Page 1 of 1

የታለ ድምፃቹ?! ዓምዶም ገብረስላሴ - የዓረና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ

Posted: 04 May 2021, 18:46
by sarcasm
እኔ ህወሓትን ስታገል ጨቋኝና ኣምባገነን ስለነበረች ነው።

ኣሁን ያለው ስርዓት ብልፅግና የምቃወም ደግሞ ወራሪ፣ ጨፍጫፊ፣ ዘራፊ፣ ኣስዘራፊ፣ ኣፈናቃይ ስለሆነ እቃወመዋለው።
እንደ የኣንድ ሃገር ዜጎች(ኢትዮጵያ) ባታስቡ እንደ የሰው ፍጡር በትግራይ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ወደር የለሽ ጭካኔ የተሞላበት ጭፍጨፋ ኣታወግዙም?

ኣዎ !

በኣማራዎች፣ ኦሮሞዎች፣ ጋምቤላዎች፣ ቤንሻንጉሎች ወዘተ ዜጎች ግድያና መፈናቀል ሲደርስባቸው ኣውግዤ ድምፄ ሳሰማ ነበር።
እናንተው ግን የታለ ወገናዊ ሃዘኔታ፣ የታለ ዜግነታዊ ግዴታ፣ የታለ ሰብኣዊ ርህራሄ የሚጋራ ድምፃቹ?

ኣሁንም ደግሜ ልንገራቹ !

በትግራይ ህዝብ ላይ ስለ ወረደው ግፍ፣ ሰቆቋና ቸነፈር ደግፋቹሃልና እጆቻቹ በደም ተጨማልቋል፤ ኣልያም በህዝባችን የወረደው መዓት ምንም ኣልተሰማቹም፤ ቢሰማቹም ድምፅ ኣላሰማቹምና ከደሙ ንፁሃን ኣይደላቹም።

የትግራይ ህዝብ በባዕድ ሃይሎችና በሃገር ውስጥ በጦር ወንጀለኝነት የሚስፈርድ በደል ደርሶበታል።
ኣሁን "በትግራይ እየተካሄደ ያለው ጦርነት ይቁም !" የሚል ድምፃቹ መስማት እፈልጋለው።

የታለ ድምፃቹ !



https://www.facebook.com/amdom.gebresla ... 3044915652