Page 1 of 1

የትግሬ ነጻ አውጪ ለምን ወደቀ?

Posted: 25 Mar 2021, 01:41
by Horus
ለምንድን ነው የዎይኔ ከ 45 አመት ብክነት ከሽፎ ለሞትና ወድቀት የበቃው? ለምንድን አንድ አላማ ወይም ጥረት በውድቀት የሚያበቃው? ለምንድን ነው ትህነግ የትግሬ ህዝብ ወኪል ነኝ፣ ድምጽ ነኝ እያለ 45 አመት ላይ ታች ሲል ሁልግዜ በውድቀት የሚጠናቀቀው? ይህ ለምን ሆነ?ይህኮ መሰረታዊ፣ መሰረታዊ ጥያቄ ነው።

እኔ ሆረስ ነኝ፣ ቃላት አልሰነጥቅም ። መልሱ አጭርና ቀላል ነው።

ምንም ነገር፣ ማንኛውም ነገር አለ ሞዴል አይሰራም ። ሞዴል የሌለው ነገር በአለም ላይ ተፈጥሮ አያቅም ። ፍጥረት (ኔቸር) ራሷ ሞዴል አላት ። እንዲያውም የኛ ሰው ሰራሽ ካልችር ሁሉ ሞዴል የሚገኘው ከፍጥረት ነው። ባንድ ቃል ሶስት መደምደሚያዎችን መጥቀስ ይቻላል።

አንድ፣ የተሳካ፣ የሚሳካ ነገር ሁሉ የተሳካው የሚሳካው ትክክለኛ ፣ እውነተኛ ፣ ሞዴል ስላለውና በዚያ ሞዴል መሰረት ስለተሰራ ነው ። ለምሳሌ ኢትዮጵያ የምትባል ክስተት ወይም ሪያሊቲ ያለውው፣ ምትኖረው ትክክለኛ፣ እውነተኛ ሞዴል ላይ ስለቆመች፣ ትክክለኛ ፓራዳይም ላይ ስለ ተሰራች ነው። ትህነግ የፈረሰው የተሳሳተ ሞዴል እና ዲዛይን መሰረት ስለቆመ ነው ።

ሁለት፣ ምንም ነገር ወይም ማንም ሰው አንድ የስራ ሞዴል፣ አንድ የመገንቢያ ሞዴል እስከ ሚያገኝ ድረው ምንም ነገር መወሰን፣ ማቀድ፣ ማሳካት ወይም መፈጸም አይችልም ። ብዙ ሰዎች፣ ፓርቲዎች፣ ድርጅቶች ወዴት እንደ ሚሄዱ፣ ወዴት እንደ ሚዞሩ ማወቅ መወሰን ተስኖአቸው ፈዘው ደንዝዘው ሚኖሩት ሚቀሩት ሞዴል አልባ ስለሆኑ ነው። ሞዴል ወይም ፓራዳይም የሌለው ምንም መሆን ምንም ማድረግ አይችልም ። ዛሬ በኢትዮጵያ ብዙ ብዙ የጎሳ ህልመኞች ፈዘው የቀሩት ሞዴል ስለሌላቸው ነው ።

ያ ደሞ የኢትዮያ ሞዴል ይባላል። ከኢትዮጵያ ሞዴል ውጭ የሆነ ነገር መሆን የሚመኝ የሳይኮሎጂ ህመምተኛ የጎሳ ደንቆሮ ብቻ ነው ።

ሶስት፣ ማንም ሰው። ማንም ድርጅት፣ ፓርቲ፣ ንቅናቄ፣ ግንባር የተሳሳተ፣ የዉሸት፣ የተረት፣ የቅዠት አላማ፣ ምኞት፣ ሞዴል ወይም የዉሸት ፓራዳይም ይዞ አንድ ነገር ለማድረግ ቢነሳ፣ ቢለፋ፣ ቢታክት በፍጹም ስኬታማ ሊሆን አይችልም ።

ዛሬ እነ ዎያኔ ይህን ሁሉ ጩሀትና ድራማ እየፈጠሩ፣ ይህን ሁሉ አቧራ እያስነሱ የትም ያልደረሱት፣ የትም የማይደርሱት የሚጠቀሙበት ሞዴል፣ የሚመሩበት ፓራድይም፣ የሚያዩበት አይን የተሳሳተ፣ ዉሸታም፣ የሌለ የማይሆን ሞዴል ስለሆነ ነው። ለዚህ ነው ትህነግ ከታሪክ የተወገደው !

ማለትም አንድ ሰው፣ አንድ ድርጅት ፣ አንድ ሲስተም የሆነ አላማ አንስቶ ስኬት ለመፍጠር ራሱ የሚያስብ፣ የሚፈጥር፣ የሚመዝን ፣ የሚረዝን አንጎልና ኢንተለጀንስ እንዲኖ66ረው ያስፈልጋል ። ችግር መፍታት የማይችል አንጎል ዝቅተኛ ኢንተለጀንስ ያለው፣ የማሰብ፣ የመፈልስፍ፣ የመፍጠር ችሎታው የመነመነ የእውቀት ድሃ ሰው ወይም ፓርቲ ነው።

ይህ መሰረታዊ ሳይንስ ነው ዛሬ በኢአትዮጵያ የጎሳ አይምሮ ውስጥ ያለው የኢንተለጀንስ አልባነት ቀውስን ፍንትው አድርጎ የሚገልጽልን !!!
ዎያኔ ለምን ወደቀ የሚለው ጥያቄ ህን ነው መልሱ !

ይህ የባህሪ ህግ ለሌሎችም በምኞትና ምናብ ላይ ስሜት ለሚገፋቸው ትምህርት ይሁን !!!