ግጭት ለማጥፋት ትውፊት ማፍረስ ጥፋት መጨመር ነው። አንዱ በጥረቱ ያፈራውን ለሌላ መስጠት ጎታች ነው። የኦርቶዶክስ ንብረት የሆነ ሁሉ የቤተ ክርስቲያኗ ብቻ ነው።ለሌላውም እምነት እንድሁ።
Posted: 12 May 2021, 12:14
ግጭት ለማጥፋት ትውፊት ማፍረስ ጥፋት መጨመር ነው። አንዱ በጥረቱ ያፈራውን ለሌላ መስጠት ጎታች ነው። የኦርቶዶክስ ንብረት የሆነ ሁሉ የቤተ ክርስቲያኗ ብቻ ነው።ለሌላውም እምነት እንድሁ።
---በመጀመሪያ የእግዜርን ለእግዜር የቄሳርን ለቄሳር ብለን ሁላችን እንቀበል። ይህ ማለት መንግስት እጆቹን ከቤተ-እመነት ያንሳ ። እያንዳንዱ ጥንታዊ የአበው እምነት የሆኑት ኦርቶዶክስ ክርስትና እና ኢትዮዽያዊ እስልምና የሁሉም ዜጋ እሴት ናቸው። መጠበቅ እና መከበር ይገባቸዋል። በመቀጠል በአገራችን ኦርቶዶክስ ክርስትና በኩር ቀደምት ሃይማኖት ነው ስለዚህም ብዙ ታሪካዊ እና መንፈሳዊ ፀጋ ለአገሪቱ አበርክታለች። ለኢትዮጵያም ብዙ ታሪካዊ ተገድሎዎች ከብዙ ጠላቶች ጋር ፈጽማለች። ስለዚህም የክርስቲያን እና የእስላሙ እንድሁም ሌሎች አዲስ እምነት ተከታዮች ሁሉ ቅርስ ናት። ልንጠብቃት እንጅ ልናጠፋት መጣጣር ከፍተኛ የታሪክ ሽተት እና ፀፀት ይሆናል።
----ይህች የበኩር እምነት በስሟ በርካታ የእራሷ የሆኑ ንብረቶች በየዘመኑ አፍርታለች። በየጊዜው ከቀማኞች ጋርም ተጋፍጣለች። በትክክለኛው እና ፍትሃዊ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ህገ-ደንብ ቤተ-እመነቷ ንብረቷን የመጠቀም፣ የማከራየት፣ የመሼጥ፣ የማስተላለፍ ፍቃድ ያላት ህጋዊ እና መንፈሳዊ አካል ናት። ደርግ በሶሻሊዝም የቀማት ንብረት እና ህጋዊ ስያሜዎች ሁሉ በፍትሃዊ መንግሥት አንፃር የእርሷ ናቸው። የአገር ሃብት የሚያድገው ሌላ ተጨማሪ ሃብት በመጨመር እንጅ ነጥቆ ለሌሎች በመስጠት አይደለም። ሰለዚህ መንግስት የጉልበተኝነት ስሜት ውስጥ በመግባት የመስቀል አደባባይ ለፍጥርያ ስግደት መፍቀዱ የስህተተ መንገድ ብቻ ሳይሆን የሰነፍ መፍትሄ ነው። ይህን ፈቃድ መስጠት የምትችለው እራሷ ቤተ ክርስቲያኗ ብቻ ናት። በተመሳሳይም ቦታውን ለመጠቀም የሚፈልግ ሁሉ የቤተ ክርስቲያኗን ፈቃድ በክራይም ይሁን በነፃ ማግኜት እንጅ መንግስትን ጉልበተኛ ተራ ኣስከባሪ መሆን አይችልም። ሌሎች ቤተ-እምነቶችም የእራሳቸው ንበረት በማፍራት ተጨማሪ ትውፊት እና ፀጋ መፍጠር እንጅ ሌላ ቀድሞ ባፈራው ላይ መደረብ አንድም ስንፍና ሁለትም ከሃይማኖት በጎ ሥራ ይልቅ ዕብሪተኝነት ግብር ይመስላል።
--- Confiscating' and distributing wealth created by others to those who did not is an act of robbery, it will not bring prosperity. Instead creating wealth results in growth and development. A government acting as steward of robbery is an evil agent of misery, anarchy and impoverishment. The Ethiopian government illegal action exerted on the Ethiopian Orthodox Churches rightful property (fixed or non-fixed) is unwise. Hands off from the oldest religion of the country - Orthodox Christianity.