Page 1 of 1
320 የአሸባሪው አባላት በመከላከያ ሰራዊት ተደመሰሱ!
Posted: 14 May 2021, 09:33
by Ejersa
በማይካድራ ጭፍጨፋ አድርሶ ወደ ሱዳን በመሸሽ ተደራጅቶ የተለያዩ የመገናኛ መሳሪያዎችንና መድሀኒቶችን በመያዝ ከሱዳን በአምዳይት አድርጎ ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ የነበሩ 320 የጁንታው አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ከ320 አባላት ውስጥም የተማረኩ የጁንታው አባላት መኖራቸው ተመልክቷል፡፡
በሚኒስቴሩ የመከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊ የሆኑት ብርጋዴር ጄነራል ተስፋዬ አያሌው ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጠቡት ወቅት እንዳሉት ከመከላከያ ሰራዊት የተሰረቁ እና የወጡ፣ሳተላይት ስልኮች ፣ የሬድዮ መገናኛዎች እንዲሁም መድሃኒቶች በሰራዊቱ ቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ተናግረዋል።
ከሱዳን መከላከያ ሰራዊት አመራሮች ጋር ሚስጥራዊ ግንኙነት ሲያደረጉ የነበረውን መረጃ የመከላከያ ኃይሉ በቁጥጥር ስር ማዋሉንም የመከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊው ብርጋዴር ጄነራል ተስፋዬ አያሌው ተናግረዋል።
የጁንታው አባላት ከውጭ በሶስት ቡድን ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ እና ረጅም ቅድመ ዝግጅት ሲያደርጉ እንደነበርም የገለፁት ብርጌዳር ጄነራል ተስፋዬ ፣የአንደኛው ቡድን መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገ እና አባላቱ ቀደም ብለው የመከላከያ ሰራዊት አባል የነበሩ እና የሸሹ ነገር ግን የጁንታውን አባል ሲደግፉ የነበሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ሁለተኛው ቡድን ደግሞ ሱዳን ካርቱም ሆኖ ስልጠናዎችን የሚሰጥ ሲሆን ሶስተኛው በሀገር ውስጥ የነበረ መሆኑን ብርጋዴር ጄነራል ተስፋዬ ገልጸዋል።
በሀገር ውስጥ የቀሩ የጁንታው ርዝራዦችን ለማደን የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እና “መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት እያደረስን ነው” በሚል የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ መሆኑን ብርጋዴር ጄነራል ተስፋዬ አያሌው ተናግረዋል።
ምንጭ Ethiopian Broadcasting Corporation
Re: 320 የአሸባሪው አባላት በመከላከያ ሰራዊት ተደመሰሱ!
Posted: 14 May 2021, 11:00
by Ejersa
Ejersa wrote: ↑14 May 2021, 09:33