Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42558
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ኢትዮጵያዊያን እራሳችን ለእራሳችን ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መፈጸም እንችላለን !!

Post by Horus » 04 May 2021, 19:06

እኔ ሆረስ ዐይነ ኩሉ ነኝ፤ ቃል መፍለጥ አልወድም።

ነጮች አገርና መንግስት አቁመው የፖለቲካ ስርዓት ከመፍጠራቸው ቀድሞ ኢትዮጵያ በመንግስት ተገራጅታ የኖረች አገር ናት።

ማን ይሙት ታያላችሁ ምናልባት ባፍሪካ ታሪክ ያለ ነጭ ሞግዚትነት በራሷ እውቀት፣ በራሷ ህዝብ አደራጅነት የራሷን ዴሞክራሲ የምታቆም አገር ኢትዮጵያ ትሆናለች ። ያውሮፓን ፈቃድና የገንዘም ምጸዋት ፎቃቆች ከምርጫ ቢወጡ ፈስ ቀለለ ማለት ነው።

በነገው ምርጭ ደጋግሜ እንዳልኩት ከ600 ወረዳዎች ቢያንስ 1/3ኛ ወይም 200 ወረዳዎች ትክክለኛ ታማኒ ምርጫ ከተደረገ ትልቅ ድል ነው ለኢትዮጵያ። በአመጽና የዘር ቀውስ ውስጥ ያሉት ወረዳዎች መንግስት ሰላምና መረጋጋት አድርጎ ህግ ሲያስከብር ልዩ ምርጫ (እስፔሻል ኢሌክሽን) እያደረጉ ፓርላማውን ይቀላቀላሉ

ሮማ ባንድ ቀን አልቆመችም። እንዲያውም የዚህ ምርጫ ትልቅ ጥቅም ዛሬ ሰላምና ሰራት ያስከበሩት እና ሰላም ወዳድ የሆኑት ወረዳዎች እውነተኛ ዲሞክራሲን ለሌሎቹ ሰላም ጠል፣ ኢትዮጵያ ጠል፣ የውጭ ፍርፋሪ በመልቀም የሰለጠኑት እንዲማሩ እድል ያገኛሉ ። ሁሉ ሕዝብ እኩል ነቃተ ህሊና የለውም ። ሁሉ ሕዝብ እኩል የፖለቲካ ብስለት የለውም።

ዴሞክራሲ ዝም ብሎ ሆሆታ አይደለም፣ የአንድ ሕዝብ ራስ ገዝነት እና የፖለቲካ ዳኝነት ችሎታ መለኪያ ነው። ስለሆነም የዛሬ ወር ትክክለኛ ምርጫ ሚያዘጋጁት ወረዳዎች "የዲሞክራሲ ትግበራ" ማሳያ፣ ማስተማሪያ፣ ማሰልጠኛ ይሆናሉ !!

ያለ አውሮፓ ቅኝ ግዛታዊ መልካም ፈቃድ እኛ ኢትዮጵያዊያን በራሳችን ዴሞክራሲን ለራሳችን ሕዝብ እውን እናደርጋለን !!


ኢትዮጵያ አይነኬ፣ አይበገሬ ለዘላለም ትኑር !