Page 1 of 1

“በዶ/ር ሙሉ ነጋ የሚመራው የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳድር ለጁንታው በድብቅ የጦር መሳርያ ያስታጥቅ ነበር” Geez Media

Posted: 03 Apr 2021, 15:24
by Ejersa
በትግራይ ሲሰራ የነበሩት ወንጀሎች ኣንድ በኣንድ እየወጡ ይገኛል እየጮህን ያለነው በምክንያት ነው። ኣሳዛኙ እና በኣገር ክህደት የሚያስከስሰው የጦር መሳሪያ ወደ ህወሓት ማቀበልና የህዝብ ንብረት ዝርፍያ በበላይነት በዶ/ር ሙሉ ነጋ የተመራው የወንጀል ውስብስብ እንሆ።

የወዳደቁ ብረታ ብረት በሚል ሽፋን የጦር መሲርያ ፣ኮምፒተሮች ፣ጀነሬተሮች፣ ሞተር ሳኪል፣ፎቶ ኮፒ፣ማሽነሪዎች ወዘተ.... ከታች በምታዩት ንግድ ፍቃድ ባላቸው ሰዎች ከትግራይ እንዲወጣ
በማድረግ፤የጦር መሳርያው ለጁንታ ታጣቂ ይሰጡታል ሌላው ንብረት ደሞ ከትግራይ ውጪ እንዲቸበቸብ ተደርጓል።

በጣም የሚገርመው እነዚህ እቃዎች የያዙ መኪኖች ኬላ ላይ እንዳይፈተሹ የትግራይ ኮምሽነር መንግስትኣብ ኬላ ላሉ ሰዎች ያዝ ነበር። መኪኖቹ የይለፍ ፍቃድ የሰጠው የትግራይ የንግድ ቢሮ ሃላፊ ዮሴፍ(1997 ዓ.ም የትግራይ ንግድ ኢንዳስትሪ የነበረ እና ሰው ያስለቅስ የነበረ ሙሰኛ ጁንታ ነው) ፣ምክትል ቢሮ ሃላፊ አዳነ ሲሆኑ ኮምሽነር መንግስትኣብም ተባባሪ ነው። የዚህ ሁሉ በበላይ የሚያስተባብር ግን ዶ/ር ሙሉ ነጋ ነው።

የወዳደቁ ብረታ ብረት በሚል ሰበብ የጦር መሲርያ፣የቢሮ ቁሳቁሶች እና ሞተር ሳይክል ወዘተ የጫኑ መኪኖች በየኬላው ሳይፈተሹ መኪኖቹ ወጅራት ከደረሱ ቦሃላ ዓዲ ሓና የሚባል ቦታ ወረድ ብሎ ገረብ ሸለላ በተባለ ቦታ የጦር መሰርያው ተራግፎ እዛ አከባቢ ላሉ የጁንታ ታጣቂዎች ይሰጥዋቸው እንደነበር እና የቀረው የቢሮ እቃ እና ሌሎች እቃዎቻ ደሞ ከትግራይ ውጪ ሊሸጥ ይወጣ እንደነበር የአከባቢው ነዋሪዎች ለግዕዝ ሚዲያ ገልፀውልናል።

በትግራይ ክልል ብዙ የቢሮዎች መውደማቸው ይታወቃል ይሄን ተገን በማድረግ ብዙም ያልወደሙ እቃዎች ወድመዋል በሚል ሰበብ ነው ከትግራይ እየወጡ እንዲሸጡ የተደረጉት።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳድር ቁንጮ አመራር በየቦታው ለተበታተነው ጁንታም በድብቅ ሲያስታጥቅ ነበር፣ሙስና ላይ በሰፊው ገብቷል ስለዚህ የፌደራል መንግስት ጊዚያዊ አስተዳድሩ ቁንጮ አመራር የሰሩት ወንጀል አጣርቶ በሃገር ክህደት እና በሙስና ሊጠይቃቸው ይገባል።

ጀግና የሃገር መከላከያ ሰራዊት ዋጋ ከፍሎ ያመጣው ለውጥ እንዳይቀለበስ የሚመለከተው ሁሉ ሊረባረብ ይገባል። ጁንታው አለሁ የሚለው በጊዚያዊ አስተዳድር የሰጋቸው ሰዎች ተማምኖ ነው።