መልእክት አንድ
-የኤርትራ ጦር ከትግራይ አይውጣ፤በትግራይ የሚፈፅመውን ጭፍጨፋ፣ዘረፋና ውድመትም ይቀጥል።
እና
-ኢትዮጵያውያን ለትግራይ ህዝብ ምኑ ናችሁ? ወገኑ ወይስ ጠላቱ?
ኢትዮጵያውያን ሲሰለፉ...ትግራይ ሀገር ትሁን እያሉ ነው!?
+++++++
ኢትዮጵያውያን አሜሪካንን ጣልቃ አትግቢብን ብለው ሰልፍ ሲወጡ ምን እያሉ እንደሆነ በቅጡ መረዳትና ሀላፊነት መውሰድ አለባቸው።
ላለፉት 6 ወራትና እስከ አሁንዋ ሰአት ድረስ በትግራይ ህዝብ ላይ በአለም ታይቶ የማይታወቅ በአይነቱ የተለየ ጭካኔ የተሞላበት ግፍ በኢትዮጵያ፣ኤርትራና አምሀራ ሰራዊቶች በሰማይና በምድር በሚያደርጉት ዘመቻ የዘር ጭፍጨፋ እየተፈፀመ ነው።
በዚህ የትግራይን ህዝብ እንደ ህዝብ ለማጥፋት እየተካሄደ ባለው የተቀናጀ ጦርነት
-ከ 5 ሚልዮን በላይ ህዝብ ለርሀብ ተጋልጧል፤
-ከ2.5 ሚልየን በላይ ህዝብ ከቀየው ተፈናቅሏል።
-ከ60ሺ በላይ ህዝብ ወደ ሱዳን ተሰዷል፣
-ከ150 ሺ በላይ ንፁሀን በግፍ ተጨፍጭፏል፤
-ከ50 ሺ በላይ ሴቶች ተደፍሮል፤
-ገበሬዎች እንዳያርሱ ታግዷል፣የእርሻ መሳርያዎቻቸው ተሰብሯል፣በሬዎቻቸው ታርደው ተበልቷል፣ሲያርሱ የተገኙትም ተገድሏል፤
-በመላው ትግራይ የነበሩት ማህበራዊ ተቋማት ተዘርፎል፣ፈርሷል፤
-ከ1ሺ በላይ አነስተኛና መካከለኛ የማምረቻ ተቆማት ተዘርፏል፣ፈርሷል፤
-ከ50 በላይ ከፍተኛ ኢንዳስትሪዎች ፈርሷል፣ተዘርፏል፤
-በከፍተኛና አነስተኛ የማምረቻ ተቋማት ይሰራ የነበረ ከ350ሺ በላይ ሰው በተቋማቱ መፍረስና መዘረፍ የተነሳ ከስራው ተፈናቅሎ ለችግር ተጋልጧል፤
-የኢትዮጵያና ኤርትራ ሰራዊቶች በጦርነቱ በአለም አቀፍ ህግ የተከለከሉ የኬሚካል የጦር መሳርያዎችን በመጠቀም ከተሞችን ከነ ነዋሪዎቻቸው እያነደዷቸው ነው፤
-የኤርትራና የኢትዮጵያ ጦር ለርሀብ ለተጋለጠው ከ5 ሚልዮን በላይ ህዝብ አስቸኳይ አለም አቀፍ እርዳታ እንዳይገባ ከልክለው ህዝቡን በርሀብ እያስጨረሱት ነው፤
ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግስት
-የኤርትራ ሰራዊትን አስገብቶ ይህን ሁሉ ግፍ በትግራይ ህዝብ ላይ ሲፈፀም የሉአላዊነት ጥያቄ አልተነሳም፤
-የUAE ድርኖች የትግራይ ከተሞችን ሲያፈርሱና ህዝቡን ሲጨፈጭፉ የሉአላዊነት ጥያቄ አልተነሳም፤
-የሶማልያ ሰራዊት ትግራይ ገብቶ ህዝብን ሲገድል የሉአላዊነት ጥያቄ አልተነሳም፤
-የኤርትራ ጦር አሁንም ድረስ በመላው ትግራይ ሰፍሮ ሲዋጋ፣ህዝብን ሲጨፈጭፍ፣መታወቅያ አድሎ ሲያስተዳድር የሉአላዊነት ጥያቄ አልተነሳም፤
-የኤርትራ ጦር አሁንም ድረስ ከፊንፊኔ ዙርያ እስከ 4 ኪሎ ቤተ መንግስት ድረስ የስርአቱ ታማኝ ጠባቂ ሆኖ ሲሰራ የሉአላዊነት ጥያቄ አልተነሳም፤
-የኤርትራ ጦር አሁንም ድረስ በኦሮምያ ገብቶ ከኦነግ ጋር ጦርነት ሲዋጋ፣ሰላማዊ ዜጎችን ሲገድል የሉአላዊነት ጥያቄ አልተነሳም፤
-ሱዳን እንኳን በአቅምዋ ጦርነት ከፍታ ወደ ጎንደር 50 ኪሜ ድረስ ገብታ ወረራ ስትፈፅም ፣በርካታ ሺ ሰዎችን ስታፈናቅልና በቢልዮኖች የሚቆጠር ንብረት ስትዘርፍና ስታወድም በሰልፍ ደረጃ የተገለፀ አንድም የሉአላዊነት ጥያቄ የለም፤
ታድያ አለም አቀፉ ማህበረሰብ አሜሪካንን ጨምሮ ምን አለ!?
-በትግራይ ህዝብ ላይ የማፈፀመውን የዘር ጭፍጨፋ ይቁም አለ፤
-በትግራይ ህዝብ ላይ ጭፍጨፋ እየፈፀመ ያለው የኤርትራ ጦር ይውጣ አለ፤
-በትግራይ ህዝብ ላይ የዘር ማፅዳት ወንጀል የፈፀመው የአማራ ሀይል ይውጣ አለ፤
-ለርሀብ ለተጋለጡት ከ5 ሚልዮን በላይ ለሆኑት በመላው ትግራይ ላለው ህዝብ አስቸኳይ እርዳታ ሳይደናቀፍ ይድረስ አለ፤
-በትግራይ ህዝብ የተፈፀመው የዘር ጭፍጨፋ ይጣራ፣ወንጀለኞቹም ለፍርድ ይቅረቡ አለ፤
እንግዲህ ዛሬ ኢትዮጵያውያን በሉአላዊነት ስም አደባባይ ወጥተው አሜሪካንን ለመቃወም ሲወጡ
-በትግራይ የሚፈፀመው የዘር ጭፍጨፋ አይቁም፤
-ኤርትራም አትውጣው፣ጭፍጨፋዋን ትቀጥል፤
-የአማራ ሀይልም አይውጣ፣የዘር ማፅዳቱን ይቀጥል፤
-የሰብአዊ እርዳታም ወደ ትግራይ አይግባ፤ህዝቡ በርሀብ ይለቅ፤
-ወንጀለኝቹም አይነኩ፣የትግራይን ህዝብ መጨፍጨፍ የምንደግፈው ነው፣
እያሉ እንደሆነ በግልፅ መገንዘብ ያስፈልጋል።
ይህ ማለት ጠቅለል ባለ አገላለፅ
-ጦርነት ይቁም፣ሰብአዊ እርዳታ ለህዝብ ይድረስ፣ወራሪ ጦር ይውጣ ብሎ ድምጿን ላሰማችው አሜሪካ አደባባይ ወጥቶ መቃወም አንድም ድንቁርና ወለድ ኢ-ሰብአዊነትና ፍፁም ጭካኔ ሲሆን ሁለትም ለትግራይን ህዝብ ጥፋት ያለህን ግልፅ ድጋፍ በአለም ህዝብ ፊት እንደ ማሳየት ተደርጎ የሚወሰድ ነው።
የትግራይን ህዝብ ጥፋት ደግፎ አደባባይ መውጣትስ መልእክቱና ውጤቱ ምንድን ነው?
-መልእክቱ፦ ትግራይ የኢትዮጵያ አካል አይደለችም፣የትግራይ ህዝብም ወገናችን አይደለም፣ስቃዩም ህመሙም አይሰማንም፣ጥፋቱንም የምንፈልገው በመሆኑ ሊያጠፉት ከተነሱት ሀይሎች ጎን ሆነንም አስፈላጊውን ድጋፍ እናደርጋለን የሚል ሲሆን፤
-ውጤቱም፦ የትግራይ ህዝብ ህልውናውን ለማስጠበቅ የሚያደርገው ትግል አለም አቀፍ እውቅናን የሚያስገኝለት ይሆናል። ነገ ጠላትቹን የሚከፈለውን መስዋእትነት ኸፍሎ ደምስሶ ሲያበቃ ነፃነቱን አውጆ ሀገር ሲመሰርት ከአለም አቀፉን ማህበረሰብ የሚጠይቀው እውቅናንናን ድጋፍን በቀላሉ እንዲያገኝ ያግዘዋል።
እንግዲህ
-ኢትዮጵያውያን በሉአላዊነት ተሸፋፍናችሁ በትግራይ ህዝብ ላይ የሚፈፀመውን የዘር ማጥፈት ጦርነት ደግፋችሁ ስትወጡ በቀጥታ የትግራይን ህዝብ ህዝባችን አይደለም እያላችሁ በመሆኑ ለሀገረ ትግራይ ምስረታ ያላችሁን ይሁንታ የምታረጋግጡበት ህዝበ ውሳኔ ተደርጎ ይቆጠራል።
-ኢትዮጵያውያን በሉአላዊነት ስም የምታደርጉት ሰልፍ ውጤቱ የኢትዮጵያን አንድነትና ሉአላዊነትን ማስከበር ሳይሆን ኢትዮጵያን መበታተን መሆኑን ልብ ልትሉ ይገባል።
https://www.facebook.com/Trust.Hope11/p ... 9700735710