Page 1 of 1

የኢዜማ ምስጢር ተብሎ የተለቀቀው ሰነድ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኒታ ቁልጭ አድርጎ የሚተነትን ፕሮፌሽናል Situation Analysis ነው

Posted: 27 Apr 2021, 02:52
by Horus
እኔ ይህ ሰነድ እውነት ይሁን ዉሸት፣ ኢዜማ ይጻፈው ወይ ሞሳድ ጉዳዬ አይደለም! የትንተናው ይዘት ምንድን ነው? ትክክል ነው ወይ? ጥሩ ሎጂካል ሙሉ ነው ወይ? አው፣ አው!

እዚህ ኢዜማን፣ ብርሃኑን፣ አንዳርጋቸውን፣ ምናምን ሚቃወሙት ሁሉ ላከፈው 20 አመታት ቀስተ ደመናን። ብርሃኑን፣ ግንቦት 7 ወዘተ ወዘተ ሲቃወሙ የኖሩ ፣ ሲቃወሙት የሚሞቱ ከሃሳባቸው ጋር ተቆራኝተው ጭብጥ ነባራዊ ሁኔታ ጥሎአቸው የሄደ ፍጡራን ናቸው።

ይህ ሰነድ ማንም ጻፈው ማን እውነት ተናጋሪ፣ ግልጽና ጥልቅ ግዜያዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ ትንተና ነው። በእኔ ግምት ይህ ሰነድ ሊሆን ይችላል የተመድ ጸረ ኢትዮጵያ አቋም ያስለወጠው ! ኢትዮጵያን ለማፈራረስ መሞከር ለራሱ ላሜሪካም የማይበጅ እንደ ሆነ የሚያሳይ ሰነድ ነው።

የአፍሪካ ቀንድ ዋና ስራ አሁን ኢትዮጵያን ማጠናከርና የነአይሲስና ሌሎች አሸባሪዎች ቀጠናውን እንዳይወስዱት መከላከል ነው።

ሆረስ ነኝ

Re: የኢዜማ ምስጢር ተብሎ የተለቀቀው ሰነድ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኒታ ቁልጭ አድርጎ የሚተነትን ፕሮፌሽናል Situation Analysis ነው

Posted: 27 Apr 2021, 03:18
by Horus
ልብ በሉ ኤርሚያስ ለገሰ አንድ ግዜ ኢዜማ መፍረስ ያለበት ድርጅት ነው ብሎ ነበር ። ታዲያ እንደዚያ ያሉ በራሳቸው የጥላቻ ቁጣ የበገኑ ቅናታሞች ናቸው ጋዜጠኛ ተብለው ሚዛናዊ ትችት እንዲያቀርቡ ሚጠበቀው !!

አረፈው የዩ ቱብ ሳንቲም ልቀሙ ሰከን ያለውን ፖለቲካ ለነኢዜማ ተዉት እላለሁ !!

ይህ ሰነድ እጅግ አጥጋቢ ጥልቅ ግምገማ ነው።

Re: የኢዜማ ምስጢር ተብሎ የተለቀቀው ሰነድ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኒታ ቁልጭ አድርጎ የሚተነትን ፕሮፌሽናል Situation Analysis ነው

Posted: 27 Apr 2021, 03:50
by temari
I agree! Any armed group that is outside of the state power is a potential national security threat. I found the document to be objective and professional. Ethnic based politics mostly is based on whining and crying and victimhood. So I'm not surprised if these people whine as usual. That is the only politics ethnic based politics know anyway.
Horus wrote:
27 Apr 2021, 02:52
እኔ ይህ ሰነድ እውነት ይሁን ዉሸት፣ ኢዜማ ይጻፈው ወይ ሞሳድ ጉዳዬ አይደለም! የትንተናው ይዘት ምንድን ነው? ትክክል ነው ወይ? ጥሩ ሎጂካል ሙሉ ነው ወይ? አው፣ አው!

እዚህ ኢዜማን፣ ብርሃኑን፣ አንዳርጋቸውን፣ ምናምን ሚቃወሙት ሁሉ ላከፈው 20 አመታት ቀስተ ደመናን። ብርሃኑን፣ ግንቦት 7 ወዘተ ወዘተ ሲቃወሙ የኖሩ ፣ ሲቃወሙት የሚሞቱ ከሃሳባቸው ጋር ተቆራኝተው ጭብጥ ነባራዊ ሁኔታ ጥሎአቸው የሄደ ፍጡራን ናቸው።

ይህ ሰነድ ማንም ጻፈው ማን እውነት ተናጋሪ፣ ግልጽና ጥልቅ ግዜያዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ ትንተና ነው። በእኔ ግምት ይህ ሰነድ ሊሆን ይችላል የተመድ ጸረ ኢትዮጵያ አቋም ያስለወጠው ! ኢትዮጵያን ለማፈራረስ መሞከር ለራሱ ላሜሪካም የማይበጅ እንደ ሆነ የሚያሳይ ሰነድ ነው።

የአፍሪካ ቀንድ ዋና ስራ አሁን ኢትዮጵያን ማጠናከርና የነአይሲስና ሌሎች አሸባሪዎች ቀጠናውን እንዳይወስዱት መከላከል ነው።

ሆረስ ነኝ

Re: የኢዜማ ምስጢር ተብሎ የተለቀቀው ሰነድ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኒታ ቁልጭ አድርጎ የሚተነትን ፕሮፌሽናል Situation Analysis ነው

Posted: 27 Apr 2021, 03:53
by kibramlak
ሰላም ሆረስ

እኔ ደግሞ በተቃራኒው ሆኖ ነው ያገኘሁት፣፣ እዛ ውስጥ እተፃፈው ውስጥ ምንም አዲስ ነገር አላገኘሁበትም፣፣ ሰው ሁሉ የሚያወራውን ነው ለቃቅመው የፃፉት፣፣ በተጨማሪም በአብን ላይ ያሰፈሩት ውንጀላ ከስትራቴጅም ከገፅታም አኳያ ትልቅ ስህተት ነው ብየ አስባለሁ፣፣ ምክንያቱም ኢዜማ ከብልፅግና ጋር ለመጣመር ካላሰበ በስተቀር አሁን ባለው የፖለቲካ ሙቀት ከ አብን ጋር ወደፊት ጥምር መንግስት ለመመስረት እድሉ ይኖረዋል፣፣ አማራ ክልል ብልፅግናን በጣም የተጠላ ይመስላል፣፣ አብይ የከተማ ጩኸት ብሎ አጣጥሎታል፣ እውነታው ግን ከከተማው ይልቅ የገጠሩን ማህበረሰብ ልብ የሰበረ ድርጊት ነው የተፈፀመው፣፣ እናም ኢዜማ ስትራቴጅክ ስህተት ሰርቷል ባይ ነኝ፣፣ የፈለገ ቢሆን እንደዚግነት ፓርቲ ለኢዜማ አብን እንጅ ኦኸዴድ በተአምር ሊቀርበው አይችልም፣፣ እንዳውም ብርሀኑ ወደ አብይ ጠጋ ጠጋ እያለ ይመስላል አብይን ለማዳን፣፣ ለማንኛውም ይህን ሰነድ የተባለውን አንብቤ ለኢዜማ ያለኝ አመለካከት ቀንሷል
Horus wrote:
27 Apr 2021, 03:18
ልብ በሉ ኤርሚያስ ለገሰ አንድ ግዜ ኢዜማ መፍረስ ያለበት ድርጅት ነው ብሎ ነበር ። ታዲያ እንደዚያ ያሉ በራሳቸው የጥላቻ ቁጣ የበገኑ ቅናታሞች ናቸው ጋዜጠኛ ተብለው ሚዛናዊ ትችት እንዲያቀርቡ ሚጠበቀው !!

አረፈው የዩ ቱብ ሳንቲም ልቀሙ ሰከን ያለውን ፖለቲካ ለነኢዜማ ተዉት እላለሁ !!

ይህ ሰነድ እጅግ አጥጋቢ ጥልቅ ግምገማ ነው።

Re: የኢዜማ ምስጢር ተብሎ የተለቀቀው ሰነድ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኒታ ቁልጭ አድርጎ የሚተነትን ፕሮፌሽናል Situation Analysis ነው

Posted: 27 Apr 2021, 04:19
by Horus
ክብረአምላክ
አይምሰልህ! ኢዜማዎች በጣም ጥንቁቆች ናቸው ። አሁን በግልጽ የጎሳ ፌዴሬሽን እንዲፈርስ፣ ሕገ መንግስቱ እንዲለወጥ በሄዱበት ሁሉ እያነሱት ነው። ይህም ማለት ኢዜማ በጎሳ ክልሎች ሄዶ ክልል መፍረስ አለበት የሚል ጽኑ ዜጋዊ ብሎም የብዙ ሚሊዮን ኢትዮጵያዊነት አማኝ ህዝብ ቀልብ እየሳቡ ነው።

ስለዚህ የጎሳ ድርጅቶች ላይ ግልጽ አቋም መያዛቸው ለኢትዮጵያ ወደ ፊት ፖለቲካ አስፈላጊ ነው ። ኦነግ የጎሳ ድርጅት ነው ። ትህነግ የጎሳ ድርጅት ነው። አብን የጎሳ ድርጅት ነው ወዘተ። ይህን ፋክት ማሽኮርመም ስህተት ነው። አብን ከማ ጋር ቅርበት እንዳለውና ከማ ጋር አብሮ መስራት እንደ ሚፈልግ ያውቃል። ኢዜማም እንዲሁ ።

መጀመሪያ ግን የቱ ነው የጎሳ ፓርቲ? የቱ ነው የኢትዮጵያዊ ፓርቲ? ትብለው ሎጂክ ላይ የቆመ ካታጎሪ ማበጀተ እጅግ ቀዳሚው ኮግኒቲቭ ስራ ነው። ይህ ማለት ድርጅቶች ለተለያየ አልማና የስራ ስልት ህብረት አይፈጥሩም ማለት አይደለም ።

ስለ አማራ የታጠቀ ሃይል ሲወራ አብን የተነሳው አንዳንድ አባሎቹ ተብሎ ነው ። ይህ መሰል አባባል አንድ ሰው እርግጠኛ መረጃ ሳይኖረው አይናገርም ።

ሰው ሁሉ ኢዜማና ብልጽኛ አብረው ይሰራሉ፣ መርጅ ያደርጋሉ ምናምን ይባላል። ዉሸት ነው። የኢትዮጵያ አንድነትና መኖር የሚደግፉት የብልጽኛ ክንፍ በትክክል ከኢዜማ ጋር በብዙ ነገር ሊስማሙ ይችላሉ ። ግን ልብ በል የኢዜማ ሶሺያል ዴሞክራሲና ያቢይ መደመር ልማታዊ መንግስት በጣም የለያያሉ።

ዛሬ ግን አቢይና ብርሃኑን አንድ የሚያደርጋቸው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ደህንነት ጉዳይ ነው። ያ ደሞ እጅግ እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው።

ዞሮ ዞሮ ፖለቲካ የስልጣን ጉዳይ ነውና ይህ ሁሉ ተቺና ተቃዋሚ የፖለቲካው ሚዛን ወደሱ ፓርቲ እንዲዘምም ፈልጎ ነውና ይገባኛል።

Re: የኢዜማ ምስጢር ተብሎ የተለቀቀው ሰነድ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኒታ ቁልጭ አድርጎ የሚተነትን ፕሮፌሽናል Situation Analysis ነው

Posted: 27 Apr 2021, 06:17
by kibramlak
ሆረስ፣
የብልፅግና የጎሳ ፖለቲካን ለማጥፋት በሚል መርህ ይህን ሊል ይችላል ግን እንደ እኔ እይታ ከምርጫ በፊት ይን "ውንጀላ አዘል" መልእክት ከምርጫ በፊት ብዙ ፍሬ ያፈራል ብየ አላስብም፣፣ ለምን ብትል አሁን የዘር ፖለቲካው ከመቸውም ጊዜ የተካረረበት በመሆኑ አንዱ ካንዱ እምነት እሚሰጥበት ደረጃ አደለም፣፣ ስለሆነም የዘር አዘል ፓርቲወችም ሆኑ የራሳቸው ኮንስቲቲወንሲወች የየራሳቸውን ጥግ የያዙበት ወቅት ነው፣፣ አሁን አማራው ብልፅግናን እየጠላው ያለው ኦፒዴኦ ባቦካው የደም ጭቃ ነው፣፣ ማለትም፣ ብልፅግና በኦሄዴዶች በመጠለፉ ብልፅግናን መምረጥ ማለት ኦሄዴድን እንደ መምረጥ እና የኦነግን ተከታታይ እልቂት እንደመጋበዝ ነው፣፣ ለዛ ሲባል አማራው ከብልፅግና ይልቅ አብንን ይመርጣል ማለት ነው፣፣ እንደሚታወቀው ምንም እንኳን አብን በዘር ይደራጅ እንጅ ከነ ኤሄዴድ ተርታ እሚሰለፍ አደለም፣፣ ምክንያቱም አብን ፅኑ የሀገር አንድነት አላማ የያዘ ብቻ ሳይሆን በቀላሉ ወደ ዜግነት ፓርቲ ሪፎርም መሆን እሚችል ነው፣፣ ኦህዴድ ግን ወይ ሀገር ያጠፋል ወይ እራሱ ይጠፋል እንጅ በታምር ኢትዮ ዜጋ ነኝ እማይል የትህነግ ውልድ ስለሆነ፣ ኢዜማ ኦሮምያን ጥለው መውጣታቸው ትክክል ሰለሆነ ያሁኑ የዘር ነክ ሽንቆጣ ወደአብን ማነጣጠሩ ላይ ስህተት እለ እምለው ኢዜማ የወደፊት አጋሩን (ህዝቡን) ካሁኑ ማስቆጣት አልነበረበትም፣፣ ኢዜማ እንደ ስትራቴጅ መያዝ የነበረበት፣ የወደፊት አጋሮችን እርምጃ እያሰሰ እና እየተናበበ በሁዋላ ከጥምር መንግስት በሁዋላ የዘር ፓርቲዎች እንዲከስሙ ማድረግ ነበር፣፣

Horus wrote:
27 Apr 2021, 04:19
ክብረአምላክ
አይምሰልህ! ኢዜማዎች በጣም ጥንቁቆች ናቸው ። አሁን በግልጽ የጎሳ ፌዴሬሽን እንዲፈርስ፣ ሕገ መንግስቱ እንዲለወጥ በሄዱበት ሁሉ እያነሱት ነው። ይህም ማለት ኢዜማ በጎሳ ክልሎች ሄዶ ክልል መፍረስ አለበት የሚል ጽኑ ዜጋዊ ብሎም የብዙ ሚሊዮን ኢትዮጵያዊነት አማኝ ህዝብ ቀልብ እየሳቡ ነው።

ስለዚህ የጎሳ ድርጅቶች ላይ ግልጽ አቋም መያዛቸው ለኢትዮጵያ ወደ ፊት ፖለቲካ አስፈላጊ ነው ። ኦነግ የጎሳ ድርጅት ነው ። ትህነግ የጎሳ ድርጅት ነው። አብን የጎሳ ድርጅት ነው ወዘተ። ይህን ፋክት ማሽኮርመም ስህተት ነው። አብን ከማ ጋር ቅርበት እንዳለውና ከማ ጋር አብሮ መስራት እንደ ሚፈልግ ያውቃል። ኢዜማም እንዲሁ ።

መጀመሪያ ግን የቱ ነው የጎሳ ፓርቲ? የቱ ነው የኢትዮጵያዊ ፓርቲ? ትብለው ሎጂክ ላይ የቆመ ካታጎሪ ማበጀተ እጅግ ቀዳሚው ኮግኒቲቭ ስራ ነው። ይህ ማለት ድርጅቶች ለተለያየ አልማና የስራ ስልት ህብረት አይፈጥሩም ማለት አይደለም ።

ስለ አማራ የታጠቀ ሃይል ሲወራ አብን የተነሳው አንዳንድ አባሎቹ ተብሎ ነው ። ይህ መሰል አባባል አንድ ሰው እርግጠኛ መረጃ ሳይኖረው አይናገርም ።

ሰው ሁሉ ኢዜማና ብልጽኛ አብረው ይሰራሉ፣ መርጅ ያደርጋሉ ምናምን ይባላል። ዉሸት ነው። የኢትዮጵያ አንድነትና መኖር የሚደግፉት የብልጽኛ ክንፍ በትክክል ከኢዜማ ጋር በብዙ ነገር ሊስማሙ ይችላሉ ። ግን ልብ በል የኢዜማ ሶሺያል ዴሞክራሲና ያቢይ መደመር ልማታዊ መንግስት በጣም የለያያሉ።

ዛሬ ግን አቢይና ብርሃኑን አንድ የሚያደርጋቸው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ደህንነት ጉዳይ ነው። ያ ደሞ እጅግ እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው።

ዞሮ ዞሮ ፖለቲካ የስልጣን ጉዳይ ነውና ይህ ሁሉ ተቺና ተቃዋሚ የፖለቲካው ሚዛን ወደሱ ፓርቲ እንዲዘምም ፈልጎ ነውና ይገባኛል።

Re: የኢዜማ ምስጢር ተብሎ የተለቀቀው ሰነድ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኒታ ቁልጭ አድርጎ የሚተነትን ፕሮፌሽናል Situation Analysis ነው

Posted: 27 Apr 2021, 08:45
by gearhead
አብይ ፒፒን የኢዜማ የጭን ገረድ ያረገው ከጥንስሱ ነው!! collective leadership ካልመጣ የጭን ገረድነቱ እስከፍጻሜው ይቀጥላል።ኮሮጆ ገልብጦ ያለውድድር ባሸነፈ ማግስት እለተሞቱን ይጀምራል።ልጆቹም አለዳቦ ይበተናሉ!!እሱም ለማያዛልቅ ፒፒ ከማህበረሰቡ ጋር ይቃረናል!!

ኢዜማ ፒፒን ማብጠልጠሉ ሳያንስ, የመከላከያውን አይን ጠንቁል አይነት መግለጫ ሰጭ ሚስጢር አውጭ ለመሆን ማን ፈቀደለት?? መከላከያ ካወጣው መግለጫ በ180⁰ ተቃራኒ እውነታ ሲያቀርብ መከላከያውም የኢዜማ የጭን ገረድ ነው??

ጀነራል ባጫ ቢያብራሩልን?

Re: የኢዜማ ምስጢር ተብሎ የተለቀቀው ሰነድ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኒታ ቁልጭ አድርጎ የሚተነትን ፕሮፌሽናል Situation Analysis ነው

Posted: 27 Apr 2021, 13:21
by Horus
ክብራምላክ
የእኔ እምነት በዚህ ምርጫ ኢዜማ የተወሰነ ድምጽ በፓርላማ እንዲኖረው እንጂ ሙሉ ስልጣን ለመያዝ አይፈልግም። ኢትዮጵያ ከጎሳ መንገድ ወደ ዜጋ መንገድ ሳትገባ የመንግስት ስልጣን መያዝ የሌቦችና የግብዞች ምኞት ነው። ሌቦች በማንኛውም መንግስት ስር ስለጣን እዘው ሲሾም ያልበላ ይሏል። በጎሳ አደረጃጀት እንኳንስ አገርና መንግስት ፓስቴ ቤት እንኳን ማቋቋም አይቻልም።

ስለዚህ ኢዜማ ከዘርና ዘውግ ድርጅቶች ጋር ለመደራደር ከማስላቱ በፊር አሁን ከሚታመሱት የጎሳ ስልጣን አሳዳጆች ራሱን ለይቶ መገኘት አለበት ። የቴዲ አፍሮ ምክር እዚህ ላይ ነው የሚመጣው፤ አዲስ ንጉስ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ! ጉራ ብቻም ስለዚህ ጉዳይ ነው ሚመክረው!

ወደ ፊት ኢዜማና አብን በጥቅም ከተመሳሰሉ ይቀናጃሉ፤ ዛሬ ግን ፓርቲዎች ሁሉ በጸባያቸው ቢታወቁ ነው ዜጋ የሚነቃው ፤ ማነው በጎሳ ለጎሳ የተደራጀ ? ማነው ለዜጋ በዜጋ የተደራጀ? መንግስትም እንዲሁ ነው ። ለዚህ ነው በአማራ ፒፒና በአብን መሃል ትግል የሚኖረው፣ ፖለቲካ ሁሉ ስለስልጣን ስለሆነ።

ኦነግና ኦሮሞ ፒፒ የሚዋጉት ለዚህ ነው፣ ፖለቲካ ሁሉ ስለስልጣን ስለሆነ።

ኢዜማ ጸረ አማራ ነው የሚለው ቆሻሻ ፕሮፓጋንዳ ግን አለጥርጥር የጎሳ አክራሪነት ካንሰር ለትግሬና ኦሮሞ ተገንጣይ ሊሂቃን ብቻ የታዘዘ በሽታ አይደለም
ያማራ አክራሪንም እንደ ሚለክፍ የሚያሳይ ነው። የእንብደት ምልክቱ ቀሚስ ከፍ ከፍ አንዲሉ !!