Page 1 of 1

የጁንታው አባላት ከሃገር ለመውጣት ያደረጉት ጥረት በመከላከያ ሰራዊት ከሽፏል - ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ

Posted: 23 Apr 2021, 15:55
by Ejersa

የጁንታው አባላት ከሃገር ለመውጣት ያደረጉት ጥረት በመከላከያ ሰራዊት መክሸፉን የመከላከያ ሰራዊት የግንባታ ስራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ ተናገሩ።

ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ፥ ከሃገር ለመውጣት ከሞከሩት የጁንታው አባላት መካከል አብዛኛዎቹ መደምሰሳቸውን እና የተወሰኑት ወደኋላ ተመልሰው ሸለቆ ውስጥ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

ከሃገር ለመውጣትም መታወቂያ በማዘጋጀትና ስማቸውን በሌላ ማንነት በመቀየር በሱዳንና በአማራ ክልል አቋርጠው ለመውጣት መሞከራቸውንም ገልጸዋል፡፡
ይሁን እንጅ ይህ ሙከራና እቅዳቸው ከሽፎ መደምሰሳቸውን ተናግረዋል፡፡

ቀሪዎቹም መውጫ ቀዳዳ ስለሌላቸው መከላከያ ሰራዊት እየተከታተለ እርምጃ መውሰዱን ይቀጥላልም ነው ያሉት፡፡

በመግለጫቸው በትግራይ ክልል ሄሊኮፕተር ተመቷል ተብሎ በጁንታው አባላት የሚናፈሰው አሉባልታ የተለመደ የሃሰት ወሬ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

ሌተናል ጀኔራል ባጫ በአጣየ እና አንዳንድ አካባቢዎች ጥቃት ለተፈጸመባቸው ወገኖች የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸው ለመላው ህዝብም መጽናናትን ተመኝተዋል።
ምንጭ-FBC

Re: የጁንታው አባላት ከሃገር ለመውጣት ያደረጉት ጥረት በመከላከያ ሰራዊት ከሽፏል - ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ

Posted: 23 Apr 2021, 16:55
by Fiyameta
It's sealed! No way out agame! :lol: :lol: :lol: :lol: