Page 1 of 1

አራቱ ሃያላን መንግስታትና የኢትዮጵያ ውጭ ፖሊሲ

Posted: 24 Mar 2021, 22:27
by Horus
ሃያላኑ፤
1. አሜሪካ
2. ቻይና
3. ሩሲያ
4. ህንድ

በመሰረቱ ኢትዮጵያካራቱም ጋር ወዳጅ ነች ። ግን አሜሪካ ጣልቃ ስትገባ የቀሩት ያለም ሃያልን አስቆሙት ። ከዚህ በኋላ አሜሪካ እርጉን ዝር አያደርግም።



Re: አራቱ ሃያላን መንግስታትና የኢትዮጵያ ውጭ ፖሊሲ

Posted: 24 Mar 2021, 22:52
by Horus
የኢዜማ ፓርቲ እስትራተጂክ ራዕይ ምን እንደ ሆነ አላቅም ። የብልጽግና ፓርቲ አቢይ አህመድ እንዳለው ...

በ2032 (ባውሮፓ) የአፍሪካ ምሳሌ መሆን!
በ2051 የአለም ምሳሌ መሆን!

ይህን የሁሉም ዜጋ ግላዊ አላማ መደረግ አለበት !!!

Re: አራቱ ሃያላን መንግስታትና የኢትዮጵያ ውጭ ፖሊሲ

Posted: 25 Mar 2021, 00:18
by Horus
በ2031 ኢትዮጵያ 200 ሚሊዮን ሕዝብ በአፍሪካ ቁጥር አንድ ታዳጊ አገር!!

Re: አራቱ ሃያላን መንግስታትና የኢትዮጵያ ውጭ ፖሊሲ

Posted: 25 Mar 2021, 02:13
by Horus
ያካባቢ ሃይሎች፤
1. ግብጽ
2. እስራዔል
3. ቱርክ
4. ኢራን
5. ሳዉዲ
6. አረብ ኢምሬት

ከነዚህ አንዳቸውም በቁርጥ ቀን ከኢትዮጵያ ጋር አይቆሙም

Re: አራቱ ሃያላን መንግስታትና የኢትዮጵያ ውጭ ፖሊሲ

Posted: 25 Mar 2021, 13:11
by Horus
ጎረቤቶች
ኤርትራ
ሱዳን
ደቡብ ሱዳን
ሱማሌ እስቴቶች
ኬኒያ
ጂቡቲ


እነዚህ አገሮች እያንዳንዳቸው ከአካባቢው ህይሎች ጋርና ከአራቱ ሃያላን ጋር ያላቸው ዝምድና ይለያያል

ግን እነዚህ 6 የጎረቤት አገር ሕዝቦች በሙሉ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር አንድ ናቸው ፣ የተጋቡ፣ የተዛመዱ ሕዝቦች ናቸው ። ምሳሌ የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝቦች አንድ ህዝብ ናቸው ። የሱዳን ኑቢያ በስረ ግንዱ ፣ ከዚያም ለ50 አመት በሁለቱ መካከል በነበረው የቅርብ ህዝባዊ መደባለቅ እዚህም ፅር አለ። የደቡብ ሱዳን ህዝብ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝብ ናቸው። ሱማሌ እንዲሁ፣ ኬኒያና ኦሮሞ ብለን ስንዘጋ ያለው ሃቅ ያክሪካ ቀንድ ህዝብ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ናቸው።

Re: አራቱ ሃያላን መንግስታትና የኢትዮጵያ ውጭ ፖሊሲ

Posted: 25 Mar 2021, 13:43
by Horus
ከላይ ያሉት 6ቱም አገሮች እና ኢትዮጵያም ጭምር እያንዳንዳቸው የውስጥ ውስብስብ ችግሮች አሏቸው ። ለምሳሌ

ሱዳን የፖለቲካ ችግር አለባት፣ ከግብጽ ጋር፣ ከኢትዮጵያ፣ ከደቡብ ሱዳን፣ ዳርፉር እያለ ችግሯ ይበዛል።


መጠቃቃት ለሚፈልጉ አገሮችና ቡድኖች አንዱ ላንዱ ችግር ለመሆን በቂ የውስጥ ተባባሪዎች ያሉበት ፍርክርክ ያለ ቀጠን ነው ያፍሪካ ቀንድ ።

ለዚህ ነው ኢትዮጵያ የዚህ ቀጠና ማዕከልና አደራጅ ሆና የምትቀጥለው ።

የአፍሪካ ቀንድ ማለት ኢትዮጵያ ነች !

Re: አራቱ ሃያላን መንግስታትና የኢትዮጵያ ውጭ ፖሊሲ

Posted: 25 Mar 2021, 15:30
by Horus
ኢትዮጵያ እንደ ሕዝብም እንደ አገርም ጥንካሬዋ የሚታወቀው በሰላም በደስታ ግዜ አይደለም ። በሰላም ግዜ ሁሉ ጎበዝ ነው ። የኢትዮጵያ ማያላቅ ሃይልና ቀጣይነት እየተረጋገጠ ያለው አሁን ነው። ይህች አስገራሚ አገር በዚህ ሁሉ የውስጥ፣ የውጭ ጠላት፣ ግፊት ተሸክማ አለምንም ሌላ ድራማ ሕይወቷን ትገፋልች !!!