Asswash, Aba ወንድሜ
Posted: 19 May 2021, 17:56
አደይ ትግራይ
ማነው የረገመሽ
ልጅ አይውጣልሽ ያለሽ።
የወለድሻቸው ልጆሽ
አቃጥለው አስቃጠሉሽ።
ጦርነት ዳንሳቸው
ጥላቻ ፍቅራቸው
መለያየት አንድነታቸው
ክፋት ደግነታቸው
አምላክ ይቅር ይበላቸው።
አደይ ትግራይ እግዚአብሔር ያጥናሽ
በቃሽ ይበልሽ።

ማነው የረገመሽ
ልጅ አይውጣልሽ ያለሽ።
የወለድሻቸው ልጆሽ
አቃጥለው አስቃጠሉሽ።
ጦርነት ዳንሳቸው
ጥላቻ ፍቅራቸው
መለያየት አንድነታቸው
ክፋት ደግነታቸው
አምላክ ይቅር ይበላቸው።
አደይ ትግራይ እግዚአብሔር ያጥናሽ
በቃሽ ይበልሽ።



