Page 1 of 1

ብልጽግና የጎሳ ቡድኖች ጥርቃሞ እንጂ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ፖለቲካ ፓርቲ አይደለም

Posted: 30 Mar 2021, 00:12
by Horus
ይህ የማህበረ ሰብ ሳይንስ ነው። የትግሬ ብልጽግና ፓርት፣ ያማራ ብልጽግና ፓርት፣ [deleted] ብልጽግና ፓርት፣ የኦሮሞ ብልጽግና ፓርት፣ የሱማሌ ብልጽግና ፓርት፣ የደቡብ ዕራብ ብልጽግና ፓርት፣ ያዲሳባ ብልጽግና ፓርት፣ የሚባሉት የጎሳ ቦድኖች በቅርቡ እርስ በርስ ይዋጋሉ ወይም ይፈርሳሉ ።

ብልጽግና ፓርት አንድ ድርጅት ሆኖ መቀጠላ ካሻው የጎሳ ክልሎችን አፍርሶ የኢትዮጵያ ፓርቲ መሆን ግድ ይለዋል ። አሁን ያለው ብልጽግና ፓርት የዘር ፓርቲ እንጂ የኢትዮጵያ ፓርቲ አይደለም !!


Re: ብልጽግና የጎሳ ቡድኖች ጥርቃሞ እንጂ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ፓርቲ አይደለም

Posted: 30 Mar 2021, 00:33
by Horus
ብልጽግና አንድ ጎሳ ከሌላ ጎሳ እንዴት እንደ ሚበልጥና ይበልጥ ሃያል ጦር አቁሞ ለማይቀረው የእርስ በርስ ጦርነት መዘጋጂያ የዉሸት ግዜያዊ ቅንጅት እንጂ እውነተኛ የኢትዮጵያ ድርጅት ከቶም ሊሆን አይችልም ። አንድ ሰው በኢትዮጲያወነቱ የምት ሄዶ መናገር፣ ምደራጀት፣ መመረጥ የማይልበት ጭራቅ የሆነ የፖለቲካና የፓርቲ ሲስተም ኢትዮጵያዊ ብሎ የሚጠራው ካለ እሱ ደደብ የፖልቲካ ደንቆሮ ማለት ነው።

Re: ብልጽግና የጎሳ ቡድኖች ጥርቃሞ እንጂ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ፓርቲ አይደለም

Posted: 30 Mar 2021, 00:36
by TGAA
Prosperity party by design is the most deformed party that ever existed. It has a Ethiopian nationalistic aspirations, democratic wishes , and capitalist drive but it tries to plant all these in weyene kill farm, watering it with hate, covering all telltale signs of Ethnic cleansing .

Re: ብልጽግና የጎሳ ቡድኖች ጥርቃሞ እንጂ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ፓርቲ አይደለም

Posted: 30 Mar 2021, 00:37
by Masud
Yes in the eyes of Fuga Uragies, but it is recognized political party and ruling party. Duqet!

Re: ብልጽግና የጎሳ ቡድኖች ጥርቃሞ እንጂ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ፓርቲ አይደለም

Posted: 30 Mar 2021, 00:55
by Horus
አንድ ዘመናዊ የፖለቲካ ፓርቲ ከዘመናዊ የፖለቲካ ሲስተም ጋር የተሳሰረ ነው። አንድ መንንግስት ማለት ያንድ አገር እስቴት የሚመራውና ፖሊሲ የሚያወጡለት ፓርቲዎች ናቸው። 9 የተለያዩ ጎሳዎች ሁሉም አንዱን ለመቅደም በሰላምም በጦርም የሚዋጉ የዘር ፓርቲዎች የኢትዮጵያ አንድ ሃገራዊ ፖሊሲና ኢትዮጵያዊያን በግለሰብ ዜግነታቸው የሚያከብር፣ የሚያስችል ፓርቲ ከቶን ሊሆን አይችልም። ይህ የዘር ጥርቃሞ ዞሮ ዞሮ የጎሳ ከበርቴው ኪራይና ጉቦ መሰብሰቢያ መሬት መቸብቸቢያ መሳሪያ ነው የሚሆነው !

Re: ብልጽግና የጎሳ ቡድኖች ጥርቃሞ እንጂ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ፓርቲ አይደለም

Posted: 30 Mar 2021, 01:40
by Horus
የብልጽኛ ፓርቲ ትልቅ ድክመትና ያቢይ አህመድም ደካማ ጎን ምን እንደ ሆነ ልንገራችሁ ።
መደመር ያቢይ ሃሳብ እንጂ የብልጽግና ሃሳብ አይደለም ። ብልጽኛ የአንድ ፓርቲ እስትራተጂ (አሰራር ዘዴ) እንጂ ፍልስፍናም፣ ቲኦሪም፣ ር ዕዮተ አለም አይደለም። በደመመር በሚባል የማህበረ ሰብ ሳይንስ የቆመ የንግስት ስርዓት የለም ።

ትልቁ ስህተትና ድክመት መደመር ማለት አቢይ እንጂ ብልጽግና አይደለም ።

መደመር የሚባለው ሃስብ በአቢይ አህመድ አንጎል ወስጥ ህብር፣ ውህደት፣ ቅንብር ሊኖረው ይችላል ። ግን በብልጽግና አባልትና እና በድርጅቱ ውስጥ ያለ ርዕዮተ አለም አይደለም።

ስለዚህ ትልቁ የዚህ ፓርቲ ድክመትና ያቢይም ድክመት አቢይ አህመድ እና ብልጽግና ፓርቲ ለየቅልና አንድ ያልሆኑ ነገሮች ናቸው።

አቢይ የሚፈልገው በግለ ሰብ ዜጋ ላይ የተደራጀ አገራዊ ኢትዮጵያዊ ፓርቲና ፕሬዚዳንታዊ የመንግስት አወቃቀር ነው።

ብልጽግና ግን በውጭ መልኩና በመልክቱ ያቢይ አህመድ ምስል ይመስላል ፤ በውስጡና በተግባሩ እንደ ኩበት የተፍረከረከ የጎሳ ጥርቃሞ ነው ።

ይህ ነው የዚያ ፓርቲ ግዙፍ ድክመት !