Page 1 of 1
ከምዕራብ የስንዴ ጥገኝነት ነጻ የሆነች ኢትዮጵያ
Posted: 23 May 2021, 01:53
by Horus
ኢትዮጵያችን በዛሬና በ2030 መካከል 10 ቢሊዮን ችግኝ በመትከል አረንጓዴ ኢትዮጵያ እውን ትሆናለች! ያም ማለት
ቆላ ኢትዮጵያን በእርሻና ደን መሸፈን ነው
የክብትና እንሰሳዎች ቁጥር ቢያንስ ላንድ ሰው አንድ ወይም ላንድ ሰው ሁለት ከብት ለማድረስ ነው።
በ2030 ከ200 ሺ በላይ ከብቶች ማለት ነው
አየራችን ንጹህ፣ አፈራችን ለምና ዉሃ አዘል፣
ወንዞች ሙሉና በመስኖ የተመሰኑ
የፍራፍሬና ካፒታል
በጸሃይ ሳይሆን በኤሌክትሪክ የበራች አገር ማድረግ ነው።
ደመና አዝናቢው የዉሃ እናት ኢትዮጵያ !!!
Re: ከምዕራብ የስንዴ ጥገኝነት ነጻ የሆነች ኢትዮጵያ
Posted: 23 May 2021, 03:15
by Guest1
በ27 አመት ውስጥ ወደ በረሃ ስለተቀየረች አዎን በጣም አስፈላጊ ነው። ግን ለኢትዮጵያ አዲስ አይደለም። በደርግ በመንግስቱ በሰፊው የተጀመረ በየአመቱ የሚካሄድ ዘመቻ ነበር።
ደርግ ከዝህም አልፎ አዲስ የጀመረው ነገር ነበር። ኢትዮጵያን ባለእንዱስትሪ ማድረግ።
በኢህአደግ ዘመን ኢንዱስትሪው እንዲፈርስ ተደረገ። በምትኩ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚባለው መጣ። ማእድኗ ለውጭ ሃይሎች ተሽጠ ግብጽ፤ ቱርክ፤ ሳውዲ አረቢያ ምናልባትም ጣሊያን ከተሳታፊዎቹ የመጀመሪያዎቹ ሳይሆኑ አይቀርም። የቻይናም አለ ነዳጅና ጋስ በሶማሌ ክልል። ሆኖም የአላሙዲን ወርቅ በስተቀር በግልጽ የሰፈረ ነገር የለም። ኤፈርት ይባል እንጂ ማን ምን እንደያዘ ወይም እንደተቀራመተ የወጣ መረጃ የለም። ይህንን ሚስጢር ደብቆ ስለ አረንጓዴ አሻራ ማውራት ለጥሩ አይመስልም። መጠርጠር ብቻ?
ኢትዮጵያ ያላትን ሃብት እየሸጠች ነበር አሁንም ቀጥላበታለች። ማእድኗን የምትሸጠው ለምንድነው? ኢንዱስትሪ የላትም። የመርፌ እንኳን መስራት ያልቻለች አገር ስለሆነችና በዝቅተኝነት ስሜት የተዋጠች ለባለጸጋ አገሮች አጎብዳጅ ስለሆነች። በአስር አመት ውስጥ ዝናቡ ይመጣል። ልጆቿ በእርሻ ይተዳደራሉ መንግስታቸው ያውም ከፈቀደላቸው!! ባለኢንዱስትሪዎች መዝናኛ ፓርክና ስማይ ጠቀስ መኖሪያ ቤቶች ይገነባላቸዋል። ልጆቿ በአገራቸው ገረድና አሸክር ሆነው ያገልግላሉ ያውም ባለጽጋዎቹ ስግግብ ካልሆኑና በከፋፍለህ ግዛ እያጨፋጨፉ መግዛት እስካልቀጠሉ ድረስ። የአንድነት የእንጦጦ ፓርክ ምናምን ወዘተ... የሴይጣን ስራ ስለሚመስል እስከዛሬም አላየሁትም ለወደፊቱም አላየውም። አረንጓዴ አሻራ? አረንጓዴ ቅጠላ ቅጠሉ ነው። አሻራ ደግሞ ምንድነው? መሬቱን ማሳመር? ዛፉ አይመነጠርም? አይሰራበትም?