Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Thomas H
- Senior Member
- Posts: 13066
- Joined: 27 Jan 2007, 16:30
- Location: Kaliti
-
Contact:
-
Thomas H
- Senior Member
- Posts: 13066
- Joined: 27 Jan 2007, 16:30
- Location: Kaliti
-
Contact:
Post
by Thomas H » 14 Apr 2021, 09:54
That is it !Game over! Abiy Zinabu Ahmed threw in the towel
በዓብይ አማካሪ ደብተራው ዳንኤል ክብረት ትእዛዝ ጦርነቱ እንዲቆም እና በሽማግሌዎች እርቅ አንዲያልቅ ፀሎት ሊጀመር ነው
የትግራይ ጦርነት እንዲቆም በሁሉም ቤተ እምነቶች ሥርዐት እና ደንብ መሠረት በሁሉም ሚዲያ ተቋማት የቀጥታ ስርጭት ሽፋን የሚያገኝ የጸሎት መርሐ ግብር ከሚያዚያ 7-14 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ገለጹ።
በዚህ የጸሎትና የምህላ መርሐ ግብር ላይ ስለ ትግራይ ጦርነት መቆም ፣ ስለ ሀገር ሠላም፣ ስለ ወንድማማቾች መገዳደል፣ ስለ ኮቪድ 19 ቫይረስ ወረርሽኝ መጨመር፣ ስለ ማንነት ተኮር ጥቃት ፣ ስለ ህዳሴ ግድብ ከፈጣሪ ጋር የምንገናኝበት የጸሎት ሥነሥርዓት ይካሔዳል ብለዋል።
ሐሙስ ሚያዝያ 7/2013 ዓ.ም የሁሉም የሀይማኖት ተቋማት አባቶች በተገኙበት የጸሎት መርሐ ግብሩ መጀመሩ ይበሰራል ያሉት ጠቅላይ ጸሐፊው ጸሎቱ አርብ ሚያዝያ 8 ቀን 2013 ዓ.ም በሁሉም እምነት ተቋማት በይፋ የሚጀመር ይሆናል ብለዋል። አያይዘውም በዚህ የጸሎትና የምህላ መርሐ ግብር ላይ መላው ኢትዮጵያዊያን አማኞች ከአልጋቸው በመውረድና መሬት በመተኛት በጸሎት የሚተጉበት አዋጅ እንደሚሆን ይጠበቃል።
አያይዘውም ሁላችንም ከልባችን ሆነን በጸሎቱ ከበረታን የትግራዩ ጦርነት እንደሚቆም እና ከፈጣሪያችን የምህረት ምላሽ እንደምናገኝ ምንም ጥርጥር የለውም በማለትም አምና በኮቪድ19 ወረርሽኝ ወቅት እንዳደረግነው ሁሉ በተያዘው አጭር ጊዜ ውስጥ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ፣ ከተራው እስከ መራሄ መንግስት ድረስ እንደ ሰብአ ነነዌ ሁሉ የምናዝንበት ፣ የምናለቅስበት፣ ወደ ፈጣሪ የምንጮህበት ጊዜ ይሆናል ብለዋል ።
ፈጣሬ ዓለማት ልዑል እግዚአብሔር ጸሎትና ምህላችንን ይስማን!

-
Thomas H
- Senior Member
- Posts: 13066
- Joined: 27 Jan 2007, 16:30
- Location: Kaliti
-
Contact:
Post
by Thomas H » 14 Apr 2021, 13:49
-
Thomas H
- Senior Member
- Posts: 13066
- Joined: 27 Jan 2007, 16:30
- Location: Kaliti
-
Contact:
Post
by Thomas H » 14 Apr 2021, 22:14
የዓብይ እና የኢሳያስ ወታደሮች ለማዳበሪያ አገልግሎት ሲውሉ የሚያሳይ ቪዲዮ