@Ethio 360:- መካድ የማይቻለው የEthio 360 ድንቁርና (ሀብታሙ አያሌውን እንደሳማያ)
Posted: 28 Mar 2021, 12:59
- በኢትዮጵያ ብዙሀን ሕዝብ የለም ይላል፡፡
- አለ ወይም የለም በማለት እዚህ ላይ እኔም ማረጋገጥ ስለማልችል እተወዋለሁ፡፡ ነገር ግን ይህን ለማወቅ የሕዝብ ቆጠራ (up-to-date census) ብቸኛው መንገድ ነው፡፡ የሕዝብ ቆጠራን ግን ስላማዊ ስልፍ ወጥቶ የተቃወመና ያስቀረው እኮ የአማራ ክልል ነው፡፡
- ሀብታሙ ይህን መናገር አይነካካውም፡፡ ይልቁንስ ማተቤ ሰለሞን እንደቆጠረው እያለ ደብተራን በእማኝነት ይጠራል፡፡ አማራማ ኦሮሞን ሲያሳንስና ሲያጠፋ የኖረ ስለመሆኑ እስካሁን ያልገባቸው ደደቦች በEthio 360 ውስጥ ብቻ የቀሩ ይመስለኛል፡፡ አማራ ብቻ ተለይቶ ተጨፈጨፈ እያሉ ያለቅሱና የሟች ቁጥር ተለይቶ ሪፖርት ሲርብ ደግሞ ሬሳ ተቆጠረ እያሉ ሌላ ለቅሶ ሲያቀልጡ እንደነበረው ማለት እኮ ነው፡፡
- የአማራ ሕዝብ ቆጠራ ይቅር እያለ ሰልፍ ሲወጣ የESAT ሲሳይ አጌና ቆጠራ ከተካሄደ ብዙ ሕዝብ ወደ ኦሮሞነት ይመለሳል እያለ ለሰፈኛው ለቅድመ ቅስቀሳ በሚዲያቸው ቀርቦ ይወራጭ ነበር፡፡ ቪዲዮአቸውን ማዳመጥ ነው፡፡
- ምርጫን በሚለከትም እኔ ኦሮሞ የማይሳተፍበት ይህ ምርጫ ተብዬ እንዲካሄድ ደጋፊ አይደለሁም፡፡ ሆኖም እንደነ ሀብታሙ አያሌው ተቃውሞዬ ሀብት ይባክናል በማለት አይደለም፡፡ በሀገር ደረጃ የምናስብ ከሆነ በምርጫ ምክንያት (ተካሄደም/አልተካሄደም) የሚባክን ሀብት አይኖርምና፡፡ አካውንቲንግ ተምሬያለሁ፣ ኢኮኖሚክስ ኮርስ ወስጃለሁ የሚለው ውታፍ ነቃዩ ኤርሚያስም የሀብታሙን አለማወቅ አልረዳውም እኮ፡፡ ከእውቀት ነጻ እንደመሆኑ መጠን ማለቴ ነው፡፡