በትግራይ የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈጸመው የአማራ ልዩ ሃይል በአሸባሪነት መፈረጅ አለበት! ኣለበለዚያ በወሎ ኦሮሞዎችና በሌሎች ላይ ጭፍጨፋ ላለማድረጉ ምንም ዋስትና የለንም - አፈንዲ ሙተቂ
Posted: 27 Mar 2021, 20:02
የአማራ ልዩ ሃይል በአሸባሪነት መፈረጅ አለበት!
ናትናኤል መኮንን የከሚሴ አካባቢ የፓርላማ ተወካዮች በተናገሩት ንግግር ተበሳጭቶ "እናንተንና ዐቢይን ከወያኔ ነፃ ያወጣችሁ የአማራ ልዩ ሃይል ነው" ብሎናል። እኛ "ግን የአማራ ልዩ ሃይል ተብዬው በአሸባሪነት መፈረጅ አለበት" ነው የምንለው። ምክንያቶቹ ሲዘረዘሩ የሚከተሉትን ይመስላሉ።
-- በትግራይ ህዝብ ላይ በፈጸመው አስከፊ የዘር ማጥፋት ጭፍጭፋ ህዝቦችን ከማቃቃር አልፎ የሀገሪቱ ስም ጠፍቷል።
--- በቅማንት ህዝብ ላይ ወሰን የለሽ የዘር ፍጅት አካሂዷል። ዛሬም ቅማንቶች እየሞቱ ነው።
--- በጃዊ ወረዳ ከሚኖሩት የጉሙዝ ተወላጆች መካከል 500 ሰዎችን በአንድ ቀን ገድሏል።
-- በመተከል ዞን የሚካሄደውን ትርምስ የሚያቀናብረውም ሆነ የሚመራው እሱ ራሱ ነው። ራሱ ባሰማራቸው ታጣቂዎች ህዝብ ይጨርስና "ኦነግ ሸኔ እንዲህ አደረገ" እያለ ይጮሃል (ዓላማውም ዞኑን በሃይል ወስዶ ወደ አማራ ክልል ማስገባት ነው)።
--- ባለፈው ሳምንት በወሎ ኦሮሞዎች ላይ የዘር ማጽዳት ዘመቻ ከፍቶ ህዝቡን ሲያምሰው ነበር።
--- በወለጋ የሚንቀሳቀሰውን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት መርታት ያቃተው የአብይ መንግሥት ከዓመት በፊት የአማራ ልዩ ሃይል ወደ ወለጋ ገብቶ ከመከላከያ ጋር በመሆን የጃል መሮን ጦር እንዲወጋ ጋብዞት ነበር። የአማራ ልዩ ሃይል ተብዬው ግን እዚያ ሲደርስ ሰላማዊ ኦሮሞዎችን መግደል ነው የጀመረው። በመከላከያ ውስጥ ያሉት ኦሮሞዎች ይህንን ሲከለክሉት ደግሞ ሌላ ድራማ አመጣ። ይህም በወለጋ የሚኖሩትን አማራዎች እየገደለ 'ኦነግ ሸኔ አማራውን ጨፈጨፈ፣ የአብይ መንግሥት ህዝቡን እያስጨረሰ ነው፣ ስለዚህ እርሱ ራሱ ኦነግ-ሸኔ ነው" እያሉ መጮኽ ነው።
--- ልዩ ሃይሉ ከሀገር ውስጥም አልፎ የሱዳን ሰራዊትን በመውጋት በሀገሪቱ ላይ ሌላ ዓለም አቀፍ ፈተና ጋርጧል።
--- ይህ ወሰን ተጋፊ የሆነው እጅግ ጽንፈኛ ሃይል "እገሌ ወረዳ የኔ ግዛት ነው፣ እገሌ ከተማ የኔ ናት" በሚል እብሪት ከአማራ ክልል ጋር የሚዋሰኑትን ክልሎች በሙሉ እየበጠበጠ ይገኛል።
-------
እኛ ከአማራ ህዝብ ጋር በሰላም እየኖርን ነው። የአማራ ልዩ ሃይል ግን አማሮችን እንድንጠላ እና እንድንዘምትባቸው ብዙ ጥረት አድርጓል። ሆኖም እንዲህ ዓይነት ዝቅጠት ውስጥ መቼም አንገባም። ህዝብና ታጣቂን ለይተን የምናውቅ ሰዎች ነን። ይሁንና ልዩ ሃይሉ በሀገር ላይ ሌላ ጉዳት ሳያደርስ በአሸባሪነት መፈረጅ አለበት እንላለን። ይህ ካልተደረገ በቀር ልዩ ሃይል ተብዬው በወሎ ኦሮሞዎችና በሌሎች ህዝቦች ላይ ተመሳሳይ ጭፍጨፋ ላለማድረጉ ምንም ዋስትና የለንም።
https://www.facebook.com/afendimutekiha ... 2270638202