የተሳሳተ የውዳሴ መድረክ ውጤቱ የተሳሳተ እንደሚሆን ግልፅ ነው
➵ ⁽⁽የምስራቅ አፍሪካ ፖሊሲ ምርምር ኢንስቲትዮት⁾⁾ የሚባለው መስሪያ ቤት የማን ነው? ስራው ምንድን ነው ? የሚለውን እናቆየውና ፣ በዓለምአቀፍ ደረጃ ያለውን የዲፕሎማሲ ገፅታም እናቆየውና ፣ ዐቢይ አሕመድ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ስራዎች ከተመደበ ወዲህ የኢትዮጵያና የምስራቅ አፍሪካ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ⁽⁽አመርቂ⁾⁾ ነው ወይስ ⁽⁽አሰቃቂ⁾⁾ የሚለውን ከጥቂት አገራት አንፃር እንየው።
በጥቅል ምልከታ በዶር ወርቅነህ ገበየሁ የተሠራው የውጭ ጉዳይ ሪፎርም ፣ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ማሻሻያ እና የዲፕሎማሲ ሙያተኞች ስምሪት ውጤት ከኤርትራ ⁽⁽ታርቆ⁾⁾ ከሌሎች የመጣላት ዲፕሎማሲ ነው።
● ኢትዮ- ሱዳን : ዛሬ ስለጋራ መሠረተ ልማት አይደለም የሚወራው ። ሰፊዋ ጎረቤት አገር ጋር ዛሬ ከይፋዊ ጦርነት (conventional war) ዋዜማ ላይ ነን።
● ኢትዮ-ኬንያ : ለረጅም ጊዜ በሰላማዊ ግንኙነት የምታወቀው ጎረቤት አገር ኬንያ በፀጥታው ምክር ቤት ሳይቀር ከኢትዮጵያ በተቃራኒ ቆማ የተገኘች አገር ነች። በርዕሰ-ብሔር ሳህለ ወርቅ የማግባቢያ ጉብኝት ለማለዘብ ሲሞከር የነበረው ጥረት ወር አልሞላውም። ጠለቅ ብለን እንየው ከተባለ በኦሮሞ ልሒቃን የሚቀነቀነው ⁽⁽የኩሽ ህብረት ⁾⁾ የኬንያም ስጋት እንደሆነ መግለጿን ስንሰማ ነበር።
● ኢትዮ-ኤርትራ : ከጅምሩ በበጎ ታይቶ ለሰላም ኖቤል ሽልማት ምክንያት ቢሆንም መተማመን ያለበት ግንኙነት እንዳልሆነ ብዙ ዝርዝር ሳይገባ የሚያውቅ ያውቃል። ዛሬ ወደትግራይ ያዘመተውን ሠራዊት ለማስወጣት ሲያንገራግር ከርሞ ⁽⁽ለመውጣት ተስማማ⁾⁾ ብለን የዘገብንለት ነው። ስለመጪው ሁኔታ የአንዳንዶችን ስጋት ልዝለለው።
● ኢትዮ-ጂቡቲ : ጂቡቲዎች ዛሬ እንደቀደመው ጊዜ ከኢትዮጵያ ጋር ስለኢኮኖሚና ፖለቲካ ውህደት እያወሩ አይደለም። ከኤርትራ ጋር በተገባው ሃኒሙን ጥርጣሬ የገባቸው የኢትዮጵያ ቀውስ ታዛቢ ሆነው የዚህች አገር ነገር እያሰጋቸው ያሉ ናቸው። ጂቡቲ የነ ወርቅነህ ገበየሁ ኢጋድ እና እነብርሃኑ ፀጋዬ መኖሪያ ብትሆንም በወቅቱ አለምአቀፍ ጫና የዲፕሎማሲ ድጋፏን ፍለጋ ከገዱ አንዳርጋቸው እስከ ሳህለወርቅ ተመላልሰዋል።
● ኢትዮ - ሩዋንዳ : አስከፊ ትዝታዋን አራግፋ በልማት ላይ ያለችው ሩዋንዳ ፊቷን አዙራብን ፕረዝደንት ካጋሜ በኢትዮጵያ ኃያላን አገራት ጣልቃ እንዲገቡ እስከመግለፅ ሔዷል። ታንዛንያም በUNSC የያዘችው አቋም ይታወቃል። እነዚህ አገራት ከኢትዮጵያ ስለሚቀርብላቸው የኃይል አማራጭ አጀንዳ ያነሱ የነበሩ ናቸው።
● ኢትዮ-ሱማሊያ : እንደአገር ከሚራመድ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ይልቅ የመሪዎች ወዳጅነት ቅድሚያ ተሰጥቶት ከፕረዝደንት ፎርማጆ ጋር የተያያዘ ክር ነው። ይህ ሁኔታ ከሞቃዲሹ ምርጫ በኋላ የሚሆነውን የምናየው ሆኖ የዐቢይ-ፎርማጆ ፖለቲካ Defacto state ለሆነችው ሱማሊላንድ የፈጠረው የመገለል ስሜት ይታወቃል።
● ኢትዮ-ደቡብ ሱዳን: በህልውናዋ ላይ ትልቅ አሻራ ያላትን ኢትዮጵያ ለዘላቂ ሰላሟ ትለማመን እና ታማክር የነበረችው አገር ዛሬ ለኃይል ሚዛን የምንመላለስባት ሆናለች።
በአጠቃላይ በቀጠናው ኢትዮጵያ የነበራት ስፍራ ሲመዘን ⁽⁽አመርቂ⁾⁾ የተባለው ስራ ምንድን ነው?
ኢጋድን እየመራች ያለችው አገር በሱማልያና ኬንያ ፣ በራሷ በኢትዮጵያና በሱዳን ፣ በዩጋንዳና ታንዛንያ መካከል የተፈጠሩ ግጭቶችና አለመግባባቶች የት ደረሱ?
➵ በዓለም ዙሪያ ምዕራባውያን ምን እያሉ ነው? ዛሬ የቡድን ሰባት አባል አገራት ምን አሉ? ባለፈው አንድ አመት ወይም ከለውጡ ወዲህ ምን ያሕል የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ሳብን?
እኛ ብንቀበለውም ባንቀበለውም ስለኢትዮጵያ ⁽⁽ባለሁለት አኃዝ ተከታታይ እድገት⁾⁾ ያወሩ የነበሩ ሚድያዎችና ዲፕሎማቶች ዛሬ ስለዘር ማፅዳት እየዘገቡና እየተናገሩ ⁽⁽አመርቂው⁾⁾ ስራ ምንድን ነው?
https://www.facebook.com/animut.abraham ... 3674963569