Page 1 of 1

አንደኛው የኢዜማና ብልጽግና ፓርቲዎች ክርክር ፤ ቁልጭ ያለው የዜጋና የጎሳ ፖለቲካ ቅራኔ! በስዩም ተሾመ ትንተና?

Posted: 16 Apr 2021, 13:36
by Horus
በቅድሚያ በትክክል ስዩም እንዳለው በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ዉሃ የሚያነሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ብልጽግና እና ኢዜማ ናቸው ። ይህ አንዱ ትክክለኛ መደምደሚያ ነው ።

ሁለተኛ በትክክል ስዩም እንዳለው ብልጽግናን ተቀባይ ፓርቲ የሚያደርገው አቢይ ብቻ ነው ። ብልጽግና ማለት አቢይ ማለት ነው። አለ አቢይ የብልጽግና ፓርቲ የሚባል ነገር አይኖርም። አለ አቢይ ብልጽግና ማለት ኢህአዴግ የሚባል የጎሳ ጥርቃሞ በትህነግ የተፈጠረ ስብስብ ነው።

ሶስተኛ፣ የጎሳ ፖለቲካ እኔ ዴሞክርሲ ሳይሆን ኤትኖክራሲ ነው የምለው። ስለሆነም የጎሳ ፓርቲ የፖለቲካ ፓርቲ አይደለም ። ይህ እጅግ መሰረታዊው ያቢይ ችግር ነው ። አቢይ አህመድ በኢሃዴግ ላይ ቆሞ ዴሞክርሲ ሊያመጣ በፍጹም አይችልም ። ይህ እጅግ መሰረታዊ ሃቅ ገና በመጀመሪያው ክርክር ግልጽ እየሆነ ነው።

አቢይ በግል አቋሙ የኢዜማ አባል ቢሆን የሚቀለው ሰው ነው ።

አራተኛ፣ ይህ ክርክር በጣም የሚፈለግና የሚደገፍ ነው ። ምክንያቱም ይህ ክርክር ያገራችን ፖለቲካ እውነተኛ ገጽታና ይዘት ማለትም ዜጋዊና ጎሳዊ መንገዶች መካከል ያለው ልዩነትና ትግል ነው። በዚህም ምክኛት ነው አሁን ባለበት ከቀጠለ ብልጽግ ና አምባገነን ፓርቲ እንደ ሚሆን ስይታለም የተፈታ ነው ።

አምስተኛ፣ ስዩም በትክክል እንዳለው አቢይ አሁን በያዘው አቋሙ ከጸና ወደ ፊት በቅንጅት የኢትዮጵያዊነት ፖለቲካ የሚያራምደው ከኢዜማ ጋር እንጂ ከኢሃድጋዊ ጎሳዊ ጥርቃሞች ጋር በመጨማለቅ አይደለም ።

ኤትኖክራሲ ማለት የጎሳ አገዛዝ ማለት ነው ። ዴሞክራሲ ማለት ሕዝባዊ አገዛዝ ማለት ነው ። ይህ ነው አንዱና ብቸኛው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ቅራኔ እምብርት !

ስዩም ተሾመ፣ ድንቅ ትንተና !!


Re: አንደኛው የኢዜማና ብልጽግና ፓርቲዎች ክርክር ፤ ቁልጭ ያለው የዜጋና የጎሳ ፖለቲካ ቅራኔ! በስዩም ተሾመ ትንተና?

Posted: 16 Apr 2021, 13:47
by Horus

Re: አንደኛው የኢዜማና ብልጽግና ፓርቲዎች ክርክር ፤ ቁልጭ ያለው የዜጋና የጎሳ ፖለቲካ ቅራኔ! በስዩም ተሾመ ትንተና?

Posted: 16 Apr 2021, 14:29
by Za-Ilmaknun
So far EZEMA is beating all rivals pants down. They are so well polished, sharp and charismatic. They define politics in modern day standards. Sad to see such politicians may not have the chance to lead the country.

Re: አንደኛው የኢዜማና ብልጽግና ፓርቲዎች ክርክር ፤ ቁልጭ ያለው የዜጋና የጎሳ ፖለቲካ ቅራኔ! በስዩም ተሾመ ትንተና?

Posted: 16 Apr 2021, 16:24
by Tiago
ብልጽግና party is simply EPDRF. on this round of discussion PM Abiy's ብልጽግና Party is thrashed . [