Page 1 of 1

የሽግግር መንግስት የሚባለው የተሳሳተ ሜታፎር ነው! ለምን?

Posted: 27 Apr 2021, 23:33
by Horus
መሸጋገሪያ ድልድይ ማለት ነው ።

ድልድይ ካስፈለገ ወንዝ ወይም ገደል አለ ማለት ነው ። ምንድን ነው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ገደል?

የጎሳ ክፍፍልና ጎሳ ፖለቲካ ነው ትልቁ ገደል! ይህ ገደል ደሞ ራሱ ፖለቲካው ነው። የጎሳ ፖለቲካ የገደል ፖለቲካ ነው ።

በሽግግር ከዚህ ወዲያ ማዶ መሻገር ማለት ከወንዙ ወዲህ አንድ ሰ ርዓት አለ፣ ከእወንዙ ወዲያ ሌላ የተለየ ተፈላጊ ሲስተም አለ ማለት ነው! ምንድን ነው ያ ሲስተም?

ከድልድዩ ማዶ ያለው የዜጋ ወይም የዴሞክራሲ ሲስተም ከሆነ የጎሳ ፖለቲከኞች እና ባለስልጣኖች እንዴት ነው ድልድዩን ተሻግረው ወደ ዜጋ አለም ሚሄዱት

ስለዚህ በዛሬ የኢትዮጵያ ሁኔታ ሽግግር ትርጉም የሌለው ሚታፎር ነው።

መሆን ያለበት በተደጋጋሚ የህዝብ ምርጫዎች አማካይነት ሰዎችን፣ ተቋሞችን፣ ሲስተሞችን መለወጥ ወይም ማሻሻል ነው።

የሽግግር ድልድይ የሚባለው ራሱ ያገሪቱ ፖለቲካ ሲስተም፣ ያገሩ የቀን ተቀን ፖለቲካ ፕሮሴስ ነው።

ድልድዩ ራሱ ፖለቲካው ነው ። ድልድዩ አሁን ያሉት ፓርቲዎች ናቸው ። ድልድዩ አሁን ያለው መንግስት ነው። ስለሆነም የፖለቲካው ሕዝብ፣ ፓርቲዎቹ፣ መንግስት ተደጋጋሚ ምርጫ ማድረጋቸውን ከቀጠሉ ያ ነው ሽግግር፣ ያ ነው ሂደት ማለት !

ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዜ ሃ ብላ መንግስት እያቆመች አይደለም! ሽግግር ለኢትዮጵያ አይሰራም ። ኢትዮጵያ መንግስት አላት፣ መንግስት ማሻሻል፣ አዳዲስ ተቋማት መፍጠርና የሚለወጡትን በሂደት መለወጥ ነው ያለባት ።

ከዚያ ውጭ አናርኪና የፖለቲካ ቀውስ ነው ። መንግስት ማለት ኦርደር፣ ሕግና ስርዓት ማለት ነው ። ይህ ሁልግዜም መኖር አለበት !!

Re: የሽግግር መንግስት የሚባለው የተሳሳተ ሜታፎር ነው! ለምን?

Posted: 28 Apr 2021, 13:08
by Horus
አሁን የሚፈለገው በያንዳንዱ ዜጋ ድምጽ የተመረጠ መንግስት እንጂ ሌላ የልሂቃን እና የፖለቲካ ነጋዴዎች መነታረኪያ ሽግግር ቅብጥርሴ አይደለም። ይህ ዉስጡ ባዶ ሆኖ ስሙ ብቻ የቀረ የግዜያዊ ህዝባዊ መንግስት በቃ እነርሳው።

ተሳካም አልተሳካም። ሙሉ ሆነም ቁንጽል፣ ርብሻ ይኑረውም ሰላም ዛሬ፣ በዚህ ታሪካዊ ወቅት ኢትዮጵያ ምርጫ በማድረግ የዴሞክራሲን ሂደትና አሰራር መለማመድ ነው።

ሌላ የፖለቲከኞች የሽግግር ጥርቃሞ ለዘረፋ፣ ደሞዝተኛ እና እክሌ የቢባሉ ሃሳብ ቸርቻሪዎች አገሪቱን ለማመስ እንጂ ቅንጣት ልዩነት አይፈጥሩም፤ እንዲያውም መንግስት ሆነው እንኳን አብሮ ሊቆሙ አይችሉም።

የ2021 ሽግግር መንግስት ሰዎች ሳያስቡ ሳያብላሉ በስመነጋ የሚወረውሩት ባዶ ቃል ነው።

በህዝቦች፣ በቡድኖች መካከል ውይይት፣ እርቅ፣ ስምምነት ማድረግ ሌላ ጉዳይ ነው ። ያን ለማድረግ የሽግግር መንግስት አያስፈልግም ። በቃ !