Page 1 of 1

የትግራይ ህዝብ ተወሯል – ሳልሳይ ወያነ ትግራይ

Posted: 28 Apr 2021, 08:46
by sarcasm
እኛም በአዲሱ የትግል ምእራፍ ላይ እንገኛለን ሲሉ የሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) ምክትል ሊቀመንበር አቶ አሉላ ሀይሉ ተናግረዋል፡፡

ምክትል ሊቀመንበሩ አከሎም እንደ ትግል ቆጥረን አዲስ የዲፕሎማሲ ስራዎች እየሰራን ነውም ብለዋል፡፡

እንደ ፓርቲ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በመሆን ህዝቡ እያጋጣመዉ ካለዉ ችግር እንዲወጣ ሰላማዊ ትግል እያደረግን ነዉም ብለዋል ምክትል ሊቀ መንበሩ፡፡

በትግራይ ክልል ያለዉ ጦርነት ሕዝባዊ ትግል ሆነዋል ያሉት አቶ አሉላ የትግራይ ህዝብ እየደረሰበት ያለዉ ግፍ የአለም ማህበረሰብ እንዲያቀዉና የሰብአዊ እርዳታ እንዲያገኝ እንዲሁም ሚድያዎች በህዝቡ ላይ እየደረሰ ያለዉን ግፍ እንዲዘግቡ የማስተባበር ስራ እየሰሩ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ትግራይ ከወራሪ ሀይሎች ነጻ እስክተወጣ እና የትግራይ ህዝብ የመረጠዉ መንግስት እስኪ መራው እንደ ፓርቲ ሆነ እንደ ግለሰብም እየሰራን ነዉ ብለዋል፡፡

Continue reading