Page 1 of 1
ሰበር መግለጫ - በወቅታዊ ሀገራዊና ቀጠናዊ፣ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር፣ የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤቱ የሰጠው መግለጫ!
Posted: 24 Apr 2021, 06:54
by Ejersa
Re: ሰበር መግለጫ - በወቅታዊ ሀገራዊና ቀጠናዊ፣ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር፣ የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤቱ የሰጠው መግለጫ!
Posted: 24 Apr 2021, 07:16
by Hameddibewoyane
የተከበራችሁ የሀገራችን ሕዝቦች፣
ከሦስት ዓመታት በፊት ወደ ለውጥ ጎዳና የገባነው በመንገዱ ላይ ችግሮች አይገጥሙንም በሚል እሳቤ አልነበረም። ሀገራችን ትከሻ ላይ የተቆለለውን የበዛ ችግር ከነውስብስብነቱ ተረድተን እንጂ፤ አቅልለን አይተን አልተነሳንም። ለዘመናት ሲከመር ቆይቶ ወደ ግዙፍ ተራራነት የተለወጠው ሀገራዊና ቀጠናዊ ችግሮች በቀላሉ መወገድ ቢችሉ ጥሩ ነበር።
ነገር ግን ችግሮቹ እንኳን እርስ በእርስ እየተጓተትን ቀርቶ አንድ ሆነንም በጥቂት ዓመታት ውስጥ ድምጥማጣቸው የሚጠፋ አይደለም። ይሄንን በሚገባ አውቀን እስከ መጨረሻው ሕቅታ ዋጋ ለመክፈል ቆርጠን ነው የተነሳነው።
ሀገራችን ያሉባት ችግሮች ምንም ያህል እንደ ምድር አሸዋ ቢበዙ ፈጽሞ ከዜጎቿ አቅም በላይ እንደማይሆኑ ጽኑ እምነት አለን።
የሚፈቱትም ተነጣጥለን ሳይሆን በአንድነትና በትብብር እንደሆነ ገና ከጅምሩ አሳውቀናል።
በወቅቱ ያለ ብዙ ፈተና በአንዲት ጀንበር የተለወጠች ሀገር ትኖረናለች ብለው የጠበቁ ሰዎች እንደነበሩ ግልጽ ነው። ለውጡ ከአንድ አቅጣጫ ይመጣልም ብለውእንደታዛቢ ዳር ቆመው የሚመለከቱ መኖራቸውም እንዲሁ።
ያኔ የለውጥ ጉዞ በጀመርንበት ወቅት ሁሉም ሰው ከፍ ባለ ሞራልና በፌስታ ተሞልቶ የነበረ ቢሆንም፣ ሁሉም በጀመረበት የመንፈስ ከፍታ እንደማያጠናቅቅ ግልጽ ነበር።
ሀገራችን ለዘመናት ስትናፍቀው የኖረችው የተስፋ አድማስ ላይ ደርሰን ሁላችንም የመንካት እድሉ ይገጥመናል ብሎ ማሰቡም ሞኝነት ነው። በየመንገዱ የሚገጥመንን እሾህና ጋሬጣ ሳያቆስለን፣ እባብና ጊንጡሳይነድፈን፣ ሀሩርና ቃጠሎው ሳይለበልበን የምናልማትን የበለጸገች ሀገር መገንባት ብንችልማ ኖሮ ገና ድሮ በአደረግነው ነበር።
በረሃውን ሳናቋርጥና ባህሩን ሳንሻገር ጉዞው ይጠናቀቃል ብለው ያሰቡ ሰዎች ከመጀመሪያውም ተሞኝተዋል። ከፊታቸው የተዘረጋውን ፈተና ቀድመው ያላዩ፣ ጉዞው መሐል ላይ ወገባቸው ዝሎ መንቀጥቀጥ ሲጀምር ቢናደዱ፣ መበሳጨት ያለባቸው በሌላ አካል ሳይሆን በተሳሳተ ግምታቸው ነው።
አሁንም ቢሆን ይበልጥ ወደ ተስፋ ሰገነታችን እየቀረብን በመጣን ቁጥር ፈተናው እንደሚበረታ መረዳት ይኖርብናል። በሀገራችን በተለያዩ ጊዜያት ያየናቸው ግጭቶች፣ የሰላም ማጣትና የደህንነት ስጋቶች በለውጥ ጉዞአችን በእጅጉ ከፈተኑን ፈተናዎች ጎራ የሚመደቡ ናቸው።
መንገድ ያስጀመረንን አንድነት ሊደቁሱ፣ እጅ ለእጅ ያስተሳሰረንን ገመድ ሊበጣጥሱ፣ የጋራ ቤታችንን ሊደረማምሱ የሚቋምጡ ብርቱ ፈተናዎቻች ጉዞ ከመጀመራችን በፊትም ነበሩ፣ አሁንም አሉ።
ምናልባትም መንገዳችን ላይ ልዩ ልዩ ጋሬጣዎችን እየጣሉ ከጉዟችን ሊያስቀሩን የሚሹ አካላትን ድብቅ ፍላጎት በአግባቡ ተረድተን በጥንቃቄና በጥበብ ወደ ግባችን መጓዛችንን እንደማናቆም እስካላሳየናቸው ድረስ በቀሪ ምዕራፎቻችንም ላይ ተከትለውን ይመጣሉ።
የጠላቶቻችን ፍላጎት በጉዞአችን መሐል ወድቀን ግባችንን ሳናሳካ እንድንቀር ነው። በጋራ ቆመን ያጸናነው ቤታችን ፈራርሶ ወደ ትቢያነት ሲቀየር ማየት ይሻሉ። እኛ ደግሞ ለዚያ የተመቸን ሆነንላቸዋል።
አንድ ቤት በሦስት ምክንያቶች ሊፈርስ ይችላል። በግንባታው ወቅት በገጠሙት ችግሮች፣ ከውስጥ ባሉ ሰዎች እና ከውጭ በሚመጡ ኃይሎች።
እነዚህ ሦስቱ አውቀውትም ይሁን ሳያውቁ የሚተባበሩበት ጊዜ አለ። አንዳንድ ጊዜ በዓላማ፣ አንዳንድ ጊዜ በሂደት፣ አንዳንድ ጊዜም በውጤት ይተባበራሉ። ከውስጥ ያሉት ሰዎች በውስጥ ጉዳያቸው ሲጣሉ፤ ከውጭ ያሉ ኃይሎች ቤቱን አፍርሰው ቤቱ የተገነባበትን ቦታ ወይም በቤቱ ውስጥ ያለውን ሀብት መዝረፍ ሲፈልጉ፣ ቤቱ እንዲፈርስ ተባብረው ሊሠሩይችላሉ። ቤቱ ሲገነባ ያጋጠሙት ችግሮች ካሉ ደግሞ ነገሩ “በዕንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ” ዓይነት ይሆናል።
የተከበራችሁ ኢትዮጵያውያን፣
ሁላችንም ልንዘነጋው የማይገባን አንድ ሐቅ አለ። ሀገራችን የጋራ ቤታችን ናት። የሁላችንም ቤቶች በዚያች ትልቅ ቤት ውስጥ የሚገኙ የቤቱ ክፍሎች ናቸው። በየክፍሎቻችን ተወሽቀን ያለነው ሁላችንም የጋራ ቤታችንን አጽንጸን በማቆየት ላይ ተመሳሳይ አቅምና አቋም የለንም። ቤትን ከውጭ የሚመጣ ኃይል ብቻውን አያፈርሰውም። የውስጦቹ ካልተባበሩት በቀር።
የቤቱ ሰዎች የውጭ አፍራሾች በሦስት መንገድ ዐውቀውም ይሁን ሳያውቁ ሊተባበሯቸው ይችላሉ። ሆን ብለው፣ ሞኝ ሆነው እና ተኝተው።
ከሚፈርስ ቤት እንጠቀማለን የሚሉ ሞኝ የቤት ሰዎች አሉ። ከመሥራትና ከመድከም ዋጋ ማግኘት የሚከብዳቸው፤ የቤቱን ፍርስራሽ ሽጠው ማትረፍ የሚፈልጉ የፍርስራሽ ጌቶች አሉ። እነዚህ ሆን ብለው ቤቱ እንዲፈረስ ይሠራሉ። ቤቱ ቶሎ ፈራርሶላቸው ፍራሹን ለመቸብቸብ ስለሚቸኩሉ፣ ከውጭ ሆነው ቤቱን ከሚነቀንቁት ጋር ተባብረው ያፈርሳሉ።
ሌሎቹ ደግሞ በምግቡም፣ በልብሱም፣ በሳሎኑም በምኝታ ቤቱም የሚፈጠርባቸውን ቅሬታ የቤት ማፍረሻ ምክንያት የሚያደርጉ የዋሐን ባለቤቶች ናቸው። ‹የላሞች ጠብ በረቱን ለተኩላ፤ የውሾች ጠብ መንደሩን ለጅብ ይሰጠዋል› እንደሚባለው፣ እነዚህ የቤት ልጆች ከውጭ ያሰፈሰፈውን ጠላት ባለማወቅ የሚያደርጉት ጠብ፣ ከተራ እሰጣገባ አልፎ ሳያስቡት ቤቱን ያፈርሰዋል።
አንዴ ከፈረሰ በኋላ ለውስጦቹ ትርፋቸው ቁጭት ይሆናል። ከመሆኑ በፊት እንጂ ነገሮች ከተበለሻሹ በኋላ መጸጸትና መቆጨቱ ምንምትርጉም የለውም።
ሦስተኞቹ ደግሞ ተኝተው ቤት የሚያፈርሱ ናቸው። የቆሸሸውን ማጽዳት፣ የተሰነጠቀውን መጠገን፣ የጎደለውን ማሟላት፤ የጠመመውን ማቅናት ሲገባቸው ‹እኔ ምን አገባኝ› ብለው ይተኛሉ። አጥሩ ሲፈርስ ሳሎን ሲድረስ ይላሉ፤ ሳሎን ሲፈርስ ምኝታ ቤት እስኪደርስ ይጠብቃሉ፤ ምኝታ ቤቱ ሲፈርስ ጓዳ ተደብቀው በመተኛታቸው የሚተርፉ ይመስላቸዋል። ሁሉም ግን የጊዜ ጉዳይ ይሆናል።
ዛሬ ታላቋ ቤታችን ኢትዮጵያ በዚህ ሁኔታ ላይ ናት። ሦስቱም ዓይነት ልጆች አሏት። ከውጭ ጠላቶቿ ጋር ይሁነኝ ብለው በዓላማለማፍረስ የሚሠሩ፤ በዓላማ ባይገጥሙም በውጤት ከውጭ አፍራሾች ጋር የሚሠሩ፤ ቤታቸው ሲቃጠል እያዩ ከመንቃት ይልቅ በሙቀቱ ተከናንበው የተኙ።
ይህ ወቅት ለኢትዮጵያ ከወሳኝ ወቅቶች አንዱ ነው። በአንድ በኩል ፍትሐዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒ ምርጫ አድርገን በሕዝብ ድምጽ የሚጸና መንግሥት ለመመሥረት በሂደት ላይ ነን።
በሌላ በኩል ደግሞ የሀገራችን ከፍታ አንዱ ማሳያ የሆነውን የሕዳሴውን ግድብ ሁለተኛውን ዙር ሙሌት ለማከናወን እየተጋን ነው። ከእነዚህ ጎን ለጎን የኢትዮጵያ ግሥጋሴ ከሚያሠጋቸው የውጭና የውስጥ ጠላቶች ጋር በየአቅጣጫው ግንባር ለግንባር ገጥመናል።
ኢትዮጵያ እነዚህን ሦስት ፈተናዎች አልፋ ግቦቿን ካሳካች፣ ከዚያ በኋላ ለማንም በቀላሉ እጅ የማትሰጥ የሁላችን መመኪያ ሆናትወጣለች።
ይህ እንዳይሳካ ‹ከምንጩ እናደፍርሰው፣ ከእንጎቻው እንሰቅስቀው፣ ከእሸቱ እናጠውልገው› የሚሉ የማሰናከያድንጋዮች በየአቅጣጫው ተነሥተዋል። ወሳኙ የእነርሱ መነሣት አይደለም፤ የእኛ ምላሽ እንጂ።
ውድ የሀገራችን ሕዝቦች፣ከለውጡ ጅማሬ አንሥቶ የገዛ ዛፋችንን ከዛፉ በተቆረጠ ጠማማ እንጨት የመቁረጥ አዝማሚያ መኖሩን እየተናገርንም እየታገልንም ነበር። በተለያየ አቅጣጫ የሚወረወረው ድንጋት በቤታችን ላይ የሚያደርሱትን አደጋ ለመግታት፣ የፖለቲካ አመራሩና የጸጥታ አካሉ መሥዋዕትነት የተከፈለበት ትግል አካሂዷል። ከጁንታው ጋር የተደረገው ትግል የዚህ አንዱ ማሳያ ነው።
እነዚህ አካላት ዛሬም አልጠፉም። የተለያዩ ብሔሮችን ስሞች ይዘው፣ ሲመች በሰላም ሳይመች በጠመንጃ የላኪዎቻቸውን ዓላማ ለማሳካት እየሠሩ ነው።የእነዚህን ተልዕኮ ያልተረዱ የዋሖች ደግሞ ሀገር እንድትፈርስ ባይፈልጉም ሀገር እንድትፈርስ ግን እየሠሩ ነው።
የቤቱ ጥያቄ የሚመለሰው መጀመሪያ ቤቱ ሲኖር መሆኑን ዘንግተውታል። ቤት እያፈረሱ ስለ ቤት ለመወያት ይፈልጋሉ። ‹ቤቴን እጠብቃለሁ፤ ሙግቴንም እሟገታለሁ› የሚሉ አባቶች ልጆች መሆናቸውን ረስተውታል። ስለ ላሟ ወተት የሚኖረው ጥያቄ የሚመለሰው መጀመሪያ ላሟ ስትኖር መሆኑን ረስተውታል። ከእነዚህ ከሁለቱ ጋር ተደምረው ‹ምን አገባኝ› የሚሉ ዜጎችም አሉ።
ምድር ቤቱሲቃጠል እሳቱ ሰባተኛ ፎቅ ላይ የሚደርስ የማይመስላቸው። ወይ ለመገንባት ወይ ለመመከት አንዳች የማያደርጉ፡፡ እሳቱንከመከላከል ይልቅ በሙቀቱ ተመቻችተው ያንቀላፉት ጭምር የሀገራችን ችግሮች ናቸው።
አሁን በአለንበት ጊዜ ሦስት ወሳኝ ዓላማዎቻችንን በጽናት ማሳካት ይኖርብናል። በመጀመሪያ አንድ ወር ያህል ጊዜ የቀረውን ምርጫ ውጤታማ እናድርገው። በነቂስ ወጥተን ካርድ እንውሰድ። ሁላችንም ይበጀናል ያልነውን እንምረጥ።
የፈለግነውን እንዳንመርጥ እንቅፋት የሚሆንብን የትኛውም አካል እርሱ የኢትዮጵያ ጠላት ነው። የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን እየተቋቋምን፤ ችግሮችን እያረምን፣ ጉድለቶችን እየሞላን ምርጫውን ውጤታማ እናድርገው። ይሄንን ምርጫ በድል ተወጣነው የምንለው ሂደቱ የሚጠበቅበትን ደረጃ ለማለፍ ከቻለ ነው። ለዚህ ደግሞ መራጩ ሕዝብ፣ ተመራጮች እና የምርጫ ቦርድ ሀገራዊ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ አደራ እንላለን።
ሁለተኛ ከምርጫው ጎን ለጎን ግድባችንን ባቀድነው መንገድና ጊዜ መገንባትና ሁለተኛውን ዙር የውኃ ሙሌት ማከናወን አለብን።
የትኛውንም ዓይነት ጫና ተቋቁመን፤ የውስጥና የውጭ ፈተናዎቻችንን አልፈን እንሞላዋለን። ኢትዮጵያን መውደዳችንን የምናሳየው የኢትዮጵያን ጉዞ በማቀላጠፍ እንጂ በማደናቀፍ አይደለም። በእሳት ላንቃ ውስጥ እያለፍንም ቢሆን ማድረግ ያለብንን ማድረግ አለብን።
በያዝነው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ግድባችንን ሞልተን ኃይል ማምረት እንጀምራለን።
በየአቅጣጫው የምናየው የወገኖቻችን አሰቃቂ ግድያ፣ ማፈናቀል፣ ቤትና ንብረት ማውደም፣ ነውጥና ሸፍጥ ሁሉ በሀገር ውስጥ ብቻ የተመረተ አይደለም። አብዛኛው ጥፋት በውጭ ተመርቶ በሀገር ውስጥ የሚገጣጠም ጥፋት ነው። ግጭቱንና ጥፋቱን ከውጭ አስመጥተው በሀገር ውስጥ የሚገጣጥሙት የእፉኝት ልጆች ናቸው። በዚህ ዓመት መጀመሪያ የእፉኝቶችን ዋና መፈልፈያ አፍርሰነዋል።
ከዚህ በፊት ፈልፍሎ እዚህና እዚያ የጣላቸው ግልገሎቹ ግን አሁንም ይቀራሉ። የትኛውንም ዓይነት የብሔርና የእምነት ስም ቢይዙ፤ ከየትኛው የውጭ ኃይል የሚረዱትን ገንዘብና መሣሪያ ቢጨብጡ ኢትዮጵያን ይፈትኗት ይሆናል እንጂ አያሸንፏትም።
መጀመሪያ በውስጣችን ያሉትን ባለ ሁለት በላዋዎች እናጸዳለን። ቀን ቀን ለኢትዮጵያ የሚሠሩ የሚመስሉ፤ ሌሊት ሌሊት በኢትዮጵያ ላይ የሚዶልቱ አሉ። እነርሱ ከውጭ ጠላቶቻችን በላይ ዋነኞቹ ጠላቶቻችን ናቸው። አጥር ላይ ተቀምጠው፣ አሸናፊውን አይተው፣ ከተመቻቸው ሊገቡ፣ ካልተመቻቸው ሊሸሹ የሚያስቡ መኖራቸውን ዐውቀናል። ወቅቱ የምርጫ ነውና መምረጥ አለብን። ወይ እነርሱን እናጸዳለን ወይ ኢትዮጵያን አሳልፈን እንሰጣለን። የኛ ምርጫ ኢትዮጵያን ለእነርሱ ስንል መሠዋት ሳይሆን፤ እነርሱን ለኢትዮጵያ ስንል መሠዋት ነው።
በአጠቃላይ ምርጫውን ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ፍትሐዊ ለማድረግ፤ ግድባችንን በታቀደለት መንገድ ገንብተን ሁለተኛውን ዙር የውኃ ሙሌት ለማከናወን፤ እንዲሁም ኢትዮጵያን ከውስጥና ከውጭ ጠላቶቿ ታድገን ወደሚገባት ደረጃ ለመውሰድ እንድንችል፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ በንቃትና በብስለት ከመንግሥት ጎን እንዲቆም ጥሪ እናደርጋለን። ቆም ብለን እናስብ፤ ከሁሉም በፊት ኢትዮጵያን እናስቀድም።
በፌዴራልና በክልል የምትገኙ የጸጥታ አካላት፣ ተቀናጅታችሁና ተናብባችሁ በመሥራት የኢትዮጵያንና የኢትዮጵያውያን ሰላምና ደኅንነት እንድታስጠብቁ እናሳስባለን።
የሚደረጉ ማናቸውም የፖለቲካና የመብት እንቅስቃሴዎች ይደገፋሉ። የትግላችን ውጤቶች ናቸውና። እነዚህ የመብትና የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ግን ኢትዮጵያን እንዲያናውጡ አንፈቅድም። ፖለቲካዊ ጨዋታውን ከጨዋታ ሜዳ ውጭ ለማድረግ ለሚፈልጉት ኃይሎች፣ ትእግሥታችን ማለቁን በዚሁ አጋጣሚ ልንነግራቸው እንፈልጋለን።
ሁሌም እንደምንለው፤ በጽናትም እንድምናምንበት፣ ለኢትዮጵያ ፈተና ብርቋ፣ ድል ማድረግም ሰበር ዜናዋ አይደለም። ከዚህ በላይ አልፋ ዛሬ ላይ ደርሳለች።
ይሄንን አልፋ ነገ ላይ ትገኛለች። ኢትዮጵያ ማሸነፏ ላይቀር እንዳታሸንፍ ሲታገሉ የኖሩትን ትታዘባቸዋለች፤ በታሪክ ሂደትም ትቀጣቸዋለች። እርሷ ግን ወጥመዱን በጣጥሳ፣ ሰንኮፉን ነቃቅላ፣ አዚሙን አስወግዳ ያሰበችበት ትደርሳለች።
ኢትዮጵያ እስካሁን የቆየችውም ወደፊትም የምትቆየውም፣ በእኛ በመስዕዋት ልጆቿ ደምና አጥንት ነው። ዛሬ እኛ የምንከፍለው ዋጋ፣ ነገና
ከነገወዲያ ሀገራችንን ወደማይቀለበስ የብልጽግና ከፍታ ላይ እንደሚያደርሳት ምንም ጥርጥር የለውም።
የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት
ሚያዚያ 16፣ 2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ
Re: ሰበር መግለጫ - በወቅታዊ ሀገራዊና ቀጠናዊ፣ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር፣ የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤቱ የሰጠው መግለጫ!
Posted: 24 Apr 2021, 08:27
by Lakeshore
ይሄ ሁሉ አንቶ ፈንቶ በንድ ቃል የጥቃለላል። ምንም ያሉት ነገር የለም አርሚጃ አየተወሰድ ነው ይህንንማ ባለፈው ፫ ኣምት ሲሉት የነበረ ነው። የህዝብ ቁጣ ይስፈራቸው ሆዳሞች ኣሉ ለመባል ብቻ የቃላት ዲሪቶ ያሰሙበት ነው። ነገረውናል አኮ መከላከያ ኣቅቶታል ብለው። አና ኣሁን ይማራው የኣሳያቸዋል አንዴት አንደሚቻል አና አነሱንም ደናቁርቶቹን ኣባሮ እውነተግና የህዝብ ተውካዮቹን ያስቀምጣል።
በመጀመሪኣ በምን መስፈርት ነው የደህንንት ሃላፊ አንዲሁም ሌሎቹ በቦታው የተቀምጡት። ስንት ኣይነት ኣዋቂ ዎች ባሉበት ኣገር ኣንዱ መልሱ አነ ጀነራል ኣሳምነውን አና የኣማራውን ጋንቴ ዶችቶር ኣሳለፈው ሰልሰጡ ነው። አና ኣሁንም ኣማራን በተሻለ ዋጋ ለመሸጥ የሚመለሱ ነው ብሎ ማሰብ አነ ተመስገን አና ገዱን ኣገኝ ሁን ስልቡ ደመቀ መኮንን መጃጃል ነው። ተግሉ መቅጠል ኣለበት ወንጀለኞች በሙሉ ለፍርድ ኣሁኑኑ ይቅረቡ አርምጃ ብቻ ሳድይሆን አርሚጃው ሚን አንድሆነ ክንሚስላቸው ለህዝብ ይቅረብ፣ ምክኛቱም ህዝቡ አነማን አንደሆኑ ስልሚያቃቸው። ኣምራው መታጠቅ ኣለበት የውጭወም ዲኣስፖራ በገንዘብ የረዳል።
ሌላው ደግሞ የኣምራን ብሶት ከግድቡ ጋር ለማገናኘት የሚሞከረው የከብት ጋሎች የወረደ ፖሊቲካ ኣይሰራም ኣማራ አየሞተ ግድብ ግድብ ማለት ምንም ትርጉም የለውም ኣማራ ሞቶ አሌክትሪኩ ማን ሊጠቀምበት ነው ጋላ ስለዚህ ህልወና ና ነጻነት ነው በመጀመሪያ አስከዛሬ የልግደቡ ኖረናል።ይሄ የለባ ኣበይ መንግስት መብራቱስ ቢመንጭ ወደ ኦሮሚያ ካልዘርጋን ሊል ስለሆነ መጀመሪኣ ጋላ ቦታውን መያዝ ኣለበት አንድ ወያኔ
Re: ሰበር መግለጫ - በወቅታዊ ሀገራዊና ቀጠናዊ፣ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር፣ የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤቱ የሰጠው መግለጫ!
Posted: 24 Apr 2021, 12:02
by gearhead
Sounds like the first collectively delivered adult communique in three years. Sobering, but not exactly refreshing.
Three years of differing to a one man populist fervor, an openly defiant ezema that had made unrefuted insinuation that PP is just its mule has left PP without a party structure, without a program and with a discombobulated base.
Otherwise, why would OPDO that at one time had a 5 million cadre base be begging for people to register? All it had to do is bring itself and two others to the poll! Same works across all other regions 3million ANDM 2 million South somalia regions combined would have delivered a competition!!
The base has no confidence with a stolen roadmap and the position of PP chair who sounds ezema than an evolving EPRDF! When the base is lethargic, the population is disinterested.
Re: ሰበር መግለጫ - በወቅታዊ ሀገራዊና ቀጠናዊ፣ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር፣ የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤቱ የሰጠው መግለጫ!
Posted: 24 Apr 2021, 12:23
by Abere
How is this a Breaking News? This same old Sh!t. Nothing New. It makes no difference - violence and massacre has been the hallmark of OLF-PP government at Arat Killo. If there is any better degree of efficiency in destroying an entire city we saw in Shashemene, Ataye, etc. that probably would be seen. It ain't change the level of cruelty deployed by ODP-OLF.
Re: ሰበር መግለጫ - በወቅታዊ ሀገራዊና ቀጠናዊ፣ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር፣ የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤቱ የሰጠው መግለጫ!
Posted: 24 Apr 2021, 14:16
by Dawi
Abere wrote: ↑24 Apr 2021, 12:23
How is this a Breaking News? This same old Sh!t. Nothing New. It makes no difference - violence and massacre has been the hallmark of OLF-PP government at Arat Killo. If there is any better degree of efficiency in destroying an entire city we saw in Shashemene, Ataye, etc. that probably would be seen. It ain't change the level of cruelty deployed by ODP-OLF.
Abere,
If you're referring to the Amhara protest who called Abiy the leader of OLF-PP, it need to be read and taken as only metaphorically speaking.
There's a qualitative difference between OLF and p2. Abiy/P2 are reformers; if he is personally related to OLF in blood as an Oromo and consequently in the common struggle against TPLF/EPRDF of the past, no one should be surprised. Similarly, he also had a lot of things in common with other TPLF opponents like the G7 as well.
So, when he told the story of passing tips to OLF, G7 during the struggle to save lives, it was part of a common cause responsibility of fellow activists therefore,
that priest's in the Amhara protest conclusion on Abiy was absolutely wrong.
Having said that, I kind of liked Abiy's tone in that last presentation regarding of the coming election; he has indicated of willing to turn a dictator if the transition requires it. For sure, he has told us clearly that he ain't resigning or agreeing in "transitional government" come rain or shine.
Looking at all the confusion, I am willing to give him the shot at the election! What do we have to lose? We already know a "transitional government" would be chaos.
Re: ሰበር መግለጫ - በወቅታዊ ሀገራዊና ቀጠናዊ፣ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር፣ የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤቱ የሰጠው መግለጫ!
Posted: 24 Apr 2021, 15:00
by Abere
Dawi,
I honestly don't see any qualitative difference between Abiy Ahmed and OLF or Abiy Ahmed and TPLF. Qualitatively it is the same OLF, but at different level of intensity and pervasiveness applying a different strategy - by stalking and stealing power from TPLF and doing things on OLF's favor. He could not do that out right unless he sugar-coated and used sweet words to lure innocents. Yes, he is a power hungry man , anyone who read his በሬ ካራጁ style book tells it all. He openly declared he is the 7th ኦሮሙማ in the Guji Aba Geda rank, probably that was also a tactic for many to fatalistically believe his words.ጦርነት ከፈታው ወሬ የፈታው ይባላል. No wonder, even in Tigray where civilization and history are as old as Ethiopia many believed the dead Meles Zenwi or Seyoum Mesfin would pop up to life, like the millions who did not believe Hailesellasie was dead. That is what devilish power hungry and [ deleted ] men used. Thus, he will try to hang on power for a while until some forces will take him off the power hook. Election in Ethiopia has no meaning - it is like drinking a muddy contaminated water. Drinking that kind of unsafe water can cause a simple diarrhea and take the life of the person who took risk to quench his thirst. So, Aby's ODP-OLF election is like that. The country can not adopt a safe road under such confusion being maneuvered by a leader in his own spokesperson mouth said convince or confuse is the rule of the game. My advice is, don't election under all the confusions. አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ ነው። What is so sad is the absence of an adult or an elderly in Ethiopian politics that is to be listened so as restore sanity. This whole Orommuma Aba Geda sh!t is taking teh country down the drain. It should openly told and stopped. This is carzy.
Dawi wrote: ↑24 Apr 2021, 14:16

Posted: 27 Apr 2021, 01:42
by Dawi
Abere,
Look my friend, by just considering the document Ezema "leaked", I expect these folks are on the ground making good judgement of Abiy/p2 fairly; may be you can & I hear you but, I am in no position from far away to assume p2 is equal to OLF?
It doesn't make any sense to me; chances are as the "leak' said, Abiy's government doesn't have strong enough army to stop all the ethnic pimps who go around committing genocide everywhere in the country.
Abere wrote: ↑24 Apr 2021, 15:00
Dawi,
I honestly don't see any qualitative difference between Abiy Ahmed and OLF or Abiy Ahmed and TPLF. Qualitatively it is the same OLF, but at different level of intensity and pervasiveness applying a different strategy - by stalking and stealing power from TPLF and doing things on OLF's favor. He could not do that out right unless he sugar-coated and used sweet words to lure innocents. Yes, he is a power hungry man , anyone who read his በሬ ካራጁ style book tells it all. He openly declared he is the 7th ኦሮሙማ in the Guji Aba Geda rank, probably that was also a tactic for many to fatalistically believe his words.ጦርነት ከፈታው ወሬ የፈታው ይባላል. No wonder, even in Tigray where civilization and history are as old as Ethiopia many believed the dead Meles Zenwi or Seyoum Mesfin would pop up to life, like the millions who did not believe Hailesellasie was dead. That is what devilish power hungry and [ deleted ] men used. Thus, he will try to hang on power for a while until some forces will take him off the power hook. Election in Ethiopia has no meaning - it is like drinking a muddy contaminated water. Drinking that kind of unsafe water can cause a simple diarrhea and take the life of the person who took risk to quench his thirst. So, Aby's ODP-OLF election is like that. The country can not adopt a safe road under such confusion being maneuvered by a leader in his own spokesperson mouth said convince or confuse is the rule of the game. My advice is, don't election under all the confusions. አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ ነው። What is so sad is the absence of an adult or an elderly in Ethiopian politics that is to be listened so as restore sanity. This whole Orommuma Aba Geda sh!t is taking teh country down the drain. It should openly told and stopped. This is carzy.
Dawi wrote: ↑24 Apr 2021, 14:16
Abere,
If you're referring to the Amhara protest who called Abiy the leader of OLF-PP, it need to be read and taken as only metaphorically speaking.
There's a qualitative difference between OLF and p2. Abiy/P2 are reformers; if he is personally related to OLF in blood as an Oromo and consequently in the common struggle against TPLF/EPRDF of the past, no one should be surprised. Similarly, he also had a lot of things in common with other TPLF opponents like the G7 as well.
So, when he told the story of passing tips to OLF, G7 during the struggle to save lives, it was part of a common cause responsibility of fellow activists therefore,
that priest's in the Amhara protest conclusion on Abiy was absolutely wrong.
Having said that, I kind of liked Abiy's tone in that last presentation regarding of the coming election; he has indicated of willing to turn a dictator if the transition requires it. For sure, he has told us clearly that he ain't resigning or agreeing in "transitional government" come rain or shine.
Looking at all the confusion, I am willing to give him the shot at the election! What do we have to lose? We already know a "transitional government" would be chaos.
Re: ሰበር መግለጫ - በወቅታዊ ሀገራዊና ቀጠናዊ፣ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር፣ የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤቱ የሰጠው መግለጫ!
Posted: 27 Apr 2021, 02:23
by Tiago
How is this a Breaking News? This same old Sh!t. Nothing New. It makes no difference - violence and massacre has been the hallmark of OLF-PP government at Arat Killo. If there is any better degree of efficiency in destroying an entire city we saw in Shashemene, Ataye, etc. that probably would be seen. It ain't change the level of cruelty deployed by ODP-OLF.
The same thing from detested ,shifty Abiy's government.Abiy knows very well his pp is largely a spent force in Amhara region but tries to hoodwink the amharas by pretending to be caring.Abiy ahmed is the most hated person in amhara kilil period.