"በኢትዮጵያ መንግስት ላይ እየደረሰ ያለው ግፊት እርምጃዎችንም ጭምር ያካተተ መሆን ኣለበት ምክንያቱም ጦርነቱ የመቆም ኣዝማምያ እያሳየ ኣይደለም" ዶይቸ ቬለ ራድዮ
Posted: 30 Mar 2021, 17:10
ዉይይት፣ የምዕራባዉያን ግፊትና ኢትዮጵያ
ትግራይ ዉስጥ ተፈፀመ የተባለዉ የሰብአዊ መብት ጥሰትና የኤርትራ ጦር ኢትዮጵያ ዉስጥ መግባቱን ሲያስተባበሉ የነበሩት የኢትዮጵያ ባለስልጣናት አቋማቸዉን የለወጡ መስለዋል--- መንግስት የሚቆጣጠረዉ የሰብአዊ መብት ኮሚሽንም በተለይ አክሱም ዉስጥ የሰብአዊ መብት ጥሰት መፈፀሙን የመጀመሪያ ደረጃ ባለዉ ዘገባዉ አስታዉቋል።
ጤና ይስጥልኝ እንደምን ዋላችሁ።ለዛሬዉ የምዕራባዉያን ግፊት የኢትዮጵያ መንግስት አፀፋና ዉይይታችን የኢትዮጵያ ሠላም የሚል ዘርዝር ያለ ርዕስ ሰጥተነዋል።የኢትዮጵያ መንግስት ትግራይ ዉስጥ «ሕግ ማስከበር» ባለዉ ወታደራዊ ዘመቻ ከቀድሞዉ የትግራይ ገዢ ፓርቲ ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሓት) ጋር የገጠመዉ ጦርነት፣ የደረሰዉ ጥፋትና ዉጤቱ የዓለም ርዕስ እንደሆነ ነዉ።
በጦርነቱ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል፣ተሰድደዋል፣ የሴቶችን መደፈር ጨምሮ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈፅሟል የሚለዉ ዘገባ ደግሞ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአዉሮጳ ሕብረትንና የዩናይትድ ስቴትስን ልዩ ትኩረት ስቧል።የኢትዮጵያ መንግስት በጦርነቱ ለተጎዳዉ ሕዝብ ርዳታ እንዲደረስ፣ የደረሰዉ ጥፋት በገለልተኛ ወገኖች እንዲጣራ እንዲፈቅድ፣ በጦርነቱ ተካፍለዋል የተባሉትን የኤርትራ ጦር፣ የአማራ ልዩ ኃይልንና ሚሊሺያን ከትግራይ እንዲያስወጣ በምዕራባዉያን መንግሥታት ከፍተኛ ጫናና ግፊት ሲደረግበትም ነበር።
Follow the below link to listen to the discussion ....
https://www.dw.com/am/%E1%8B%89%E1%8B%A ... er-sharing