንቁርና ወይም የብሽሽቅ ፓለቲካ ይሆናል ። ተግባብተናል?
ጥያቄ ከ /ከ/ ቀ ወይም ኽ ከ/ኽ/ ሀ ይገኛል። /ሽ ሰ/ እንዴት?
Re: ሕዝብ የሚለው ቃል ከየት መጣ?
Posted: 25 May 2021, 06:44
by DefendTheTruth
Fiyameta wrote: ↑25 May 2021, 03:50
In Eritrea we say ህዝቢ ኤርትራ። We don't say ህዝብታት ኤርትራ, which is not only grammatically incorrect, but sounds very silly. In fact, out of curiously, I try saying "ህዝብታት ኤርትራ" several times, and it sounds so offensive to my ears each time I say it, not to mention vulgar!
Let's not confuse many things for the sake of political expediency.
Language is based on grammer, politics is based on convention and the two are not one and the same, in my view.
We have to differentiate between a collection and an individual (singular) entity. A set is a collection, while an element of the set is singular (if it is a set of singular elements).
A collection can't be pluralized, while a collection of collections shouldn't be singularized.
We can refer to the the Eritrean People from both sides (perspectives), like we do for every other people of this world.
In a given village there are a number of families (a collection of individual families), which doesn't mean at the end the single family is supposed to be called in plural. We also know that when we refer to a family, we don't mean an individual, rather refer to a collection.
If I am referering to the Eritrean people as a singular, with which I don't have a problem, and also refer to the people of Ethiopia in the same way but then there will be a grammatical confusion to flatly call the peoples of the two countries also the people (in a singular) of the two countries, with some sort of semantic confusion. we are refereing to two collections here, separated on the national boundary in this case.
And I don't think there is a rule to separate (sub-categorize) people only on national boundaries, if the issue at hand may necessiate this.
This description is in english and I don't think that the grammatical concept (foundation) that translates into Amharic or Tigrigna is different here
Re: ሕዝብ የሚለው ቃል ከየት መጣ?
Posted: 25 May 2021, 12:22
by Roha
Thank you Horus,
This is a very good discussion that a brilliant mind of your kind can only disect.
የ'ሕዝብ' ስረቃል...
ቃሉ ሲጀመር የጥንታዊ ቀምጥ ወይም ቆጵት ነው። በዚያን ዘመን 'ከብ' ብሎ ይጀምራል ። 'ካ' በግብጽ ያንድ ነገር መንፈስ፣ ምስል፣ ወይም ዛሬ ጎስት፣ ኢሜጅ የምንለው ነበር። 'ባ' በግብጽ ህይወት፣ ህያው ማለት ሲሆን ዛሬ በላቲን 'ባዮ' የሚባለው ነው። በአነባበብ ደረጃ ግብጾች እንዴት እንዳሉት አሁን ተረስቷል። ስለሆነም አናባቢ የሌለው 'ከብ' አንድ ሰው ማለት ነበር።
'ከ' በድምጽ ሺፍት 'ሸ'፣ 'ሰ' ይሆናሉ ልክ ጠ፣ ጨ እንደ ሚሆነው ። ስለሆነም 'ሸብ፣ ሰብ' ዛሬም በሴምና በላቲን ውስጥ አሉ። ለምሳሌ ሆሞ ሴፒየን በሚለው የሰው ልጅ መጠሪያ ውስጥ ያለው ሴፒየን ሰብ ከሚለው የተወረሰ ነው ። ሰብ ማለት በኢትዮጵያ አብዛኛው ቋንቋዎች ሰው ማለት ነው።
በጉራጌኛ ሰው በቀጥታ ሰብ ይባላል። ቤተሰብ ስንል ቤተሰው ወይም የሰው ቤት ማለታችን ነው። ሰብ ወይም ሰው አንድ ግለሰብ ነው ።
Re: ሕዝብ የሚለው ቃል ከየት መጣ?
Posted: 25 May 2021, 12:50
by Guest1
እንደ ዜግነት ማህበረሰብ people of a place አህል / አህል ሻዕብ በአንድ አካባቢ የሚኖር ሰው ዘመዳሞች ወይም ወዳጆች (ዝምድና ወይም ጉርብትና የፈጠሩ)።
society, nationality, people as in nation ኡማ / ሻዕብ / ኡማ ሻዕብ
people in general ናስ አናስ ይህ ሰብ ስው
specific አህል በአንድ አካባቢ የሚኖሩ (ቦታና ዝምድና) and general ብሄር/ ዜግነት ኡማ ሻዕብ ይህ ፓለቲካና ሶሻል እንበለው ቃል ነው። ናስ አናስ አጠቃላይ ሰብ = ሰው ነው ዝምድናም ቦታም ፓለቲካም የሌለበት።
ከግለሰብ ጋር ለማነጻጸር
The individual
በአረብኛ person = ናፋር/ ሻኻስ /ዋሂድ ዋሂዳ /ኢንሳን (@lissan masry_..Arabic dictionary online)
አንድ ሰው ናፋር ሻኽስ እከሌ? ዋሂድ...አንዱ አንዷ = አንድ ሰብ አንድ ሰው በእንግሊዝኛ አንድ ሰው a person /one person /the one አንዱ ለሰውም ለሌላም ነገር the book/ the one over there. etc
ምን ለማለት? በአንድ አካባቢ የሚኖሩ በደም የተሳሰሩም
ስብ = ሰው man
nation ብሄረሰብ ፓለቲካ
peoples ህዝቦች ፓለቲካ
people ህዝብም ፓለቲካ
በፓለቲካ አንድ ቃል እንደየጊዜው ፓለቲካ ትርጉም ይሰጠዋል።
ህዝብ ብዙ ስለሆነ ህዝቦች አይባልም? ስህተት ስህተት ስህተት!! kkkkk
የሁለት አገር ህዝብ = ህዝቦች፤ በክልል ደረጃም ህዝቦች ይቻላል (በአሁኑ ፓለቲካዊ ቢደረግም በአንድ ክልል ውስጥ ያሉ የተለያዩ ብሄሮችን ለመወከል)
የአማራ ህዝቦች ማለት ትክክል ብቻ ሳይሆን በጣም ትክክል ነው። ምክንያቱም በክልል መወሰን አትችልምና። በተለያየ ቦታ የሚኖሩትን ለመግለጽ የአማራ ህዝቦች!!! ይህን ስንቀበል አማራ ህዝብ እንጂ ህዝቦች አይደለም የሚለው ክርክር አለማወቅ ነው።
ahunis altegbabanim? wey gud!!
Re: ሕዝብ የሚለው ቃል ከየት መጣ?
Posted: 25 May 2021, 12:59
by Noble Amhara
Anta Doma Ras chegaru
Hizboch is the term that is used for Kilil
Hizb is the term that is used for Hager, Awraja, Woreda, Zone, Ketema, Kebele
If Amhara was a country we would say the Amhara Hizb instead of Hizboch which was brought by Ferenji Inspired TPLF as division and weakness
Abiy Ahmed is copying us when he says Ye Ethiopia Hizb a term we began to use during Italian invasions
Guest1 wrote: ↑25 May 2021, 12:50
እንደ ዜግነት ማህበረሰብ people of a place አህል / አህል ሻዕብ በአንድ አካባቢ የሚኖር ሰው ዘመዳሞች ወይም ወዳጆች (ዝምድና ወይም ጉርብትና የፈጠሩ)።
society, nationality, people as in nation ኡማ / ሻዕብ / ኡማ ሻዕብ
people in general ናስ አናስ ይህ ሰብ ስው
specific አህል በአንድ አካባቢ የሚኖሩ (ቦታና ዝምድና) and general ብሄር/ ዜግነት ኡማ ሻዕብ ይህ ፓለቲካና ሶሻል እንበለው ቃል ነው። ናስ አናስ አጠቃላይ ሰብ = ሰው ነው ዝምድናም ቦታም ፓለቲካም የሌለበት።
ከግለሰብ ጋር ለማነጻጸር
The individual
በአረብኛ person = ናፋር/ ሻኻስ /ዋሂድ ዋሂዳ /ኢንሳን (@lissan masry_..Arabic dictionary online)
አንድ ሰው ናፋር ሻኽስ እከሌ? ዋሂድ...አንዱ አንዷ = አንድ ሰብ አንድ ሰው በእንግሊዝኛ አንድ ሰው a person /one person /the one አንዱ ለሰውም ለሌላም ነገር the book/ the one over there. etc
ምን ለማለት? በአንድ አካባቢ የሚኖሩ በደም የተሳሰሩም
ስብ = ሰው man
nation ብሄረሰብ ፓለቲካ
peoples ህዝቦች ፓለቲካ
people ህዝብም ፓለቲካ
በፓለቲካ አንድ ቃል እንደየጊዜው ፓለቲካ ትርጉም ይሰጠዋል።
ህዝብ ብዙ ስለሆነ ህዝቦች አይባልም? ስህተት ስህተት ስህተት!! kkkkk
የሁለት አገር ህዝብ = ህዝቦች፤ በክልል ደረጃም ህዝቦች ይቻላል (በአሁኑ ፓለቲካዊ ቢደረግም በአንድ ክልል ውስጥ ያሉ የተለያዩ ብሄሮችን ለመወከል)
የአማራ ህዝቦች ማለት ትክክል ብቻ ሳይሆን በጣም ትክክል ነው። ምክንያቱም በክልል መወሰን አትችልምና። በተለያየ ቦታ የሚኖሩትን ለመግለጽ የአማራ ህዝቦች!!! ይህን ስንቀበል አማራ ህዝብ እንጂ ህዝቦች አይደለም የሚለው ክርክር አለማወቅ ነው።
ahunis altegbabanim? wey gud!!
Re: ሕዝብ የሚለው ቃል ከየት መጣ?
Posted: 25 May 2021, 13:21
by Horus
መለከት፣
መጀመሪያ ያንተን ልመልስ። እጅግ፣ እግጅ ትክክለኛ ማስተዋል ነው ያደረከው። ይህ እኔ ለ30 አመት የስረ (ስረው) ቃልና (ኤቲሞሎጂ) እና ስነቃል (ፊሎሎጂ) ለማግኘት ከምጠቀመው ሜቱሎጂ (መንገድ) አንድ ዋነኛው ነው ። ጉራማይሌ መንገድ ነው የምለው ለራሴ።
እሱም ያለው አንድ ቃል ከቀን ወደ ግራና ከግራ ወደ ቀኝ መባሉን፣ መጻፉን መመርመር ነው ። በዕልፍ የሚቆጠሩ ቃላት አፈጣጠራቸው እንደዚያ ነው ። ለምን ይህ ሆነ በለኝ?
በሁለት ምክኛቶች፡
አንዱ የሂሚራይቲክ ሳቢያዊ ቅድመ ግዕዝ ሲጻፍና ሲነበብ ዝግዛግ ነበር ። ማለትም አንዱ መስመር ከግራ ወደ ቀኝ ይጻፋና መስመሩ ሊያልቅ የሚቀጥለው መስመር ዝቅ ብሎ ከቀኝ ወደ ግራ ይጻፍ ነበር። ቆይተው የመጡ አንባቢዎች ይህን ሳያውቁ ከቀኝ ወደ ግራ የተጻፉትን ከግራ ወደ ቀኝ ማንበብ ገቡ ። በዚያ ሳቢያ ግማሾቹ ቃላት ልክ እንዳልከው በሁለቱም አቅጣጫ እየተጻፉና እየተነበቡ መጡ።
ለምሳሌ አለም የሚለውን ቃል ተመልከት? ጉራማይሌው መላአ (መላ፣ ሙሉ፣ በሞላ)፣ ሁሉም፣ ኦል ማለት ነው ። የሁለቱም ቃላት (አለም፣ መለአ) ትርጉም አንድ ሲሆን አጻጻፉ ግን ጉራማይሌ ነው ።
እርግጥ ሌሎችም ሰዎች የቃል ፊሎሎጂ የሰሩባቸው መንገዶች አሉ። ርዕሱ መጻፍ የሚያጽፍና አንድ ቀን በቋንቋ ምርምር ተቋም የሚሰራ ይሆናል፤ ይህ ጉዳይ በፍጹም በኢትዮጵያ ስለማይታወቅ ማለት ነው ።
አንድ ቃል እንደ ማንኛውን የካልቸር ምርት ታሪክ አለው ። እኛ በፍጹም የቃላት ታሪክ አናጠናም፣ኤቲሞሎጂ ማለት ነው ። እንዲሁም እያንዳንዱ ቃል የተቀመረበት ስነት (ስርዓት) አለው መለከት ማለትና መከለት አንድ አይደሉም። ይህን እኛ የትም ቦታ አናጠውም።
እስካሁን ያለን መዝገበ ቃላት (መግለጸ ቃላት ቢባል ነው ትክክል) ብቻ ነው ። መግለጸ ቃል (ዲክሽነሪ) አንድ ቃል ከሌላ መለያና ያንድ ቃል ይዘት (ትርጉም) በሌላ ቃል ወኪልነት የማወቂያ መንገድ እንጂ ስለ ቃሉ አመጣጥ ታሪክ ወይም ስለቃሉ ፈተላ ስነት አይነግረንም።
ይህ ደደብ የጎሳ ፖለቲካ ቀውስ ትንሽ ጋብ ካለ ይህን መሰል ጉዳዮች ላይ እናተኩር ይሆናል!
ኬር!
Re: ሕዝብ የሚለው ቃል ከየት መጣ?
Posted: 25 May 2021, 13:37
by Guest1
N B
ante chigram? እኔን ነው? እኔም መሳደብ አያቅተኝም። ተረጋጋ። ክክክክክ
Anta Doma Ras chegaru
Hizboch is the term that is used for Kilil
Hizb is the term that is used for Hager, Awraja, Woreda, Zone, Ketema, Kebele
from the specific to the general
ከቀበሌ ከፍተኛ/ወረዳ ከተማ አውራጃ ክልል ክልል ክልል ...= አገር
ህዝብ ህዝብ ህዝብ ህዝብ ህዝብ ህዝብ ህዝብ ////// አንድ አገር = ህዝብ
ስለዝህ ሁለት አገር ////// ህዝቦች
መደበላለቅ አይቻልም።
አማራ አንድ ህዝብ ነው። ግልጽ ነው።
from the specific to the general
በገጠር በከተማ በወረዳ በክልል ክልል ክልል... = በአንድ አገር
ህዝብ + ህዝብ + ህዝብ + ህዝብ + ህዝብ + ህዝብ ... = ህዝቦች።
እንደፈለግን መረዳት እንችላለን። ግን በአጠቃላይ ለማሳየት የተፈለገው ህዝብም ህዝቦችም የፓለቲካ ቋንቋ ነውውውውውው አራት ነጥብ!! ብዙ ክልል ያለውን ህዝብ በአንድ ክልል ብቻ አድርጎ ማስቀመጥ ፓለቲካ ወይም ድንቁርና ነው!! ስለዝህ ህዝቦች መባሉ ስህተት አይደለምምም እንዲያውም ትክክል!
ለክልል ህዝቦች ከተባለ ለአገርም ህዝቦች ነው። ስዋስዉ እንዴት ነው? ክክክክክክ
ስዎች ክፉ ናቸው = የሰው ልጅ ክፉ ነው። ሰው እና ስዎች ሁለቱም አጠቃላይ ናቸው። ማለት ሰዎች ብዛትን አያመለክቱም። ህዝብ በአንድ አካባቢ ህዝቦች በብዙ አካባቢ የሚኖሩ ህዝቦች ይቻላል። ስለዝህ የክልሉ ህዝቦች ትክክል። የአገሪቷ ህዝቦች በተለያዩ አካባቢ የሚኖሩትን ለማመልከት .. ማለትም አይከለክልም። የለም አንድ ህዝብ መባል አለበት እየነገርከን? ፓለቲካ ነው (ኢኮኖሚክሱን አላነሳንም እስካሁን) ህዝብም ህዝቦችም ...ፓለቲካ ነው !! አረ አታድርቀኝ ክክክክክክክክክክክክክክክክክ የፈለገውን በል!
የቀረ ያለ ይመስላል። እመለስበታለሁ። ክክክክክክ
Re: ሕዝብ የሚለው ቃል ከየት መጣ?
Posted: 25 May 2021, 14:13
by Horus
መለከት፣
አስተያቶቹን ሳነብ ሁሉም የተለያየ ጥያቄ ላይ ስለሆኑ አንተ ባየሀው ጉራማይሌ ላይ አንድ ሁለት ምሳሌዎች ላክልበት ።
ብሄር የሚለውን የዘመናችን ገናና ቃል ተመልከት?
ብሄር ለሚለው ቃል ሁሉም ሺ አይነት ትርጉም ቢሰጥም ቃሉ በጣም ቀጥተኛ ነው ።
ብሄር የህብር ጉራማይሌ ነው ። ብሄር የምንለው ህብር የሚለውን ከቀኝ ወደ ግራ በመጻፍና ማንበብ ነው ። ስለዚህ ብሄር ማለት ህብረት ማለት ነው ።
ብሄር ማለት ማህበር ማለት ነው! ሌላ ምስጢር የለውም ። የቃል ስርና ስን ከላይ ያለው የሰው ና የሕዝብ ስር ጋር አንድ ነው ።
ዜጋ የሚለው ቃልም ተመሳሳይ ታሪክ አለው
Re: ሕዝብ የሚለው ቃል ከየት መጣ?
Posted: 25 May 2021, 14:35
by Horus
ዲዲቲ
እኔ እዚህ ላይ አንድ የሰዎች ስብስብ የቱ ፖልቲካዊ ነው? የቱ ሶሺያል ነው? ኢኮኖሚክ ነው ወደሚለው ለመሄድ ግዜም ፍላጎትም የለኝ። የተለያዩ የሰዎች ስብስብ ምን ምን ይባልሉ የሚለው ሶሲዮሎጂ ውስጥ አልገባም ። ነገር ግ ን ስለካታጎሪ ያልከው እንዲህ ነው።
ያሜሪካ ሕዝብና የቻይና ሕዝብ ሁለቱም አንድ ካታጎሪ ናቸው፣ ሕዝብ ናቸው! የተለያየ ካታጎሪ የሚያደርጋቸው ሕዝብ የሚለውው ቃል ሕዝቦች በመባል አይደለም። አሜሪካ እና ቻይና የተለያዩ ጂኦግራፊ፣ አገር፣ መንግስት ስለሆኑ ነው ። ሕዝብ የሚለው ቃል በቻይናም፣ ማሚሪካም ም በኢትዮጵያም አንድ ካታጎሪ ነው።
Re: ሕዝብ የሚለው ቃል ከየት መጣ?
Posted: 25 May 2021, 14:55
by Guest1
ዲዲቲ
በሳቅ ሊሞት ነው! ክክክክክክክክክክክክክክክክክክክክክ ሆዴን አመመኝ!!!
እኔ እዚህ ላይ አንድ የሰዎች ስብስብ የቱ ፖልቲካዊ ነው? የቱ ሶሺያል ነው? ኢኮኖሚክ ነው ወደሚለው ለመሄድ ግዜም ፍላጎትም የለኝ። የተለያዩ የሰዎች ስብስብ ምን ምን ይባልሉ የሚለው ሶሲዮሎጂ ውስጥ አልገባም ። ነገር ግ ን ስለካታጎሪ ያልከው እንዲህ ነው።
ያሜሪካ ሕዝብና የቻይና ሕዝብ ሁለቱም አንድ ካታጎሪ ናቸው፣ ሕዝብ ናቸው! የተለያየ ካታጎሪ የሚያደርጋቸው ሕዝብ የሌው ቃል ሕዝቦች በመባል አይደለም። አሜሪካ እና ቻይና የተለያዩ ጂኦግራፊ፣ አገር፣ መንግስት ስለሆኑ ነው ። ሕዝብ የሚለው ቃል በቻይናም፣ ማሚሪካም ም በኢትዮጵያም አንድ ካታጎሪ ነው።
Re: ሕዝብ የሚለው ቃል ከየት መጣ?
Posted: 25 May 2021, 15:27
by Guest1
ለምሳሌ አለም የሚለውን ቃል ተመልከት? ጉራማይሌው መላአ (መላ፣ ሙሉ፣ በሞላ)፣ ሁሉም፣ ኦል ማለት ነው ። የሁለቱም ቃላት (አለም፣ መለአ) ትርጉም አንድ ሲሆን አጻጻፉ ግን ጉራማይሌ ነው ።
መለዐ መዐለ ዐለመ ዐመለ ለዐመ ለመዐ/ ዐለመ ዐለም ዐመለ ዐመል ሲጠብቅ ዐልለመ ዐለመ በ መ እና ል ምክንያት ብዙ ቃል ተፈጠረ። እልም እርም ትልም ጭልም ህልም
ከበደ ከደበ በደከ በከደ ደበክ ደከበ አንድ ብቻ ከበድ ያሉ ተናባቢዎች በመሆናቸው።
ከረመ ከመረ መከረ መረከ/ቀ ረከመ ረመክ ለምን በ ረ እና በ መ ምክንያት ሳይሆን አይቀርም 3+ ክምር ጥምር ጭምር ተምር ቀመር? ....።
ምን ለማለት? ሁሉም ቋንቋ ስርኣቱን ተከትሎ ሊሆን የሚችልና የማችል ቅንብር አለው። አጻፋፉ ከግራ ወደ ቀኝ ቢሆንም ትርጉም በንባብ የሚገኝ ስለሆነ በስህተት የመጣ አይመስለኝም።