ባሕላዊው ጋዜጤኛ ደረጀ ሃብተወልድ ማን ነው ?
Posted: 30 Mar 2021, 08:32
በስንት ኩረጃ እና ጉቦ እስከ 7ኛ ክፍለ የደረሰ እና እንግሊዝኛን ቋንቋ እንደ ጦር የሚፈራው ነገር ግን ራሱን እንደ ጋዜጠኛ የሚያየው ባሕላዊው ጋዜጠኛ ደረጀ ሃብተወልድ ማን ነው ?
ተፃፈ በኤርሚያስ ለገሰ
አንዳንዴ ወርዶ መናገር ያስፈልጋል መሰለኝ!
አሁን አንተ ጋዜጠኛ ነህ? የውስጣችንን ገመና ጊዜው እስኪመጣ አንናገረው ብለን እንጂ፤ የአምስተርዳም ስቱዲዮ በአረቄና ቢራ ተሰክሮና ጥንቢራ ዞሮ ዜና እና ትንታኔ እንደሚሰጥ ድፍን አውሮፓ እንደሚያፍርባችሁ ታውቃለህ? ኤዲተሮቻችሁ እንዴት እንደሚሸማቀቁባችሁ አታውቅም ማለት ነው? ስም ልጥራ እንዴ? በተቃራኒው እናንተው ሰክራችሁ የምትሰሩት ዜና " የአማራ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት አቶ አገኘሁ ተሻገር ጠጥተው አሽከረከሩ" አልነበር? ተው!
ጊዜው ሳይደርስ አታስለፍልፈኝ።
ኧረ ለመሆኑ ከሚባረሩት የመጀመሪያው ረድፍ ሆነህ የእኛ ቀድሞ መልቀቅ በድንጋጤ ትንሽ እንዳቆዩህ የማይታወቅ ይመስልሃል? አሁን ሚዲያው በጎፈንድ ሚ ሲታመስና ከአንዳርጋቸው ጽጌ ጋር ዱላ ቀረሽ ድብድብ ውስጥ ሲገባ ወንድማገኝ ጋሹ " እነ ደረጄ እንደ አሮጌ ኮልኮሌ የትም ሲወረወሩ?" ማለታቸውን ላስታውስህ?...ለመሆኑ " እለታዊ" የሚባለው ፓኬጅ ውስጥ ለምን እንዳልተካተትክ ታውቃለህ?
ወይንስ አቶ ነዓምን ዘለቀ " ደሬ 360 የሚባል ሚዲያ እየከፈቱ ስለሆነ ስደባቸው?" የሚል ትዕዛዝ ሲሰጥህ ( በረከት ያቋቋመው ዋልታ እያለህ ምን እንደምትሰራ ስለሚያውቅ) ምን ምላሽ እንደሰጠህ ላስታውስህ እንዴ? "ለ7ኛ ጨ እልክለትና እሱ እንዲሰድባቸው አደርጋለው" ነበር ያልከው።
ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዲሉ አቶ ነዓምን ዘለቀ <<ሞት ነው የሚያለያየኝ>> ብሎ ከሚለው ድርጅቱ ከነበረው ግንቦት ሰባት መልቀቂያ አስገብቶ የወጣበት መሰረታዊ ምክንያት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት መሆኑን ታውቃለህ? ግዴለህም ትንሽ ደፈር ብለህ ጠይቅና እኔን ውሸታም አድርገኝ! ደብዳቤው ራሱ ነዓምን በሚዲያው እንዲነበብ ስላደረገ እዛው ታገኘዋለህ።
ይሄ ብቻ እንዳይመስልህ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ዲሲ ሊመጡ ሶስት ቀን ሲቀራቸው ዲያቆን ዳንኤል የሰራው ሸፍጥና ተንኮል በኢሳት ላይ መግለጫ መሰጠቱን አታውቅም ማለት ነው? በል ወደ ኃላ ሄደህ ተመልከት። ከቻልክ ሰዎቹንም ጠየቅ፣ ጠየቅ አድርግ። ከለውጡ በፊት ሚዲያው በዲያቆን ዳንኤል ክብረት ላይ ያለውን አመለካከትና የሰበሰባቸውን መረጃዎች ጠይቅ። በተለይም ዲያቆኑ ስለ ሟቹ ፓትርያርክ በመጽሔት የወጣው ሚዲያው ውስጥ ተሰንዶ ተቀምጧል።በተለያዩ ጊዜያቶች በውይይትም ተደጋግሞ ይነሳ ነበር። ያው! ሰውየው ማን እንደሆነ እና መረጃው ማን ጋር እንዳለ ታውቀዋለህ ብዬ ነው ስም ከመጥራት የተቆጠብኩት።
የሆነው ሆኖ እኔ በግላጭ መረጃውን አቅርቤያለሁ። የጋዜጠኛ ሀ!ሁ! ለ!ሉ! ደግሞ የመረጃውን ትክክለኝነት ማጣራት ነው። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደሩ ዶክተር ሙሉ አለ! መጠየቅ ይቻላል። የካቢኔ አባላት አሉ። እነሱንም መጠየቅ ይቻላል። የተባረሩት አሉ። እነሱንም መጠየቅ ይቻላል። የምን ሳያጣሩ ዘሎ ፊጢጥ ማለት ነው?
እንዴት ነው መላው፣
እንዴት ነው መላው፣
እይተነው ጊዜ ወደሚያደላው!
በተረፈ በሚዲያ ማብራራያ ትሰጥበታለህ ላልከው ምላሼ " አዎ!" ነው። ያውም! በቀጥታ ስርጭት ከ5ሺህ ሰው በላይ በየቀኑ (ከሰንበት እስከ ሰንበት) እየተመለከተኝ። ያውም! በ24 ሰዓት ውስጥ ከ70ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን በዩቲዩብ በጉጉት እየተከታተሉኝ! ያውም ሚሊዮኖች በመረጃ ቲቪ ሳተላይት እየተከታተሉኝ! ያውም!እንዳንተ ያለው ተደጋፊ ተደማሪ እና ውታፍ ነቃይም ጨጓራው እየተላጠ እየተከታተለኝ። ምን አማራጭ አላችሁ ብለህ ነው? መንግስት እንደሆነ እንኳን ሊመለከታችሁ ከሚዲያ ሞኒተሪንግም አስወጥቷችኃል። እንደ ኢቲቪ! ፋና! ዋልታ! OBN!
ለማንኛውም የአዲስ አበባ ጥያቄ የህልውና ጥያቄ ስለሆነ በተለያየ ሴራ ጥያቄውን ለማዳፈን የሚመጡትን ያለ ምህረት እንታገላለን። ይኸው ነው!
Source: https://www.facebook.com/kalkidan.legesse.58